>

በሁለት ምእራፍ የተከፈለው የኢህአዴግ የተቃርኖ ተውኔት ፍፃሜው ምን ይሆን? (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

በሁለት ምእራፍ የተከፈለው የኢህአዴግ የተቃርኖ ተውኔት ፍፃሜው ምን ይሆን?
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ህወሀት /ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ሲወጣ ይከተለው የነበረው የአገዛዝ ዘዴ በህገ መንግስት የብሄር ብሄረሰቦች መብት እስከ መገንጠል ይከበራል የሚል ሲሆን በድርጅት ደግሞ ዴሞክራሲያዊ መአከላዊነትንና አብዮታዊ ዴሞክራሲን አዳቅሎ ህወሀት በነፃ አውጭነት መንፈስ ሌሎችን የግንባሩ አባልና አጋር ድርጅቶች ለህወሀትና በተለይም ለአቶ መለስ የለማወላወል ትእዛዝ እንዲቀበሉና እንዲፈፅሙ ማድረግ ነበር።ይህ የመጀመሪያው ምእራፍ ተቃርኖ በአቶ መለስ ሞት ፣ በህገመንግስት የተደነገገውን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የግንባሩ አባል ድርጅቶች መጠየቅ በመጀመራቸውና በህዝብ ትግል ተሸንፎ አዲስ ጠቅላይ ምንስትር መርጦ ሁለተኛውን የተቃርኖ ምእራፍ ጀምሮዋል።አዲሱ ጠቅላይ ምንስትር የሚከተሉት ስልት በህገ መንግስት የተደነገገውን ራስን በራስ የማስተዳደር መብትና የድርጅቱን ዴሞክራሲያዊ መአከላዊነት ባህል በመራቅ አንድነት ፍቅርና ይቅርባይነትን መርህ አድርጎ በኢህአዴግ የተከፋውን ወገን በማሰባሰብ ለውጥ ማምጣት የሚል ይመስላል።በህገ መንግስት የተከፋፈለውን ሀገር  ስለ አንድነትና መደመር በማስተማር መሰብሰብ ባለመቻሉ የሀይል እርምጃ መውሰድ ጀምሮዋል።
በኔ እምነት ሁለቱም  ምእራፎች ከመርህና ህጋዊ አሰራር ያፈነገጡ ስለሆነ የኢህአዴግን ማርጀትና የተፈጥሮ የእድገት ደረጃ መገለጫወች ከመሆን ባለፈ የሀገራችንን ውስብስብ ችግር የመፍቻ ዘዴ ሊሆኑ አይችሉም።በመሆኑም ግዜው ሳይረፍድና ችግሩ ሳይወሳሰብ በመርህ ላይ የተመሰረተ የሀገራችንን ችግር የሚመጥን የለውጥ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።
Filed in: Amharic