>

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ  (ከትግርኛ ቃል በቃል የተተረጎመ)

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ 
(ከትግርኛ ቃል በቃል የተተረጎመ)
በሶማሌ ክልል የተፈጠረው ግጭት ወደ ከፋ ሁከት እና ብጥብጥ ሊገባ የሚችል ተግባር ስለሆነ  ጉዳዩ በእስቸኳይ ቁጥጥር ሥር እንዲውል እና የሕግ የበላይነት እንዲከር የትግራይ ክልል መንግሥት ጥሪውን ያቀርባል።
ምንም ዓይነት ችግር ቢፈጥር  በሕጋዊ እና ኃላፊነት በተሞላ አግባብ እንጅ በኃይል ለመፍታት መውደድ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው እና ለፌዴራላዊ ሥርዓታችን መፍረስ አደጋ በመሆኑ በፍጥነት መቆም አለበት።
የፌዴራል መንግሥት እና የሶማሌ ክልል መንግሥት በአሁ ሰዓት  በክልሉ  የተፈጠረውን ችግር  በተረጋጋ እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት በሚያረጋግጥ መልኩ ሊፈቱት ይገባል።
ይህ አካሄድ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓታችንን በመሸራረፍ እና አደጋ ላይ የሚጥል በመሁኑ   ውሎ ሳያድር እንዲታረም የትግራይ ክልል መንግሥት በጥብቅ ያሳስባል።
በዚህ አጋጠሚ በዚህ ግጭት በጠፋው የሰው ሕይወት እና በወደመው ንብረት መሪር ኃዘን የተሰማን መሆኑን እየገለፅን፣ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም ለመላው የሶማሌ ክልል  ፅናትን እንዲሰጣችሁ ለማለት እንወዳለን።
የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕዝብ ግንኙነት ቢሮ
ሐምሌ 28 ፣ 2010 ዓ.ም.
መቐለ!
መላኩ ቢረዳ
Filed in: Amharic