>
5:20 pm - Wednesday November 30, 2022

"ሕግ አስከባሪ" የተከዜ ማዶ ልጆች ?? "የትግራይ መኳንንት ልመዱት (ከመስከረም አበራ)  

“ሕግ አስከባሪ” የተከዜ ማዶ ልጆች ??
“የትግራይ መኳንንት ልመዱት
ከመስከረም አበራ
ሰው የሆነ ሁሉ አብዲ ኢሌ የሚባል ጨካኝ አረመኔ በመያዙ ደስ ሊለው ይገባል፨ ይህ ሰው ህዝብ ዘርፎ የሚያዘርፈው አንሶት በስሙ በሚነግድበት ህዝብ ላይ የአለምን መከራ የሚያወርድ ምኑም ለተቀመጠበት ወንበር የማይበቃ ሰው ነው፨
ከሌብነት ፣ ዘረፋ እና ጭካኔ ብቻ የተሰራ ሰው ከእሱ ብሶ ሃገር እገነጥላለሁ ሲል ዝም ተብሎ ካልታየ ማለት በአብዲ አሳቦ ለዘራፊው ህወሃት ማልቀስ ነው፨ ለአብዲ ጥብቅና የሚሞክራችሁ ሰዎች የልጃቸው ሞት ሃዘን በቀብሩ ለቅሶ  ያልወጣላቸውን ሰልስት እየፈለጉ እየፈለጉ የሚያለቅሱ እናቶችን ትመስሉኛላችሁ፨
ችግራችሁ ይገባናል ፤ዘረኝነት አለያም እሱን ተከትሎ የሚመጣው ጥቅመኝነት ነው ለአረመኔ ጠጥብቅና የሚያስቆማችሁ፨ ዘረኝነት እና ራስ ወዳድነት መንታ ናቸው፨ ባይሆንማ ኖሮ በአብዲ ኢሌ ለበቅ ሲገረፍ የኖረው የኢትዮ-ሶማሌ ህዝብ ድራጎኑ ገለል ተደርጎለት ተንፈስ ሲል ደስ ሊላችሁ ይገባ ነበር፨ ለመሆኑ ለአብዲ ጥብቅና የሚቆመው ከዘረፋ እና ጭካኔ በቀር ምን ያጎድላል ተብሎ ነው?
መለስ ዜናዊ ልዩሃይል የሚባለውን ፖሊስ በሶማሌ ክልል ሲተክል በህዝብ ላይ ሊያወርድ ያሰበውን መርገም የሚያስተናብር ትልቅ እኩይየመለስ የልብ ሰው ተደርጎ የታሰበ ሰይጣን ነው አብዲ ኢሌ፨ በዚህ ልዩ ሃይል በኩል በመለስ እና አብዲ ጥምር ክንድ  በዛ ክልል ህዝብ ላይ ያልወረደ መከራ የለም፨ ሴት ልጅ ረክሳለች ፣በቀን በብርሃን ከጎዳና ላይ አፈፍ ተደርጋ የጋጠ-ወጥ ወታደር መጫወቻ ሆናለች ፣ወንድ ልጅ መፈጠሩን እስኪጠላ በጄል ኦጋዴን መከራን ተቀብሏለል ፨
ከእለታት አንድ ቀን  የትግራይ ተወላጅ ሞተ ቀርቶ ትግረኛ ሲያወራ በጎኑ ያለፈ ሰው ሊገላምጠው ያሰበ መሰለን ብላችሁ እንደተልባ የምትንጫጩ ሰዎች የሶማሌ ህዝብ ሞት፣ ግርፋት እና ፈርጀ ብዙ አበሳ አይሰማችሁም፨ እንዲህ እንድታስቡ የሚያደርጋችሁ ምን ያለ አፈጣጠር እንደሆነ ሳስበው ይገርመኛልም፣ ያሳዝነኛልም፣ እውነት ለመናገር ይቀፈኛልም፨ሻሸመኔ መጥረጊያ የሚያዞር ሁለት ትግሬ ታሰረ ብላችሁ እንደ ብራቅ ስትጮሁ ነበር፨ በጄል ኦጋዴን የታጎረው ህዝብ ግን እንደ እናንተው ዘመዶች ዘጠኝ ወር ተረግዞ ከእናት መማህፀን የተገኘ ክቡር የሰው ፍጡር ስለመሆኑ አስባችሁ ታውቁ ይሆን ? እስር ቀርቶ ሞት ብርቅ ባለልሆነበት ሃገር የሁለት ትግረሬ መታሰር እንደ አዲስ እብድ ሲያስለፈልፋችሁ “ዘረኝነታችሁን ይማር!” ከማለት ወውጭ ምን ይባላል?????
ዛሬ በድንገት የህግ ሰዎች ሆናችሁ “ትዕግስትህ በዛ” እየተባለ የሚብጠለጠለውን የዶ/ር አብይን መንግስት በጉልበተኝነት የምትከሱ ሰዎች በእኩለ ሌሊት ወደ ሌላ ክልል ወታደር ልኮ የሰው ቤት ያመሰውን አባይ ወልዱን ምንም ሳትሉ አልሞት ባይ ተጋዳዩን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ነፍሰ ገዳይ ስትሉ የነበራችሁ ሰዎች ናችሁ፨
ህወሃት ከየመን ሁቲ ወሮበሎች ጋር ተመሳጥሮ በማያስተዳድረው ግዛት ላይ መንገደኛ ከአውሮፕላን አውርዶ አምጥቶ ያልታወቀ ቦታ ሲያስቀምጥ የሰፈራችሁን ሰዎች  የጀግንነት ልታደንቁ ከበሮ ያነሳችሁ ፍጡራን ናችሁ ፨ ከአንድ ቤት ሶስት ጎረምሳ ተገድሎ ሬሳቸው እንደ ከሰል በጆንያ ታስሮ ታስሮ የእናት በር ላይ ሲደረደር ትንፍሽ አላላችሁም፨
 በምርጫ ማግስት በዋና ከተማ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ቅልጥ ያለ ጦርነት ሲታወጅ መለስ ስላደረገው ብቻ ልክ ይመስላችሁ ነበር፨
ጊዜ እና ሁኔታ እየመረጡ የህግ ሰው መሆን አይቻልም፨ በሰው አመካኝቶ ከማልቀስ የራስን ለቅሶ በግልፅ ማልቀሱ ይሻላል፨ ወንጀለኛ ሁሉ ይታደናል ፣ ከህዝብ ጋር የቆመ ብቻ ያሸንፋል ፨ ዶ/ር አብይ ከህዝብ ጎን የቆመ ዕለት አሸንፏል ፤ልመዱት ! “
Filed in: Amharic