>
7:31 pm - Monday May 16, 2022

የአዲስ አበባ ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የለውም!!! አቶ አዲሱ አረጋ

የአዲስ አበባ ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የለውም!!! አቶ አዲሱ አረጋ

ቃሊቲ ፕሬስ

(ከዚህ በታች ያለው አቶ አዲሱ አረጋ የኦህዴድ ቃል አቀባይበቁቤ የጻፉት የመጀመሪያው ክፍል ተተርጉሞ ነው። ከዘጠናበመቶ በላይ የአዲስ አበባ ዝብ አፋን ኦሮሞ የማይናገርእንደሆነ እየታወቀ፣ አዲስ አበባን በተመለከተ አቶ አዲሱበአማርኛም ሁፋቸውን አለማቅረባቸው፣ ምን አልባትየአዲስ አበ ህዝብ እንዳያውቀው ከመፈለግም ሊሆንይችላል። ሆኖም  ምን ጊዜም እዉነት፣ ግለጽነት ለሁሉምገር ይበጃልና ጦማሪያን ጽሁፉን ተርጉመውእንደሚከተለው አቅርበዉልናል)

ፊንፊኔ የኦሮሞ ምድር ነች፣ የኦሮሞ እምብርትና የሜጫ ቱለማ ማዕከል ነች፣ የነ ቱፋ ሙና የቀጀላ ዶዮ የአቤቤ ቱፋ ጉደታ አራዶ ጀሞ ደበሌ ሶራ ሎሜ ገለታ አሸቴ አጣሌ ጃተኒ እና የነ ሹቡ እጄርሳ ቀዬ ነች።ፊንፊኔ የዐፄ ምኒልክ መቀመጫ ሆና ማገልገል ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የኦሮሞ ገበሬዎችን እየበላች፣ እየነቀለች፣ የኦሮሞን ባህልና ማንነት እየናደች አሁን የደረሰችበት ደረጃ ላይ መድረሷ የሚታወቅ ነዉ። ከደርግ መዉደቅ በኋላም የሽግግር መንግሥቱ ቻርተር ከ1983-1987 በጸደቀዉ መሰረት ፊንፊኔ ራስ ገዝ ሆና ክልል 14 ተብላ ራስዋን እንድታስተዳድር ታዉጆ ነበር። ለአራት ዓመት ያህል ክልል ሆና ትተዳደር ነበር። ፊንፊኔ ራስዋን የቻለች ክልል ሁና ራስዋን በምታስተዳድርበት ወቅትም በ 1986 የድንበር አዋጅ ብላ ሕግ ደነገገች፤ በዚህ ባወጣችዉ ሕግ መሰረትም እስከ ቡራዩ ለገጣፎ ለገዳዲ ሰበታ ገላን እና የመሳሰሉትን ጠቅልላ ለመስፋፋት የኦሮሞን ህዝብና የኦሮሚያን መንግሥት ሳታማክር ህግ ደነገገች።

በ1987 የኢፌድሪ (FDRE) መንግሥት ስርዓት ተደነገገ። የሀገራችን መንግሥት አዋጅ የሆነዉ ይህ አዋጅ ስለ ፊንፊኔ ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች እንዲቀየሩ በግልጽ አረጋገጠ። የመጀመሪያዉ ፊንፊኔ ራስዋን የቻለች ክልል መሆንዋ ቀርቶ በከተማ አስተዳደር እንድትዋቀር ወሰነ፤ ሁለተኛዉ በአንድ ወቅት ተቋርጦ የነገረዉን የኦሮሞንና የፊንፊኔን ግንኙነት መልሶ አስተሳሰረዉ። በሽግግር ወቅት ፊንፊኔና ኦሮሚያ የክልል ለክልል ግንኙነት ነዉ የነበራቸዉ። ይህ ሕግ ከጸደቀ በኋላ ግን ፊንፊኔ የኦሮሚያ አካል እንደሆነችና ኦሮሚያም ከፊንፊኔ ልዩ ጥቅም እንዳላት በግልጽ ተነሳ። ሶስተኛዉ ፊንፊኔ የፌደራል መንግሥት መቀመጫ በመሆንዋና በዉስጥዋ የሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦችን መብት ለመጠበቅ ሲባል እንደ ክልል የራስን እድል በራስ የመወሰን የሚል ሳይሆን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ብቻ ተወስኗል። የኢፌድሪ ሕገ መንግሥት በኦሮሞና በፊንፊነን መሀከል ተቋርጦ የነበረዉን የረዝም ዘመናት ልዩነት ቀይሮ ፊንፊኔ የኦሮሞ አካል እንድትሆን ወስኗል። ፊንፊኔ የኦሮሞ መሆንዋን አረጋግጧል።

በ1987 የወጣዉ አዋጅ ፊንፊኔ ራስን በራስ የማስተዳደር እንጂ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት እንደሌላት፣ የፊንፊኔ ከተማ ጉዳይ በአዋጅ የሚወሰን መሆኑን በመግለጽ ቀድሞ የነበሩ ህጎችን( በ1986 የወጣዉን የከተማዋን ድንበር የሚደነግገዉን ህግ ጨምር) ሽሮታል።ስለሆነም በፊንፊኔ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞኖች መሀከል የሚገኘዉ የድንበር ጉዳይ የሚወሰነዉ ድንበር አከባቢ ባለዉ ኦሮሞ በኦሮሚያ መንግስትና በአዲስ አበባ መስተዳደር መልካም ፍቃድ ብቻ መሆኑ በግልጽ መታወቅ ይኖርበታል። በመሆኑም በ1986 የተደነገገዉ ፊንፊኔን የማስፋፋት አዋጅ የኦሮሞን ሕዝብና የኦሮሚያ መንግሥትን ያላማከረ በመሆኑ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለዉም።

የፊንፊኔና የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የድንበር ጉዳይ በአንድ ክልል አስተዳደር ዉስጥ የሚደረግ ዉይይት መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። የፊንፊኔ የድንበር ጉዳይ በ1987 የወጣዉን የሀገራችንን አዋጅ መሰረት ባደረገ መልኩ የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎትና ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ ብቻ መተግበር ይኖርበታል። የፊንፊኔን የድንበር ጉዳይ በጥንቃቄ ለመፍታት 10 ሰዉ ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ ጥናት ያቀረበ ሲሆን የኦሮሚያ መንግስት የጥናቱን ዉጤት ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ወደ ስራ ለመተግበር እየተንቀሳቀሰ ነዉ።

Filed in: Amharic