>

ትግራይ እንደ ክሬሚያ ! ? ! (ዳንኤል ገዛህኝ)

ትግራይ እንደ ክሬሚያ ! ? !
ዳንኤል ገዛህኝ
* አንደኛው ትግራይ-ትግርኝ/ዘ-አግአዝያን። ሁለተኛው ደግሞ የትግራይ የብቻ ሀገርነት ሲታሰብ ያለ ወልቃይት ምንም ነው እና እሳቤው ከኤርትራ ጋር በኮንፈደሬሽን መስማማት ካልተቻለ ፕላን B ዘጠኝ ብሄሮችን ያካተተ ሀገር መመስረት። ትግርኝ-ትግራይ
 
በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ከሚገኙት 50 ስቴቶች ውስጥ በአሳ ሀብት የምትታወቀው አላስካ ከረጅም አመታት በፊት የራሽያ ግዛት ነበረች። በዚች ስቴት የራሽያ እንዲሁም ዋናዎቹ ተወላጅ አሜሪካውያን Native Americans ወይንም Indian American /Red Indians/ በግዛቱ በብዛት ይኖራሉ። ይሁን እና እነዚህ ዜጎች የአኑዋኑዋራቸው ሁኔታ በስፋት እንደሚታወቀው የየ ስቴቶችም ህጋዊ እውቅናና ድጋፍ እንደሚያሳየው ህይወታቸው እርዳታ ላይ የተመሰረተ ነው። ታድያ ከሶስት አመታት ቀደም ብሎ የነዚህን የኢኮኖሚ አቅማቸው በመንግስት እርዳታ ላይ የተመሰረተ ዜጎችን ደካማ ጎን በማየት ራሽያዎች ሀገሪቱ ቀደም ሲል ከዘመናት በፊት ወደነበሩበት እንዲመለሱ የሀገሪቱ ህግ እንደሚፈቅደው አስር ሺህ የሚደርሱ ነዋሪዎች ፊርማ በማሰባሰብ ሪፈረንደም እንዲካሄድላቸው በኬጂቢ እንቅስቃሴ ተጀምሮ በራሸያ ስፓንሰር አድራጊነት የተጋጋለ ስራ ተጀምሮ ነበር። ሆኖም ከተያያዥ የፓለቲካ እና ውስብስብ የስቴትዋ ችግሮች ጋር ተዳምሮ ጉዳዩ እንደታሰበው ሳይሳካ ቀረ። ዜጎቹ ምንም እንኩዋን ሪፈረንደም ማካሄድ ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ቢሆንም ቅሉ ግን ሳይቻላቸው ቀርቶዋል። ዲሞክራሲ “ትሰማዋለህ ግን አትዳሰሰውም …ታደምጠዋለህ ግን አታየውም ” እንዲሉ ነገር።
      በኢትዮጵያ የሀገሪቱ “ህገ-መንግስት” አንቀጽ 39 “የብሄር ብሄረሰቦች መብት የራስን እድል መወሰን እስከመገንጠል” የሚል መብት የሚመስል ግን መርዘኛ አንቀጽ ከኤርትራ ነጻነት በሁዋላ ሀያ ስድስት አመታትን አስቆጥሮ ዛሬ አንቀጹ ለተፈለገው አላማ ለማዋል ጥረት ተጀምሮዋል።
      ክሬሚያ የ ዩክሬን አካል ነበረች ይሁን እና ከፈረንጆቹ 2004 ጀምሮ ራሽያ በጀመረችው የተስፋፊነት እንቅስቃሴ ባለፈው ዓመት ክሬምያ ከነዋና መናገሻዋ ሴቫስቶፓል በራሽያ ፌድሬሽን ስር መውደቅዋ ከቀናት ጦርነት በሁዋላ እውን ሆኖዋል። የአቅም ጉዳይ ቢያነጋግርም ወደ እናት ሀገርዋ እንደምትመለስ ዩክሬን ትዝታለች የተካሄደው ምርጫ የይስሙላ እንደሆነ አለም ይስማማል።
ወድ እኛዋ ትግራይ ስንመጣ የትግራይ ህዝብ ምን እያሰበ እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም። ተሸናፊዎቹ ፓለቲከኛዎች ህዝቡን ከእናት ሀገሩ ከኢትዮጵያ ብቻ አይደለም ከሚዲያ ነጥለውታል።
ለዚህ ደግሞ የሀገሬው ተወላጅ ነን የሚሉ አክቲቪስቶች ትልቁን አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።
ምንም እንኩዋን በመገንጠል ጉዳይ ላይ የትግራይ ፓለቲከኛዎች እና ልሂቃን ህዝቡን ባያወያዩትም፤ ፍቃዱን ባይጠይቁትም ባለፈው አስራ አምስት ቀን የክልሉ ፕ/ት “ዶ/ር ደብረጽዮን መገንጠልን የሚያመላክት ቃል በሚድያ ሰጥተዋል።
እርግጥ ነው ትግራይ ልገንጠል ካለች በህዝበ-ውሳኔ 51 ከ 100 መብትዋ ነው። እናም ትግራይ ብሄራዊ ባንዲራ…ብሄራዊ መዝሙር ሀገር ሆና የመጠራት መብት ይኖራታል።
ትግራይ ተፈጥሮአዊ አቀማመጥዋ ተደምሮ አስተማማኝ የተፈጥሮ ሀብት የላትም። ሀብት ኖሮዋቸው ጋዝ እያወጡ ሀገር ሆነው መቀጠል ያልቻሉትን እነ ደቡብ ሱዳንን ልብ ይሉዋል።
በእርግጥ ከዚህ ስትራቴጅ ጀርባ ሙዋቹ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ የህዳሴውን ግድብ ታሪካዊ እቅድ፣ ንድፍ እና ፕላን ከንጉሰ ነገስት ግርማዊ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ በመውሰድ ግድቡ ከሱዳን ሀያ ኪሎ.ሜ. ርቀት ላይ በማስጀመር የወደፊትዋ ትግራይ ተካላይ መሬት ውስጥ በማድረግ አዲሱን የትግራይን ካርታ እንዳየነው ለትግራይ የማታ የማታ አባይን የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ለማድረግ የታለመ ግብ ነበር። ምንም እንኩዋን በጊዜው እንደሰደድ እየተዛመተ የነበረውን ህዝባዊ አመጽ አቅጣጫ ለማስቀየር እግረ መንገድ ቢያገለግልም ግን አባይ ለትግራይ እንደታሰበው ላይሆን እዚህ ደርሶዋል።ቢሆንም ግን ሙዋቹን ጠ/ሚ/ር አስደንግጦዋቸው ፍርሀት ውስጥ በጊዜው የከተታቸው Arab Spring እንደሰደድ እየገሰገሰ ከነበረበት ጉዞ የአባይ ህዳሴው ግድብ ጠበል ሆኖ ሰደዱን ለማጥፋትበኢህአዴግ ላይ የመጣውን በላ በረድ አድርጎላቸዋል።
የትግራይ ህዝብ ምን እያሰበ ነው በፓለቲከኞች ተጠልፎ ሊገነጠል ? ሊሆን የማይችል ጉዳይ ነው። ለዚሁ ህልም ትግራይ የሱዳንን ከረንሲ ለመጠቀም ህውሀት Curency Swamp ጀምሮ ነበር በዶላር ሳይሆን ከራስዋ ከሱዳን በሱዳን ገንዘብ መገበያየት።
ወደ ዋናው ነጥብ ስንመጣ ክሬምያ ያለውድ በግድ የራሽያ አካል ሆናለች የምትተዳደረው በኮንፌድሬሽን ስርአት ነው በዚህ የተነሳ በርካታ የዩክሬን ዜጎች ተሰደዋል እምቢተኝነት አሳይተዋል ሞተዋል የደረሱበት ጠፍቶዋል ዜጎች በጉዳዩ አዝነዋል። የትግራይ እናቶች እና።አዛውንቶች እየተጎሰመ ባለው የእንገነጠላለን ፕሮፓጋንዳ በእጅጉ እያዘኑ ነው። ነገሩ ቁርጥ ከሆነ የትግራይን ህዝብ መሸሸግያ አድርገው የመሸጉትን ወንጀለኛዎች ለመንግስት በማስረከብ የትግራይ ህዝብ ታሪክ ሊሰራ ይችላል የሚል አንድምታ ውስጥ ውስጡን እየተነገረ ነው እንጅማ ትግራይ እንደክሬምያ በጥቂት አምባገነኖች ልትወሰድ የማይሆን ጉዳይ ነው። በመሰረቱ ጉዳዩ ሳይታጠቁ ሆነ እንጅ ትግራይ ሁለት ፕላን ነበራት።
አንደኛው ትግራይ-ትግርኝ/ዘ-አግአዝያን። ሁለተኛው ደግሞ የትግራይ የብቻ ሀገርነት ሲታሰብ ያለ ወልቃይት ምንም ነው እና እሳቤው ከኤርትራ ጋር በኮንፈደሬሽን መስማማት ካልተቻለ ፕላን B ዘጠኝ ብሄሮችን ያካተተ ሀገር መመስረት።
ትግርኝ-ትግሬ
ራያ
ኢሮብ
ኩናማ
አፋር
ወልቃይት
ቅማንት
ቤንሻንጉል
ጋምቤላ
እነዚህን ብሄሮች ወደትግራይ ለማካለል ካርታው ተሰርቶ ለሙከራ ግን በስህተት አስመስሎ በኢቲቪ እንዲታይ ተደርጎዋል። ቅማንት በማንነት ከተቀረው አማራ/ጎንደር ጋር እንዲቃቃር ስራ ተሰርቶዋል፤ በወልቃይት አካባቢ ከኢህአዴግ/ህውሀት ተቀናሽ ታጋዮች መሬት እየታደላቸው ከመቁዋቁዋሚያ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በአርባሽዎች በስፍራው ሰፍረው ቤተሰብ እንዲመሰርቱ እንዱስፋፉ የኢኮኖሚ እና የአስተዳደር ስልጣን የበላይነት እንዲኖራቸው ተደርጎዋል፤ በቤንሻንጎል አማራዎች ቁጥራቸው እንዲመናመን በጅምላ ግድያ ከሀያ አመታት በላይ ከኖሩበት ከቀያቸው ከንብረታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርገዋ፤ ይህ ከመከወኑ በፊት በክልሉ ህገ-መንግስት መጤ የተባሉ የሌላ ብሄር ተወላጆች የመኖር ዋስትና እንዳይኖራቸው ቀደም ተብሎ ትልቅ ሻጥር ተፈጽሞዋል ፤ በጋምቤላ በኑዌሮች እና በአኝዋኮች መካከል የጎሳ ግጭት ከማቀጣጠል እስከ አኝዋኮች ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል የዘር ፍጅት በግልጽ ቁዋንቁዋ የዘር ማጥራት Ethnic Cleansing ተካሂዶዋል፤ ይኽውም ኑዌሮችን በማቀፍ በመደገፍ አኝዋኮች ላይ እልቂት እና ስደት በማወጅ እስካሁን ድርጊቱ ቀጥሎ ፤ በአሶሳ፣አበቦ፣ ዲማ አካባቢ በደቡብ ሱዳን የረጅም አመት ቀውስ ሳቢያ ጦርነት እና እልቂት ምክንያት በተባበሩት መንግስታት የስደተኛዎች መርጃ ቢሮ እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስት በጎ ፈቃደኝነት ከዘጠኝ መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ኑዌር የደቡብ ሱዳን ዜጎችን በመጠቀም ትልቅ የሪፈረንደም ድምጽ ይሆኑ ዘንድ ሻጥር ተሰርቶዋል። ምንም እንኩዋን እነዚህ ኑዌሮች የደቡብ ሱዳን ዜጎች ቢሆኑም ለትግራይ ድጋፍ ሰጭ ዜጋ እንዲሆኑ የተደረገበትን ሂደት እነሱም እንዳይቃወሙት እድርጎዋቸዋል።
በ1951 የጄኔቫ ኮንቬንሽን እንዲሁም በተሻሻለው የ1967 ፕሮቶኮል እና ስምምነት መሰረት UNHCR. የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኛዎች መርጃ ኮምሽን ከተቁዋቁዋማበት አላማዎች አንዱ ከሀገራቸው በልዩልዩ ምክንያት በስምምነቱ ፈራሚ ሀገር ተጠልለው ለሚገኙ ስደተኛዎች ዘላቂ መፍትሄ Durable Solution መስጠት ነው።
መፍትሄዎቹም በአርቲክል 11(2) እንደተቀመጠው ኑዌሮችን የትግራይ ክልል ቁጥር ማሙዋያ እንዲሆኑ ታስቦ ተደርጎዋል። ስደተኛ ሶስት የመፍትሄ ማግኛ መብት አለው።
1 .ወደ ሶስተኛ ሀገር መማር መስራት እንዲችል የዳግም ሰፈራ መብት ወይንም Resettlment.ይህ መብት ኑዌሮቹ ሆን ተብሎ እንዳያገኙ በዚህ መብት እንዳይዳኙ ተደርጎዋል።
2. በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ ወይንም Voluntery Repatreton. ይህ ደግሞ መሆን የሚችለው አሁን ነው። በተለያዩ የአፍሪካ የስደት ጣቢያ ሁለተኛ ሀገር የሚገኙ ደቡብ ሱዳናውያን የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር ዶክተር አብይ አህመድ የጀመሩት የሀገሪቱን መሪ እና ተቃዋሚ የማሸማገል ሰራ ፍሬ አፍርቶ በካርቱም አስማሚነት ስደተኛዎቹ በቅርብ ወደሀገራቸው ሊመለሱ ነው። የኢትዮጵያዎቹን በተመለከተ የተባለ ነገር እስካሁን የለም ።
3.ስደተኛዎች ካሉበት ሀገር መንግስት ዜጎች ጋር ተመሳስለው የሀገሪቱ መታወቂያ ተሰጥቶዋቸው በዘላቂነት አብረው ተቀላቅለው መኖር Local Integration. እንግዲህ በዚህ በሶስተኛው ነጥብ ነው ዘጠኝ መቶ ሺህ ኑዌር ደቡብ ሱዳናውያን ሌሎች ትግራዋይ እንዲሆኑ የታጬት።
እነ አፋር ላይ ለረጅም ጊዜ የትግራይ የበላይነት እና ተስፋፊነት ሲሰራ ቆይቶዋል ምንም ለውጥ ባይታይበትም።
ለማንኛውም ትግራይ መንግስት እና አዲስ ሀገር ሆና ለመውጣት የጀርባ ታሪክዋ ሲታይ በቂ አይመስልም። የአፍሪካ አንድ አዲስ ሀገር ለመሆንም ያለችበት የነበረችበት Geo-Political ዳራ ሲታይ የማይሆን መሆኑ ይከሰታል። ምን አልባት የመገንጠል ህልምዋ ቢሳካ ራስዋን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ባይሆንላት የሰሜን ሱዳን የካርቱም ኮንፌደሬሽን አስተዳደር ልትሆን ይሆን ? ምክንያቱም ከኢኮኖሚውም ከታሪካዊ ብቃትም “ትንሽ ቆሎ ይዘህ ወደ አሻሮ ተጠጋ…”  አልሰመረም። እንኩዋን አንድ ለመሆን የትግራይ “በጉዳዬ ተሳታፊ ሁኑልኝ…” በማለት ኤርትራን የመጋበዝ እከክልኝ ልከክልህ ሙከራ ከወደ ኤርትራ በተሰደደው ምላሽ “የኤርትራ መንግስት ቀጥተኛ ግንኙነት ከፌደራሉ መንግስት ጋር እንጅ…ከትግራይ ጋር ባለ መርህ አልባ ግንኙነት አይደለም” የሚል ሆኖዋል። አውቆም ቆምጦዋል ይሉዋል። ቸር ያሰማን።
Filed in: Amharic