>

ዓረና መድረክ መገንጠል፣ መነጠል፣ መበታተን ኣይደግፍም ! (አምዶም ገ/ሥላሴ)

ዓረና መድረክ መገንጠል፣ መነጠል፣ መበታተን ኣይደግፍም !
አምዶም ገ/ሥላሴ
አረና ማንኛውም ሰው ትግራዋይ፣ ኣማራ፣ ኦሮሞ ወዘተ በመሆኑ ብቻ ከተጣያቂነት ነፃ እንዲሆንም ሆነ ተለይቶ እንዲ ወነጀል ኣንፈቅድም።
ዓንቀፅ 39 ከህገ መንግስት እንድትወገድ ይታገላል። ጥረቱ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትኖረን እንጂ ኣንድ ያኮረፈ ቡድን እንገንጠን ብሎ የሚበትናት ሃገር እንድትኖረን ኣይደለም።
ዓረና ለህግ ልዕልና ይታገላል።  ማንኛውም ዜጋ ህግ ጥሶ(ወንጀል ሰርቶ) ሲገኝ ጉዳዩ በገለልተኛ ፍርድ ቤት እንዲታይና ያለ ውጫዊ ተፅዕኖ ፍርዱ እንዲያገኝ ይታገላል።
  ዓረና እነ ስብሓት ነጋ፣ ኣባዱላ ገመዳ፣ ኣዲሱ ለገሰና ካሱ ኢላላ የመሳሰሉት ነባር መሪዎችም ከህግ በላይ እንዲሆኑ ኣይፈልግም።   ጥፋት ሲገኝባቸው ህግ ፊት ቀርበው እንዲፈረዱ ያደርጋል። ጥፋት ከሌላቸው ደግሞ መብታቸው እንዲከበር ጥረት ያደርጋል።
   እንጂ ማንኛውም ሰው ትግራዋይ፣ ኣማራ፣ ኦሮሞ ወዘተ በመሆኑ ብቻ ከተጣያቂነት ነፃ እንዲሆንም ሆነ ተለይቶ እንዲ ወነጀል ኣይፈቅድም።
ማንኛውም የዓረና ኣባል ስለ መገንጠል ከፃፈ ወይም ካወራ የግሉ መሆኑ ይታወቅ። ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል ያተረፈችው ቁምነገር ምን ኣለ? ያስቀረችው ጦርነትስ የታለ?
ደቡብ ሱዳንና ሱዳን ተበታትነው ያገኙት ጥቅም የታለ?
ዓረና፣ ኦፌኮ፣ ሲኣንና ኢሦዴፓ የመሰረቱት መድረክ መገንጠል ይቃወማል። በኢፌድሪ ህገ መንግስት ያለው ዓንቀፅ 39 ህገ መንግስታዊ መርህ ተከትሎ እንዲወጣ ይታገላል።
የምንታገለው ለህግ ልዕልና ነው ! ትግራይ ኣትሸሽም !
Filed in: Amharic