>
5:13 pm - Friday April 19, 9686

የታላቁ ህዳሴ ግድብ በጣልያኑ ሳሊን ኩባንያ ከ350 ሚለየን ዩሮ በላይ ካሳ ተጠየቀበት (ደረጄ ገረፋ ቱሉ)

የታላቁ ህዳሴ ግድብ በጣልያኑ ሳሊን ኩባንያ ከ350 ሚለየን  ዩሮ በላይ  ካሳ ተጠየቀበት
ደረጄ ገረፋ ቱሉ
 
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሜካንካል ስራውን ሜቴክ በጊዜ እና በትክክል ሰርቶ ማስረከብ ስላልቻል ሳሊን ሌሎች ስራዎችን መቀጠል አልቻለም።በዚህም ምክንያት ሳሊን ኩባንያ የኢትዮጵያን መንግስት ከ350 ሚለየን  ዩሮ በላይ  ካሳ እንደጠየቀ ለፕሮጀክቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልፀውልኛል።
ግድቡ በጠቅላላው ስራ ይጀምራል በተበለበት ጊዜ ላይ በሜካንካል (ሜቴክ የያዘው ክፍል) ስራው ችግር ምክንያት 16ቱም ታርባይኖች መስራት አለመቻላቸው በጣም አስደንጋጭ እንደሆነ ምንጮቼ አክለው ገልፀውልኛል።

በአገራችን ውስጥ በህዝብ ዘንድ ቁጣ እየፈጠሩ ያሉ የግፍ ዘረኛ አገዳደሎች ዜና ትኩረት ማስቀየሻ ዜናም የሚመስል ነገር ቢኖረውም ሀሳቡ…ካልሆነ ግን ግብጾች  ለጊዜውም ቢሆን እፎይታ ያገኛሉ ።እኔ ተራ የስሚንቶ ክምር በሆነ የአገሬ ሀብት አንጀቴ ይቃጠላል ።ግን ማነው የግብጽን ምኞት አሳክቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ህልምን እያጨለመ ያለው?…ሜቴክ (እነ ጀነራል ክንፈ ዳኘው) ?..ራሱ ሳሊኒ ( ሆሲን ሙባረክ  ሳሊኒ አባይ ላይ የጀመራቸውን የግድብ ግንባታ እንዲያቆም በወቅቱ የጣሊያን መሪ ከነበሩት በርሌስኮኒ ጋር ሲደራደሩ እንደነበረ  አይዘነጋም…እናም በቂ ገንዘብ ካገኘ ሰበብ ፈልጎ ሊያቆም አስቦ)ወይንስ የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ ውስጥ ባሉ ፖለቲከኞች  ሽኩቻ?….ብቻ ያንገበግባል!..የኢንጅነር ስመኘው ሞት ብዙ የተወሳሰቡ ነገሮችን ያሳያል ።የህዳሴው ግድብ አብዮት የሚያስነሳ አደገኛ የፖለቲካ ጨዋታ ነው! …ወይኔ!…እኔማ ያን ግንባታ ባላየሁ ነው ያልኩት! ህልም ሆኖ አይቀራትም!

Filed in: Amharic