>
5:13 pm - Friday April 20, 0621

ቀይ  መስመር   ማለፍ  ዋጋ  ያስከፍላል!! (የሰሜኑ ቋያ)

ቀይ  መስመር   ማለፍ  ዋጋ  ያስከፍላል!!
የሰሜኑ ቋያ
እኛ  ትግራዯች  ድሮም በጠመንጃችን ነው  የተከበርነው  አሁንም  በግራም  በቀኝም  በሻዕቢያና  በአማራ ተከበን  ሊውጡን ነው  ስለዚህ  ታጥቀን እንጠብቅ!!
ህወሃት- እነ ተወልደን ( ሃደ ዓይኑ)  እነ ገብሩ አስራት እነ አለምስገድና  ሌሎቹንም አመራሮቿን  በውስጥ የስልጣን   ሽኩቻ  ምክንያት  ካስናበተች በኃላ  ጥርሷን አራግፋ  በአንድ  ጥርስ  ብቻ  ስትናከስ  መቆየቷ  ግልፅ  ነው  ያች ያላትን  አንድ  ጥርስም የዛሬ 6 ዓመት አካባቢ  በተፈጥሮ ምክንያት  ወልቆ  ወደቀ   አሁን  ምን ቀራት  ??  “ድድ ” ብቻ እውነታው  ይህ ነው::
ነገር ግን  ይህ ግምገማ  በራሱ  ስህተት  መሆኑ  የገባን  በቅርቡ  ነው ማለትም  ድድ  አልባ  መሆኗን  ያወቅነው  ቅርብ  ጊዜ  ነው ህወሃት  ምን ጊዜም እራሷን  ችላ  የማትቆም  የልጅነት ልምሻ  ያጠቃት ብቻ  ሳትሆን  ማስብ ያቃታት  ድኩማን  ድርጅት  ነች  ስንል  ብዙ  ማስረጃዎችን  በማቅረብ ነው።
  ህወሃት  በእርሷ  ልክ ስው  የሚያስብ አይመስላትም ነገር ግን  ህዝቡና  ህወሃት  ልዩነታቸው  ህዝቡ  አቦ ሽማኔ  ህወሃት  ኤሊ  መሆናቸውን  አይደለም  ዛሬ  መቶ  አመት  ቢጨመራቸውም  አይገባቸውም
  ህወሃት  የምትስራቸውን  ተንኮሎች  እንኳን  በአግባቡ  ማስኬድ  አቅቷት  ሁሉም  ነገር  የህፃናት  ጫወታ  መምስሉን  ስናይ  ከላይ  የምንላቸውን  ሃሳቦች  ያጠናክራል
ለምሳሌ
1- ህወሃት – በአማራ ክልል  የእርስ በእርስ  ግጭት  እንድከስት አበክራ  እንደምትስራ  እንኳን የብአዴን  አመራር  ድፍን  የአማራ  ህዝብ  ጠንቅቆ ያውቃል
    – የአማራና  የቅማንትን ልዩነት  ከሀ  እስከ  ፐ   ምን ምን እንደስሩ  ይታወቃል
  ከስው ሃይል  ምልመላ  እስከ በጀት  ምደባ  ከዛም በማህበራዊ  ሚድያ  ሽፋን መስጠትና  ነገሮችን  በማቀጣጠል  እልቂት  እንድከስት  ማድረግ  ይህም  የተወስነው  ተሳክቶላቸዋል
 ይህንን አካሄድ  ብአዴን  ተው  እጃችሁን  አንሱ  ሲል  የለንበትም  እያሉ  ሲክዱ  ቆዩ  አሁን ስሞኑን  የቅማንት  ኮሚቴ  ነኝ ባዩና  የህወሃት  ጉዳይ  አስፈፃሚው  ሃይል  ጭልጋ  ውስጥ  ነጋዴ  ባህር  ላይ  የህወሃትን  ባንድራ  አምጥቶ  ስቀለ   ህዝቡም  ለምንድነው  ብሎ  ሲጠይቅ  የተስጡት  መልስ  ለዚህ እንድንበቃ  ህወሃት  ብዙ ወጭና  ድካም ደክማለች  ደግሞም  ከህወሃት  ጋር በነበረን ስምምነት  መስረት  ነው  አሉ:; የተወስነ  ግጭት  ተነሳ   ነገር ግን  ለሁሉም  ቀይ መስመር  አለውና  ለኮሚቴው  ግልፅ  መልዕክት  ተነግሮታል  ከአሁን  በኃላ  እንኳን  ይህች  ባዶዋ  ህወሃት  ቀርቶ  ማንም  እንደማያድነው   እነርሱም  ገብቷቸዋል   ካልገባቸው  ደግሞ  ቋንቋ  መቀየር  ነው   ምክንያቱም  ይሄ ለአማራ   ቀይ  መስመር  ነው::
2- ህወሃት – አማራ  ክልል በተስገስጉ  ተላላኪዎቿ አማካኝነት  በክልሉ  ምን ያህል ስው  የታጠቀ  አለ ብላ  አጥንታለች  ከዛ  ልክ  በአማራ ክልል ያለውን  ሃይል  ያህል  ቁጥር ለመሙላት  ከምልስ ታጋዯች  እስከ  ግብርና  ጣቢያ  ስራተኞች  ድርስ   የተዋቀሩበት  ሃይል  በክልሉ በሁሉም ቀበሌዎች  ስው  ተመልምሎ  ስልጠና  እየወስደ  ነው   ስልጣኞችም  ምንድነው  ብለው  ሲጠይቁ  እኛ  ትግራዯች  ድሮም በጠመንጃችን ነው  የተከበርነው  አሁንም  በግራም  በቀኝም  በሻዕቢያና  በአማራ ተከበን  ሊውጡን ነው  ስለዚህ  ታጥቀን እንጠብቅ  የሚል መልስ ነው  የሚስጡት
  እዚህ ላይ  የሚገርመው  ስልጣኞች  ሲመረቁ  ቃል  የሚገቡት  የተነገረንን ሚስጥር  ለማንም አንናገርም የሚል  ቃል  ያስገባሉ   ህወሃት  ህግ  አታውቅ  ሲነግሯት  አትስማም  እንጅ የአንድ አገር የትጥቅ ስታንዳርድ  የሚባል አለ  አማራ  የህዝብ ብዛቱና  የትግራይ  ህዝብ  ብዛት  ለሚኖርህ  የከባቢ ታጣቂ  ብዛት  አስተዋፅኦ  መኖሩን  አይገባትም  ይግባታል ተብሎም አይጠብቅም
3- የኢትዯ-ሶማሌን  ልዩ ሃይል  እነ ኳርተር እንድሁም አብዲ  እንደ  ግል ዘበኛ  ነው የሚያዙት  ይህንን  ሃይል አንድ መፍትሄ ይደረግ  ሲባል  ሽንጣቸውን  ገትረው  ሲከራከሩና  እንዳውም  አፋርም  ያስፈልገዋል  ሲሉ  ሲከለከሉ  ቆዩ መጨረሻ  ላይ  የዚህ ልዩ  ሃይል ገመና  በግልፅ ሲታይና  አደባባይ  ሲወጣ  ወደ  እርምጃ  ሊገባ ሲል  ለማለቃቀስ  ማንም አልቀደማቸውም
 – እንዳው  በአጠቃላይ   ህወሃት  እያረጠች  እንደሆነ  በፊትም  ምልክቶቹን  እያዬን ብንገምትም  ልክ እንደዚህ ከእርጥና  ወደ ህፃንነት  ታመራለች  ብለን ግን ገምተንም  አናውቅም::    ለማንኛውም  ይህችን  እርጥ  ከአሁን በኃላ  ተሽክሞ  መሄድ መሮናል  ስልችቶናልም ከአሁን በኃላ  የውክልና  ብጥብጥ በክልላችን  ውስጥ  ለማስነሳት  ማስብ በራሱ  በእሳት መጫወት መሆኑን  ልታውቀው  ይገባል  ለነገሩ  የማትስማ  የማትማር እንደሆነች ብናውቅም  ተላላኪዎቿ  ግን  ሁለት  ሶስት  ጊዜ  ልታስቡበት  ይገባል::      ቀይ  መስመር   ማለፍ  ዋጋ  ያስከፍላል!!
Filed in: Amharic