>
2:48 am - Friday February 3, 2023

"እስከ መጨረሻው እየገደሉ እየሰረቁ መቆየት ነበር ፍላጎታቸው"  የቀ/ጠ/ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ

እስከ መጨረሻው እየገደሉ እየሰረቁ መቆየት ነበር ፍላጎታቸው” 
የቀ/ጠ/ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ
ኤርሚያስ ዳውድ እንድሪስ
ይህችን ሀገር አንድ ሰው አስነስቶ ከመፍረስ እንዲያድናት ስፀልይ ነበር
 
• የሚሰሩት ስራዎች ሁሉ የማፊያ ነበሩ 
 
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለዴይሊ ማቭሪክ የወሬ ምንጭ በሰጡት መረጃ የህወሀትን ገበና እርቃኑን አስቀርተውታል፡፡
• ህወሀቶች/ደደቢቶች እኔን ተጠቅመው የበላይነታቸውን ባሰፈነ አገዛዝ ለመቀጠል ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም ብለዋል፡፡
• በእኔ የስልጣን ዘመን ሀገሪቱም ሆነ ኢህአዲግ መለወጥ አለባቸው በሚሉ ሀይሎችና ዘላለማዊ የበላይነታቸውን አጽንተው ለመቀጠል በሚፈልጉ የህወሀትና አንዳንድ የበአዲን ሰዎች መካከል ከፍተኛ የስልጣን ሽኩቻ ነበር፡፡
•በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ሆኜ ነበር የምመራው ብለዋል  ብለዋል ፡፡
• የለውጥ ሀሳብ ባቀረብኩ ቁጥር የህወሀትና አንዳንድ የበአዲን ጀሌዎቻቸው ሀሳቡን ውድቅ ሲያደርጉብኝ ነው የኖርኩት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም እንዴት ሳንዲዊች ሆነው ሀገር ለመምራት እንደተገደዱ ሁሉንም ጉድ ዘክዝከዋል፡፡
• በመለስ ዜናዊ የተቀመጠውን የአመራር መተካካት በሚመለከትም ሰፊ ልዩነት ነበረን ፡፡ በተዘዋዋሪ በህዉሓት የተቀባ መሪ ብቻ በቀጣይና በተከታታይ የመሾም ፍላጎት ነበራቸው ።
• የሶማሊያ ክልል ጉዳይ የነበረኝ መረጃዎች እጅግ በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ ነበሩ የክልሉ የነዳጅ ዘይት ጉዳይ 80 ከመቶ ገቢው የቻይናዎቹ ሆኖ ቀሪውን የህዉሓት ኮንሰልታንሲ ድርጅቶች የሚወስዱትና መጠኑ ያልታወቀ ገቢ ደግሞ የክልሉ ፈላጭ ቆራጭ አብዲ ኢሌና የህዉሓት ጄኔራሎች የቻይና እና የሱዳን ኩባንያዎች ጋር ሕዝብ ሳያዉቅ በሚስጢር የተከወነ ነበር ።
• ይህ እቅድ ሊጠናቀቅ አልቻለም፡፡ እኔን ጨምሮ በርካታ ወጣት አመራሮች አይምሮአቸው በኮሙኒስታዊ ፖለቲካ ከተጠመቀውና ከነባር የኢህአዴግ ፖለቲከኞች ከፍተኛ ፈተና ገጠመን፡፡
• ለለውጥና ለዲሞክራሲ ዝግጁ ያልሆኑ የህወሀትና አንዳንድ የህወሀት ነባር ፖለቲከኞች በሙስና የነቀዙ ነበሩ፡፡ በዚህ የተነሳ በፓርቲያችን ውስጥ መገፋፋትና ከፍተኛ አለመረጋጋት ተፈጠረ፡፡
•|ስለዚህ ጉዳዩን ወደፓርቲዬ በመውሰድ የመልካም አስተዳደር ችግር አለብን፤ ህዝቡ አመራሩን ተጠያቂ ማድረግ መቻል አለበት አልኩኝ፡፡
• አደጋው ምዝበራውን አስፋፍቶ በውስጣችን መከፋፈል የሚፈጥር ነበር፤ ብዙ ነገሮች ከምንቆጣጠራቸው ውጪ ወጥተውም ነበር፡፡ “አገሪቷ ትጋጣለች” “እንደጉድ ትመዘበራለች”
• ወጣቶች በተለይ በኦሮሚያ ህወሀት የፈጠረው የኢፍትሀዊነት ፖለቲካ ይብቃን እኩል ተጠቃሚ እንሁን ብለው ከፍተኛ ተቃውሞ አነሱ፡፡ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችም አመጹ ተቀጣጠለ፡፡ ደደቢቶች/ እስከ መጨረሻው ድረስ ለመግደል ቆርጠው ነበር ።
• ለውጥ ካላደረግን በስተቀር መበታተናችንና ሀገሪቱም አደጋ ላይ መውደቋ ግልጽ ሆኖልኝ ነበር፡፡
• በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ቁጣውና ተቃውሞው በርትቶ የብሄር መጫረስ አደጋ አፍጥጦ እየመጣ ነበር፡፡ እኛ የምንወስደው የለውጥ እርምጃ ግን ሀገሪቱን ለማዳን ፍጹም የዘገየ ነበር፡፡ በተራው ህዉሓቶች ብድርና ገንዘብ ከፌዴራል መንግሥት እዉቅና ዉጪ ያሳድዱ ነበር ።
• የተበላሸ ብድር እየተባለ ወደ ህዉሓት ደጋፊ ድርጅቶችና ወደ ትግራይ ክልል በመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ዋነኛው ፈተናዎቼ ነበሩ ።
• የተሀድሶ ስበሰባ ባደረግን ጊዜ ይህን ይቀይራል ያልኩትን ሀሳብ የያዘ ዶክመንት አቀረብኩ፡፡
• አንድ ሰው መጥቶ ይህቺን ሀገር ከመበታተን አደጋ እንዲያተርፋት አስብ ነበር፡፡ ፈጣሪ ፀሎቴን ሳይሰማ አይቀርም ። ይህ ሰው ደግሞ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ ካለው በተለይ ከኦሮሚያ ወገን ካልሆነ አደጋው የከፋ እንደሆነ ይታየኝ ነበር፡፡
• አሁንም ቢሆን ይህ ሁኔታ እንዲቀየርና ሀገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ከአደጋው እንድትተርፍ ካስፈለገ የተጣመመው ፖለቲካችን መስተካከልና የፖሊሲ ተቃርኖአችን መፈታት ይኖርባቸዋል፡፡
• ሀገሪቱ አሁን ላይ ሶስት መሰረታዊ እንቅፋቶች እንደተደቀኑባት ያስቀመጡት ሀይለማሪያም ደሳለኝ አንደኛው ኮሙኒስታዊ ዘመም የሆነ የግራ ክንፍ ፖለቲካን ከጫካ ጀምሮ ሲያቀነቅን የኖረው ህዉሓት / ኢህአዴግ መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች የተከበሩባትና የሰፋ የፖለቲካ ምህዳር ያላት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ይፈቅዳል ወይ የሚለው ጉዳይ ነው ይሉናል፡፡
• በሌላ በኩል ደግሞ የመንግስታዊና የግሉን የኢኮኖሚ መስክ የተቆጣጠሩት በመንግስት ጭምብል ስር ያሉት ህዉሓት የሚያስተዳድራቸው ፤ ግዙፍ ድርጅቶች (እንደ ሜቴክና ኢፈርት ያሉት ሲሉ ይጠቅሳሉ) የተቆጣጠሩትንና ብልሹ አፈጻጸም ያላቸውን ፕሮጀክቶችና ድርጅቶች ወደተስተካከለ መንገድ ማስገባትም ከባድ ፈተና ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ፡፡
• በመጨረሻም በሀገራችን ያለው አንዱና ታላቁ ተቃርኖ በቡድን መብትና በግለሰብ መብት መካከል ያለው ተቃርኖ ነው ይላሉ፡፡ እኛ ግን ዘርን መሰረት ያደረገ የቡድን መብትን በማስፈን ተጠምደን ቆይተናል፡፡ ሁለቱ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ቢሆኑም በተግባር ግን ይህ አይተረጎምም፡፡
ከዚህ አካሄድ ደግሞ ህወሀትና የኦሮሞው ወገን ተጠቃሚ ሆነው ቆይተዋል፡፡ ይህ እንዴት ይፈታል ለሚለው መልሴ እነዚህን ሁለት ጉዳዮች እንደምንጋፈጥበት መንገድና አብይ በሚኖራቸው አቀራረብ የሚወሰን ነው የሚሆነው በማለትም አስረድተዋል ፡፡ ምንጭ :- Esmael Dawed Enderis

 

Filed in: Amharic