>

ፅንፍ የወጣ ብሔርተኝነት የጣራ አወርድ ብሎ የብብትን መጣል አንዳይሆን (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

ፅንፍ የወጣ ብሔርተኝነት የጣራ አወርድ ብሎ የብብትን መጣል አንዳይሆን
መንገሻ ዘውዱ ተፈራ
ሰሞኑን በአማራ ክልል በሚገኙ የዞን ከተማዎች እየተካሄደ የሚገኘው የአማራ ብሄር ንቅናቄ (አብን) እንቅስቃሴ ከአንዱ እኔም የተሳተፍኩበት አማራ ላለፉት 27 ዓመታት ሲፈፀምበት ከነበረው ግፍና መከራ አንፃር ተገቢነቱን ለመረዳት ብሞክርም ህውሓት ሲፈስበትና ሲያራግበው ከነበረው አካሄድ መለየቱ አልታየኝም።
የአማራ ክልል ህዝብ ኢትዮጽያዊነት ከአጥንትና ደሙ የተዋሀደ ከሌላው ኢትዮጽያዊ ውጭ እራሱን ለይቶ የማያይ ህይወቱም ሆነ ድህነቱ በኢትዮጽያዊነት የፀና ስለመሆኑ ማንኛውም ወገኑ የሚመሰክርለት ሲሆን እምነቱና ተግባሩም 2008 የራሱን መገደል መታሰር መሰደድ ሳይሆን የኢትዮጽያዊ ኦሮሞ ወገኖቹን መተንኮስ ውስጡን ስለነካው አትንኩብኝ ብሎ አጋርነቱን ያሳየበት በቂ ማስረጃ ነው።
ታዲያ ይህን አንድነት አብሮነት አንዴት በዚህ አይነት የህውሓት የተስሳተ ፍልስፍና አክረን እንዳንበክለውን እሰጋለሁ።
በእኔ እይታ አዎ ላለፉት 27 ዓመታት ህውሓቶች በሸረቡት ሴራ ወላጅን ከልጅ ውንድምን ከወንድሙ እህቱ ጎረቤት ከጎረቤቱ ስፈር ከስፈር ሰራተኛው በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ከሰራተኛው እንድንባላ እንዳንግባባ ሲያደርግ ቆይተዋል። ለዚህ ደግሞ መደራጀት እንዲህ ያለውን መስሪ ስይጣናዊ ስራ ለመከላከል አይነተኛ መፍትሄ መሆኑን አምናለሁ ተገቢም ነው።
ነገር ግን አንዳንድ ስጋት የጫሩብኝን ቁም ነገሮች ማንሳት የግድ ይለኛል ብየ ስለማምን እንደሚከተለው ለማቅረብ እሞክራለሁ፦
1. መደራጀት ምንም ማካካሻም ሆነ ማስተባበያ ሊቀርብለት የማይችል አስፈላጊ ተቁዋም ሲሆን የተለያየ አቅም እውቀት ሀብትን በመጠቀም የግለሰብን ሆነ የቡድን ደህንነትን ለማስጠበቅ አካባቢን ክልልን ሐገርን ለማልማትና ስራ አጥነትን ድህነትን ለማጥፋት ሁሉ ወሳኝ ሀይል ነው። ግን በመደራጀት የራስን ደህንነት ለማስጠበቅ ለመልማት ፍላጎት እንደአለንና እንደምንፈልገው ሁሉ የሌላውንም ደህነት መጠበቅ መልማት መሻት የግድ ስለሆን አደረጃጀታችን ከቂም የፀዳ በፍቅርና በይቅር ባይነት አብሮ መኖር የተመሰረት መሆን እንዳለበት አምናለሁ።
በመሆኑም ይህን ብሶት ያሰቃየው መደራጀት የጠማው ህዝብ ሳንመክር ችግሮቹን  የችግሮቹን ምንጭ ለይተን ሳናሳየው የምናደርገው እንቅስቃሴ ለሌላ ችግር እንዳያጋልጠን የሚደራጀውን ፍላጎት በጥንቃቄ መረዳትና ጥንቃቄ የተሞላበት በአስረጅ የተደገፈ ቢሆን ጠቃሚ ነው ብየ አምናለሁ።
2. እኛ የመደራጀት ፍላጎት ብቻ ስለእለን በተቀደደልን ቦይ መፍሰስ ሳይሆን ይህ የምንደራጅበትና ሊያደራጀን ስለሚፈልገው ቡድን ለመረዳት መጣር አለብን። ሳናውቀው ዝም ብለን ለመከተልማ ብአዴንስ አለሁላችሁ ብሎ አልነበር። አሁን አለሁላችሁ የሚለን አብን ያቀረበልን የትግል ፕሮግራም ቢያንስ ከድሮው የህውሓት አደረጃጀት የሚለይበትን የሌላ ዙር ተልዕኮ አስፈፃሚ አለመሆኑን በጥንቃቄ መረዳት ይገባል ብየ ለመረዳት እሞክራለሁ ሁላችንም በግል በጋር እንድንሞክር እመክራለሁ።
ለእኔ የሚታዩኝ ከፊቴ ያሉ ስጋቶች
አሳታፊነቱ ለምሳሌ ጎንደር በውስጡ በጎንደሬነታቸው የሚኮሩና የሚመኩትን ተከዜ ዳር ሳህላ ማዶ ያሉ አገው፤ ሱዳን ጠረፍ ከመተማ እስከ ቁራ ያሉ ጉምዝ፤ በጎንደር ዙሪያ ላይ አርማጭሆና ጭልጋ ያሉ ቅምንት፤ አለፋ ጎንደር ከተማ እስራኤል የሚገኙቤተ እስራኤል ወገኖቻችን ምን ታስቦአል? እውነት አማራው አይተዋቸሁም በሚለው መሽንገያ ብቻ የምንተወው ነው።
እውነት ህውሓት ይህን ክፍተት ተጠቅሞ ነገ እናንት 4 ጎሳዎች እናንተ ጎንደሬ ነን ትላላችሁ እንጅ እነሱ አይፈልጉችሁም በማለት ቅማንት አማራ እያለ ለማጋጨት ላይ ታች እንደሚለው ነገ ለማጣላት ያጠመደልን ፈንጅ እይደለም?
አንዳንድ ጊዜ ከ 20 ዓመታት በላይ በፖለቲካ ድርጅትነት ተመዝግበው ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ያላገኙትን ነፃነት አብን ተችሮት ሳይ እነ አቶ በረከት ስሞን የብአዴን በር ሲጠብባቸው የከፈቱት መሹለኪያ ይሆን ብየ አስባለሁ።
 በአጠቃላይ አማራነትን ማጠናከሩ ጥሩ ሆኖ ሳለ ለአማራ መደራጀትና መጠናከር መሰረት የሆነውን ህብር የፈጠሩ ሁሉን አቀፍ ጎንደሬነት ወሎየነት ጎጃሜንት ሸዌነት ከብብታችን እንዳናጣው ሰከን ብለን እንድናስብ ለማሳሰብ ነው።
ኢትዮጽያ በክብር ለዘላለም ትኑር።
Filed in: Amharic