>

የህወሓት ፀሃይ በምስራቅ ጠልቃለች! (ያሬድ ደግነቱ)

የህወሓት ፀሃይ በምስራቅ ጠልቃለች!
ያሬድ ደግነቱ
አብዲ ኢሌ የተባለው የህወሓት ብልሹ ኮርማ ከሶማሌ ክልል ዘወር መደረጉ ከጅግጅጋ እስከ ሞቃዲሾ የተዘረጋው የህወሓት የሽብርና የህገወጥ ንግድ ሰንሰለት የመበጣጠስ አንድ አካል ነው።
በዚህም ምክኒያት የህወሓት ፀሃይ እዚያ አካባቢ ለመጥለቋ ማሳያ ነው። ይህን ደግሞ የህወሓት የሳይበር ሠራዊት አባላት ከአንገታቸው በላይ በቀራቸው ጉድጓድ ውስጥ ሆነው በሚያሰሙት የመጨረሻ እስትንፋሳቸው አረጋግጠውልናል።
ከሰሞኑ ወደ መንበረ ስልጣን የመጡት አዲሱ የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንትም የለውጥ ኃይሉ አካል መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን ለህወሓት ምህረት እንደሌላቸው አቋማቸውን ግልፅ አድረገዋል።
እዚህ ላይ ግን ሁለት ጉዳዮች በደንብ መታየት ይኖርባቸዋል። የመጀመሪያው የህወሓት ፀሃይ በጠለቀች ቁጥር የትግራይ ህዝብ ፀሃይ እየወጣች ነውና በህወሓት እኩይ ስራና ቡድናዊ ጥቅም ምክኒያት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር በሰላም ለመኖር የተቸገረው የትግራይ ህዝብ የህወሓትን “የአድነኝ” ጩኸት ችላ በማለት ይህን መልካም አጋጣሚ በአግባቡ ሊጠቀምበት ይገባል።
የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ መልክት በዋነኛነት የሚመለከተው የትግራይን  ህዝብ ነው። 
የትግራይ ህዝብ ይህንን መልክት ሰምቶ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አሁን አገራችን ከያዘችው የለውጥ ጎዳና አንጣር ግዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም። ዶ/ር አቢይ እንደተናገሩት የትግራይ ህዝብ ወንጀሎችን ደብቆ ከተኛበት መንቃት አለበት።
ስርአት ይሄዳል፣ ስራአት ይመጣል-ይህ የማይቀር ሃቅ ነው። መታሰብ ያለበት፤ ቋሚ ስለሆነው፤ ስለወደፊት ከቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ በወንድማማችነት እና በእህታማማችነት አብሮ ስለመኖር ነው።
ይህ መሰረታዊ ነገር በጣት በሚቆጠሩ ወንጀለኞች ምክንያት መናጋት የለበትም። እስከዛሬም ድርስ በእነዚህ ወንጀለኛ- ህውሃት መሪውች ላይ ከትግራይ ህዝብ አንድም የተቃወሞ እንቅስቃሴ አለመስማታችን በጣም የሚገርም ነው። ነገር ግን አሁንም አረፈደም።  በዋለ በአደረ ቁጥር ግን በራሱ በትግራይ ሕዝብ ላይ ችግሮች እንዲወሳሰቡ ከማድረግ ውጭ ሌላ ትርፍ የለውም። አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ፤ “የትግራይ ሕዝብ (በተለይም እዚያው ነዋሪ የሆነው) ታፍኖ ነው የሚኖረው ” ብለው የሚሰጡት ምክንያት በፍፁም ተቀባይነት የለውም።ምክንያቱም፤- ኦሮሞውም፣ አማራውም ሌላውም የኢትዮጵያ ህዝብ አሁን የትግራይ ሕዝብ ታፍኗል ከሚባለው በላይ  በህውሃት ታፍኖ ሳለ ነው የህውሃትን መንግስት እስከሞት ድረስ የተቃወመው።
በመጨርሻም ይህንን የመሪያችንን ወቅታዊና አስፈላጊ መልክት የትግራይ ህዝብ ችላ ብሎ አሁንም በዝምታው ከቀጠለ ግን፤ አንዳንዶች እንደሚጠረጥሩት  “አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ” ተደርጎ በሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግንዛቤ እንዳይወሰድበት ስጋት አለኝ።
Filed in: Amharic