>

ሕውሓት በአማራ ላይ የሾማቸው ሁለቱ  ቅኝ ገዢዎች እያሴሩ ነው!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ሕውሓት በአማራ ላይ የሾማቸው ሁለቱ  ቅኝ ገዢዎች እያሴሩ ነው! !!
አቻምየለህ ታምሩ
ከታች የምትመለከቱት [ወጣቱ] አሚር አማን ሐጎስ ይባላል። እናቱም  አባቱም  የሕወሓት ሰዎች ናቸው። እናቱ የቴዎድሮስ አድሐኖም እህት ናት። አሚር አማን  የብአዴን ስራ አስፈጻሚና የአማራን ድርሻ ወስዶ  የጤና ጥበቃ ሚንስትር ሆኖ እየሰራ ይገኛል።
ሁለተኛው ሰውዬ «የአማራ ክልል» የሚባለው  ምክር ቤት ሕግ ተርጓሚ ፣ አማራን ወክሎ የፌዴሬሽን ም/ቤት አባልና  የሕግ መወሰኛ ክፍል ሰብሳቢ ነው። ስሙ  መኮነን ወልደ ገብርዔል ይባላል። የሕወሓት ታጋይ ነው።
የዘር ፖለቲካ የሚያራምድ ማንም ሰው የግድ እሱም በዘሩ መደራጀትና በዘሩ የተደራጀ ፓርቲ መሪ መሆን አለበት እንጂ ዘሩ ያልሆነን ድርጅት ሊመራና ሊወክል  አይችልም። አማራም በዘሩ መደራጀት አለበት ከተባለ  አማራን መወከል ያለበት አማራ መሆን ይኖርበታል።  አሚርና መኮነን ግን አማራ ያልሆኑና ሕውሓት በአማራ ላይ የሾማቸው  ቅኝ ገዢዎች ናቸው።
ልብ በሉ! መኮነን  «የአማራ ክልል» የሚባለው  ምክር ቤት አባል፣ አማራውን ወክሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የሆነና «አማራ ክልል ምክር ቤት» በሚባለው  መስሪያ ቤት ደግሞ  የሕግ መወሰኛ ክፍል ሰብሳቢ የሆነና  የሶስት ስልጣኖች  የእጥፍ ድርብ  ባለቤት ነው። በሌላ አነጋገር  ሶስት የአማራ ተወላጅ ወሳኝ ስልጣኖችን ደራርቦ የያዘውና  የአማራ ወኪል የሆነው  ትግሬው መኮነን ወልደ ገብርዔል ነው።
እነዚህ ሁለቱ  ከሰሞኑ  ከዘመዶቻቸው  ከወያኔዎች ጋር  የወልቃይት ጥያቄ የሚመታበትን ሴራ ሲሸርቡ ሰንብተዋል።  በርግጥ በዚህ ሴራ ከዚህ በፊት መኮነን ወልደ ገብርዔል ባለፈው አመቶ በአውስትራሊያው SBS Amharic ላይ ቀርቦ  «ወልቃይት የትግራይ አካል ነው፤ ከአማራ ጋር ምንም ትስስር የለውም።»  ሲል  በአደባባይ አውጇል።
ምስኪኑ የአማራ ገበሬ ግን እነዚህን  ቅኝ ገዢዎቹንና  ዘራችን ለሚሉት  ጥቅም ለቆመው ወያኔዎች  ላቡን እያንጠፈጠፈ ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም እየከፈለ፤ እንዲሁም  የመኖሪያ ቤት  ሰጥቶ  አዘባንኖ  ያኖራቸዋል።
ብአዴን ውስጥ ያሉ እውነተኛ የአማራ ልጆችም  የአማራ ወኪል ነን  የሚሉ  ከሆነ የአማራን ድርሻ የሚጫረቱ እነዚህ  ነውረኞች እንዲባረሩ  በመታገል  በቅኝ ገዢዎቹ ተይዞ የነበረውን   ቦታ በአማራ ልጆች እንዲያዝ ማድረግ አለባቸው።  ምስኪኑ ግብር ከፋይም እንደ በግ ካራጁ ኋላ መጎተቱን፤ ለሚያርዱት ቀለብ መስፈሩንና  ለገዳዮቹ ውለታ መክፈሉን ማቆም ይኖርበታል።
Filed in: Amharic