>

ጣኦታችሁን መለስን እዛው ማምለክ ትችላላችሁ በግድ ማስመለክ ግን አይታሰብም!!! (አንድነት ለሀገሬ)

ጣኦታችሁን መለስን እዛው ማምለክ ትችላላችሁ በግድ ማስመለክ ግን አይታሰብም!!! 
አንድነት ለሀገሬ
 
• መለስ ዜናዊ ከተደነቀ ግራዚያኒም  ይደነቅ ፤ይዘፈንለት
 
መቐለ ለመለስ ዜናዊ ብትዘፍንለት ፤በየዓመቱ ሞቱን ፤ድርጊቱን ብትዘክርለት አያስቸግረኝም። መለስ ዜናዊ የአድዋ ልጅ ነው። ከትግሬ በመወለዱ የኮራ፤ከወርቅ ዘር በመወለዱ ትግሬ ቢያከብረውና እሽከም ቢልለት አይገደኝም።መለስ ዜናዊ የእኔ ልጅ ነው፤ ለእኔ ጠቅሞኛል ካለችና በየዓመቱ ምስሉን ይዛ ሰላማዊ ሰልፍ ብታደርግ አልቃወምም። መለስ ዜናዊ ለትግሬ ጠቅሟል ብላ መቐለ ብትዘፍን፤ብታዜም፤ ቅኔ ብትቀኝ የራሷ ጉዳይ ነውና ጣልቃ አልገባም።
መቐለ ድንበር አልፋ ፤ከሚገባት በላይ ስለ መለስ ዜናዊ ማቅራራት መረን የለቀቀ አሰራር ነው። መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ሰው ሳይሆን ኢትዮጵያን ለማጥፋት የደከመና የታገለ ሰው ነው።
በኢሬቻ በዓል ጊዜ መለስ ዜናዊ ያሰለጠነው አጋዚ ወታደር ከሰባት መቶ በላይ ንጹሃን ዜጎችን ያስገደለ መዋቅር ያዘጋጀና ያደራጀን ሰው የኦሮሞ ሕዝብ አክብረው ማለት ትርጉም የለውም። ገዳይህን፤ወንድሞችህን፤እናቶችህን ፤አባቶችሁን እህቶችህን የረሸነና እንዲረሽን መዋቅር የዘረጋን ሰው አመስግኑልኝ ፤አክብሩልኝ ብሎ ለማስገደድና ለማሳመን መሞከር አይኖቻችሁን ጨፍኑና ላታልላችሁ ማለት ነው።መለስ ዜናዊ የአድዋ ልጅና የወርቅ ልጅ ብቻ ሳይሆን ለትግሬ መልካም ያደረገ እንጂ ለኦሮሞ ፤ለአማራ፤ለጋምቤላ ፤ለሱማሌ፤ለአፋርና ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ገዳይና አፈናቃይ ነውና የመለስ ዜናዊ ስም ሲነሳ ደም ያፈላል።
የሚደንቀው ግን ብዙ ዩኒቨርሲቲዎች የከፈተ፤ልማት ለኢትዮጵያዊያን ያመጣ፤መንገድ በብዛት የዘረጋ፤ባቡር በአዲስ አበባ ያዙኝ ልቀቁኝ እንዲል የቻይና ጌቶች እንዲመጡልን ያደረገ፤ኮንዶሚኒዮሞች በአዲስ አበባ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ እንዲገነቡ መዋቅር የዘረጋ ይባላል።እርግጥ እነዚህንና ሌሎችን ነገሮች እንዳሉ እንመለከታለን።ግን በአንጻሩ መለስ ዜናዊና ህወሓት ባይኖሩ እነዚህ ሁሉ ነገሮች አይታዩም ነበር ማለት ደግሞ ሌላውን ሕዝብ ጭንቅላት እንደሌለው መቁጠር ብቻ ሳይሆን የማይገባውና ደደብ አድርጎ መሳል ነው።ዩኒቨርሲቲዎች ሲገነቡ የተማሩ ፤አገር የሚገነቡ ባለሙያዎች ለማፍራት የሚል አመለካከት አለ። ግን መለስ ዜናዊ በአስተሳሰብ ያልጣሙትንና የአይናቸው ቀለም ደስ ያላለውን የዩኒቨርሲቲ ምሁራን፤ከአዲስ አበባ፤ ዩኒቨርሲቲውን ዩኒቨርስቲ እንዲባል ያደረጉትን፤እንዲባረሩ ያደረገ ጀግና ነበር። መለስ ዜናዊ ዩኒቨርሲቲ የሚገነባበት ምክኒያት የሚያስቡና አዳዲስ አስተሳሰቦችን የሚያመነጩ ለማፍራት ሳይሆን የራሱን አምላክነት የሚቀበሉና እርሱ የሚላቸውን ብቻ የሚሰሩ፤የሚናገሩ ለማፍራት ነበር።ይህንንም አንድ ለአምስት በሚባል መዋቅር በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በመዘርጋት የአስተሳሰብ አፈና ያደረገ የአድዋ ልጅ እንደሆነ እናውቃለን።ይህ ሰው ነው እንደፕሮፌሶር አስራት አይነቶችን የገደለና መሰል ምሁራንን ከአገር እንዲወጡ ያደረገ።ይህ ሰው ነው አማራን በሚኖርበት ቦታ ሁሉ እንዲረሸንና እንዲፈናቀል ያደረገ።ይህ ሰው ነው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች እንዲፈናቀሉ ያደረገ።ይህ ሰው ነው የጋምቤላን አንዎኮች የጨፈጨፈና የራሱን የወርቅ ዘር በምትኩ ያሰፈረ።የአፋር ሕዝብ በክልሉ የሚገኘውን ሐብት ለክልሉ ሕዝብ እንዳያውለው በወርቅ ዘር ቀፍድዶ የሚይዝ መዋቅር የዘረጋው።ይህ ሰው ነው በሱማሌ ያየነውን እልቂት እንዲከናወን እንደ አብዲ ኢሌ የመሰሉትን በማሰማራትና የትግሬ ጀኔራሎችን በአማካሪነት ሽፋን በማስቀመጥ መዋቅር የዘረጋው።ታዲያ እንዲህ ያለውን የጭከና ሥራ የፈጸመውን ሰው አንግሱልኝ፤ዘክሩልኝ፤አመስግኑልኝ ማለት ግራዚያኒ በአንድ ቀን ከሰላሳ ሺህ በላይ በአዲስ አበባ የረሸነና የኢትዮጵያን ሕዝብ በመርዝ ጋዝ የጨፈጨፈ አክብሩልኝ እንደማለት ነው።ለመለስ ዜናዊና ለግራዚያኒ አንድ ዓይነት ባህሪ አላቸው። በአልተናነሰ መንገድ ሁለቱም ሕዝብን ረሽነዋል።መለስ ዜናዊ አማርኛና ትግርኛ እየተናገረ ኢትዮጵያዊ መስሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲርሽንና ሲያስረሽን ግራዚያኒ ጣሊያንኛ እየተናገረ ኢትዮጵያዊያንን ረሸነ።ሁለቱም ግን ነፍሰ ገዳዮች ናቸው።ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ነፍሰ ገዳዮችን የምታነግሥ ሳይሆን ነፍስ የሚያድኑትን ታከብራለች ፤ታነግሳለች።መለስ ዜናዊ የሚመሰገን ከሆነ ግራዚያኒም ሊመሰገን ይገባዋል።መለስ ዜናዊ ያዋቀረው የጦር ኃይል ትግርኛ እየተናገር የኢትዮጵያን ሕዝብ በስናይፕር ረሸነ ግራዚያኒም የጣሊያንን ወታደርና ባንዶችን አስታጥቆ ረሸነ።ሁለቱም የራሳቸውን ሕዝብ አሰልፈው ሌላውን ጨፈጨፉ።ጉድ በሉ የተጨፈጨፈው ምን ሲባል ነው መለስ ዜናዊን እንዲያደንቅ የሚገደደው?ሰለገደለው፤እንደባሪያ ስለገዛው፤የበይ ተመልክች ስላደረገው?መለስ ዜናዊ በትግሬ፤በመቐለ ሐውልት ቢቆምለትና በየዓመቱ ቢለቀስለት፤ቅኒ ቢዘረፍለት ምኔም አይደለም።ጎንደር፤ ባህርዳር ፤መተማ ፤አዳማ ፤ቢሾፍቱ፤ሶዶ፤ጋምቤላ ፤ሞያሌ ላይ የአድንቆት ሰልፍ አድርጉ ፤ሐውልት ትከሉ፤በየዓመቱ አልቅሱ ማለት ግን መጠንን ለክቶ አለማወቅ ነው።ለሁሉም ገደብና ለዛ አለው።
የገረመኝ ነገር ደግሞ የኢትዮጵያ ቲቪ በሆነው ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚቦጠቦጥበት መዋቅር ደግሞ መለስ ዜናዊን በሚመለከት ዜና መስራቱ ነው። በክልሉ  ቲቪ ቢተላለፍ ግድ ይለኝም።በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ በሚሰራው የኢትዮጵያ ቲቪ ግን ገዳዮችን አድንቁ፤ አክብሩ ፤አመስግኑ ተብሎ ሲነገርና የማናውቀውን መልካምነቱን ስለ መለስ ዜናዊ፤ ለምናውቀው ሲያስተዋውቁን መስማት በእውነት ያማል። የሚታዩት የጦር ኃይል አባላት ሲያመሰግኑት ስሰማ አልተደነቅሁም።ከጫካ የመጣ ጀኔራል የተሾመውና የተሸለመው፤ እንዲዘርፍ በር የተከፈተለት በመለስ ዜናዊ እንደሆነ ይታወቃልና።ቢጮኽለትና ቢያለቅስለት አያስደንቀኝም። ግን መብቱንና መጠኑን ያላወቅ ጦር እንደሆነ እመለከታለሁ። አሁንም የህወሓት ወታደር እንደሆነ እመለከታለሁ።ሕገ መንግሥቱን እናስከብራለን እያለን ነው።ይህ ማለት የመለስ ዜናዊን መዋቅር እናስከብራለን ነው።አሁንም መለስ ዜናዊ የሚመራውን ጦር እያየሁ ነው።አሁንም ለትግሬ ጀኔራሎች መለስ ዜናዊ ጠ/ሚ ነው።አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አቢይ አህመድ የእነርሱ አይደለም።ኢትዮጵያ በአዲስ መንፈስ ፤በእኩልነት እየተመራች መሆኑን የትግሬ ጀኔራሎች አለመቀበላቸውን እየሰማን ነው።ኢቲቪ እኮ የኢትዮጵያ እንጂ የህወሀቶች ማቅራሪያ መዋቅር አይደለም።ኢቲቪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያቀርበው ዜና መላ ኢትዮጵያን የሚመለከት ጉዳይ እንጂ የአንድ ጎጥ መሪ ታሪክ መተረኪያ የዜና ማሰራጫ አይደለም።ይታሰብበት።መለስ ዜናዊ የሚደነቅ ከሆነ ግራዚያኒም በመረሸኑ ሊደነቅ ይገባዋል።የነፍስ ገዳይ መሪ ምሳሌ ሳይሆን የነፍስ አዳኝ መሪ ታሪክ የማንዴላን ዜና ተናገሩ።
Filed in: Amharic