>

ስለ ዶ/ር አሚር እውነታውን እንናገራለን!!!  (ከድር እንድሪስ)

ስለ ዶ/ር አሚር እውነታውን እንናገራለን!!! 
ከድር እንድሪስ
ዶር አሚር እናታቸው አማራ ስትሆን ትውልድ ቦታዋ ከጎንደር በ40 ኪ.ሜ በምትገኘው #ወገራ ወረዳ አምባ ጊዮርጊስ የምትባል ቦታ ላይ ነው ትውልድ ሀገሯ። አባቱ ሸህ አማን ሀጎስ ኤርትራዊ ናቸው። በባህርዳር ህዝብ በጣም የተወደዱ እና የተከበሩ ነበሩ።  ከቴዎድሮስ አድሀኖም ጋር የሚያገናኛቸው ምንም  ነገር የለም። ቴድሮስ አድሀኖም አጎቱ ነው የሚባለው ከእውነት የራቀ ደረቅ ውሸት ነው።
ፕ/ር ይፍሩ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዲባረር አድርጓል የሚባለው ተራ አሉባላታ ነው። ታስታውሱ ከሆነ ወያኔ የህዝባ አመፅ ሲያነቃንቀው በትረ ስልጣኑን ተለወጥኩኝ ታድሻለሁ ብሎ ከዪኒቨርስቲ ምሁራኖችን አምጥቶ ሾመ ሚኒስቴር ቦታዎች ላይ። ከእነዚህ መሀል ዶር ከሰቴ አድማሱ ተነስቶ ፕ/ር ይፍሩ ጤና ጥብቃ ላይ ተሾመ።
የተሾሙት ብዙዎቹ ቀጥታ ከት/ት ተቋማት የመጡ ስለነበር ከስራው አለም ጋር ለመሄድ እና ለመልመድ ግዜ ወስዳባቸዋል። ስለሆነም ከተሾሙት ውስጥ ከዶር ነገሬ ሌንጮ  እና ዶር ሂሩት ( ባህል እና ቱሪዝም) በስተቀር ብዙዎቹ ወርደዋል ከነበሩበት ቦታ።
የፕ/ር ይፍሩ ጉዳይን በተናጠል ስናይ ከ ወያኔ መንግስት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ጋር መሄድም መስራትም ስለከበዳቸው ( የአቅም ማነስ አይደለም) ፣ በራሳቸው መንገድ መሄድ እና መስራት ስለጀመሩ ግጨት ውስጥ ገቡ። በዚህ መሀል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በእጅጉ እየተጎዳ መጥቶ ነበር።
በወቅቱ በነበረው አሰራር ከኢህአዴግ ምክር ቤት እና ከሚኒስትሮች ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ግምገማ እና ውሳኔ ምክኒያት ፕ/ር ይፍሩ እንዲነሱ ተደረገ። እዚህ ላይ ዶር አሚር እጁ አለበት የምትል ሰው የወያኔን አሰራር እና ባህሪ አለማወቅህን ማሳያ ነው። በወያኔ ዘመን ውሳኔ የሚሰጠው በጥቂት የአድዋ ህወሓቶች ከላይ ብቻ ነበር። ሌላው ሰው ውሳኔ ተቀባይ እና ተላላኪ ነበር. በዚህ ጉዳይ ጤና ጥበቃ ሚኒስቶር የሚሰሩ ወዳጅ ጓደኛ ካለ መጠየቅ ይቻላል። እኔ ከተሳሳትኩኝ እቀጣለሁ። እነ ቴድሮስ አድሀኖም የሰሩት ወንጀል እራሳቸው መጠየቅ አለባቸው እንጁ ምንነበወጣው በሌላ ሰው ሀጢያት ዶር አሚር የሚወቀሰው ስሙ የሚጠፋው።
ዶር ቴድሮስን ግን ለፍርድ ይቅረብ ብቻ በቂ አይደለም። ከዚያም በላይ ቢደረግ ይገባዋል።
ትልቁ ነገር ከለውጡም በሓላ የለውጡ ሀይል በፍጥነት ከሆኑት ግንባር ቀደም ሚኒስትሮች የመጀመሪያ ዶር አሚር ናቸው። እየሰሩ ያሉት ስራም ድንቅ እና ውጤታማ ነው።
ማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ የምንፅፈው ያልተረጋገጠ መረጃ የግለሰቦችን እና ቤተሰቦቻቸውን ህይወት የሚረብሽ መሆኑን ማወቅ አለብን። ሀላፊነት ሊሰማን ይገባል።
የዶር አሚር ሙሉ ቤተሰብ ስም ዝርዝር መናገር እችላለሁ። ነገር ግን ከወዲሁ ቤተሰቡ ላይ ማስፈራሪያ እየደረሰበት ስለሆነ ለጥንቃቄ ስል ዘልየዋለሁ።
እባካችሁ ሀላፊነት ይሰማን!
Filed in: Amharic