>
5:13 pm - Sunday April 20, 9625

ለዛሬ "የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት አይሠራም" ተብሏል!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ለዛሬ “የእቴጌ ጣይቱ ሃውልት አይሠራም” ተብሏል!!!
                     *★★★
– ነገ ግን ጊዜው ሲደርስ በወርቅ ይሠራል!!!
ዘመድኩን በቀለ
– የሆነ እንግዳ የሆነ ደብዳቤ ሰሞኑን እንዲህ ሲል ሰነበተ።
“የአዲስ አበባ ቆርቋሪና መሥራች፣ የዓደዋው ጦርነትና ለተገኘውም ድል ቁልፏና ወሳኟ ሴት፤ ለእምዬ ምንሊክ ባልተቤት ለነበሩት ለእቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘኢትዮጵያ የመታሰቢያ ሃውልት ሊሠራ ነው። እናም የፊታችን ሐሙስ ዛሬ ማለት ነው። ነሐሴ 24/2010 ዓም ከቀኑ 7:30 የዓደዋ ድልድይ አካባቢ በሚገኘው ሲግናል አደባባይ ላይ እንድትገኙ፤ በሥነ ሥርዓቱም ላይ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታደለ ኡማና ከረጅም ዓመታት የስደት ህይወት በኋላ ወደሀገሯ የተመለሰችው አርቲስት ዓለምፀሐይ ወዳጆም በክብር እንግድነት ይገኛሉ” የሚል መልእክት ተሸክሞ በዚሁ በፌስቡክ መንደራችን ሲንጎማሸር ዋለ።
~ መሸ ነጋም #ሀገር_ወዳድ_ኢትዮጵያውያንም ይህን ዜና በሰሙ ጊዜ ከመደሰታቸው ብዛት የተነሳ ምድሪቱ አልበቃ አለቻቸው። ፈነጠዙ፣ ጨፈሩ፣ በደስታም ሰክረው አቅላቸውንም ስተው ሲፈነጥዙ ዋሉ፣ አደሩም።
~ ወዲያውኑ የኦሮሞ አክቲቪስቶች  ደግሞ ይህን ዜና በሰሙ ጊዜ እንዲህ አሉ። ፊኒፊኔን ኬኛ። እስቲ ወንድ የሆነ ሃውልቱን ሲያቆም፣ ደግሞም ሲሠራ እናያለን። ተደምረናል ስንል የምር መሰላችሁ እንዴ?  ኦሆሆ እስቲ ሞክሯት። ዋ ! እንተያያለና ብለው እሪሪሪሪ አሉ። እሪሪሪ አሉ አይገልጸውም።
★ ክርክሩ ዳኝነት አሰፈለገው
#የከተማዋ_ከንቲባ_ኢንጂነር ታከለ ኡማ የግራ ቀኙን ክርክር በእጅ ስልካቸው ላይ ሲከታተሉ ቆዩ። እናም የግራ ቀኙን ክርክር በጥሞና ሰሙ፣ አደመጡም። በመጨረሻም የሃውልቱ መሠራት ከደጋፊው እና ተቃዋሚው አንጻር የትኛው ሚዛን እንደሚደፋ ገመገሙ። እናም የሚበልጥባቸውን፣ የሚያዋጣቸውንም አይተውና ገምተውም ሳይሸማቀቁ፣ ቅሽሽም ሳይላቸው ውሳኔ ወሰኑ።
“በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ያለው መረጃ ሁሉ እንደ እውነት ከተወሰደ አስቸጋሪ ሁኔታ ይፈጥራል…” በማለት በውስጠ ዘ “የኦሮሞ አክቲቪስቶች ያሉት ትክክል ነው”። እናም [ የእቴጌ ሃውልት አይሠራም ]። አከተመ። አራት ነጥብ። ብለው ክርክሩን ዘጉት።
ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከ400 በላይ ፀረ ኢትዮጵያ አቋም ያንፀባረቁበትን ጦማሮቻቸውን ከፌስቡክ ገጻቸው ላይ ሲደልቱ ውለውና ከርመው መንጋው መስማት የሚፈልገውን ” ኢትዮጵያ ” የሚለውን ቃል እየመረራቸው በመጠቀም ወደከተማዋ ከንቲባነት የሥልጣን እርከን መምጣታቸውን ዘንግቶ በግድ የኢትዮጵያዊነትን ካባ ካልተላበሱ ብሎ ይወበራል። ጓደኛቸው ጠ/ሚ ዶኮ ዐቢይ ኢንጂነሩን ወደዚህ ቦታ ሲያመጧቸው ” ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ” ካላልክ መንግሥትህ አይጸናልህም ብለው እንደመከሯቸው ማወቅ መስማትም አይፈልጉም። እናም ኢትዮጵያዊ መልኩን ነበር ዥንጉርጉርነቱን እንደማይለቅ ሁሉ ከደም የተዋሐደ ፀረ ኢትዮጵያዊነት መቼም እንዳይለቅ ሊታወቅ ግድ ይላል።
ለቦብ ማርሌ ሃውልት ያቆመች አዲስ አበባ ለመላው ጥቁር ህዝብ አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲሄድ ላደረጉት ጀግናዋ እቴጌ ጣይቱ ግን ራሳቸው ቆርቁረው ስምም አውጥተው ” አዲስ አበባ ” ብለው ለጠሯት ከተማ ግን ቁራሽ መሬትና አንዲት ሃውልት ተነፈጉ።
እቴጌ ግን የጣሊያኑ ሰላቶ የውጫሌውን ውል ማጭበርበሩ ሳያንስ ሊያስፈራራ በሞከረ ጊዜ እንዲህ ነበር ያሉት። “ያንተ ፍላጐት ኢትዮጵያ በሌላ መንግሥት ፊት የኢጣሊያ ጥገኛ መሆኗን ለማሳወቅ ነው።ነገር ግን ይህን የመሰለውን ውል በጭራሽ አንቀበለውም።እኔ ራሴ ሴት ነኝ።ጦርነት አልወድም፤አልፈልገውም። ነገር ግን ሀገሬ እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ። ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ ! እግሩን ለጠጠር ፤ ደረቱን ለጦር አስጥቶ ፤ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ፤ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ የሌለ እንዳይመስልህ ! የኢትዮጵያን ሰው ባታውቀው ነው። ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻው ጌጡ ነው። ሂድ ባሻህ ጊዜ ተመለስ ተሰናድተን እንጠብቀሀለን ። ያንተን ወንድነትና የጣይቱን ሴትነትም ያን ጊዜ እናየዋለን.! ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ።”
Filed in: Amharic