>

ከእስራኤል እና እስራኤላውያን ምን  እንማራለን?? (ሐሰን ሙስጠፋ)

ከእስራኤል እና እስራኤላውያን ምን  እንማራለን??

ሐሰን ሙስጠፋ

፩-ትላንት

በሠው ልጆች ታሪክ ዉስጥ እንደ እስራኤለውያ መከራ ያስተነገደ የኣደም ዘር ኣለ ብሎ ለማለት በእጅጉ ያስቸግራል ።እስራኤላውያን ለዘመናት ይኖሩበት ከነበረው አገራቸው ከተባረሩ ዎዲህ ተመልሰው እንደ ኣንድ ኣገር ድጋሚ እስከተመሰሩቱበት 1945 EC በሄዱበት ሀሉ ላለፉት ሺህ አመታት ሲገደሉ፣ሲሰቀሉ የመከራን አይነት ፣በአይነት በአይነቱ ፣ሲቀበሉ፣የውሻ ሞት ሲሞቱ ነበር የኖሩት።ለኣብነት ያህልም የሁለተኛው የአለም ጦርነት ፊት ኣውራሪ የጅርመን መሪ የነበረው ሂትለር ብቻ የፈጃቸው አይሁዶች ቁጥር ከአሁኗ ኤርትራ አጠቃለይ ህዝብ ልቆ ከጅቡቲ 1ሚሊዮን ይዋስና እኩል ይሆናል።ለመረጃ ያህልም

  • በተንቀሳቃሽ ተሽከርካሪ በተሞላ የመርዝ ጋዝ የተገደሉ 700.000
  • በጥይት ተደብድበው የተገደሉ 1.3ሚልዮን
  • እንደ ኦስዊሽ፣ትሬብለንካ፣ባልስን ባሉ የመሰቃያና መግደያ ካምፖች ብመርዝ ጋዝና በሌላም መግደያ መንገድ የተገደሉ 3ምልዬን

Rif. A book by Richard Evans

Title”the third reach at war;Penguin books 2008:ISBN978-1-594-20

ሌላም ኣለ እንደ ህንዳዊው የሀይማኖት ንፅፅር ሊቅ ዶር ዛኪር ናይክ is terrorism Islam monopoly መፅሃፍ ገለፃ

የእስራኤላውያን ሞት እንግልት እና ስቃይ በጅርመን ብቻ ኣለብልቃም ።ከጅርመና ፓላንድ ሸሽተው ዎዳ ሩስያና ኣሁን ኣመማት ሲባል ሞተች ብላ ምታለቅሰዋ እንግሊዝም በሽሽት እና ስደት ዎደ ክልልቸው የገቡትን ኣይሁዶችና ቀድሞ ግዛታቸው ይኖሩ የነበሩትን ጨምሮ 4ሚለዬን ጨርሰዋል።ዶር ዛኪር ናይክ is terrorism Islam monopolly? ? በሚለው መፅሃፍ  ገለፃው ከላይ ከተጠቀሰው 4ሚሊዬን ኣይሁዳውያን ጭፍጨፋ 3ሚሊዮኑን የሶቬት ህብረቱ ስታሊን እንደፋጃቸው በማስረጃ ይሞግታል።እንደው በግርድፉ እነዚህ ለጉድ የፈጠራቸው ህዝቦች በየዎቅቱ የሰው ልጅ የደረሰበትን መርዝም ይሁን መድሃኒት መሞከሪያም ነበሩ፣ሴቶቸው በግልፅ ባደባባይ ይደፋራሉ።ይገደላሉ ።የሞተውም ሆነ የተደፋረው አይሁድ ከሆነ ማንም ማን ነው ገዳዩ ብሎ ሚጠይቅ ዬለም።ምክንያቱም ኣይሁድ ከሆንክ ዋጋህ ምንም ነው።የዚህ ፅሁፍ ኣላማ ስለ እስራኤል ህዝቦች ና የተቀበሉትን ግፍ መተረክ አይደለም ይልቁንም ኣገር ማለት ባንዲራ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማሳየት ከዚህ የተሻለ ምሳሌ ሳላገኘሁ እንጂ!!

፪-ዛሬ ላይ

ትላንት እንደ ውሻ በሄዱብት ሁላ የዉሻ ሞት ሲሞቱ የነበሩት አይሁዶች፡ሴት ልጅ በኣባቷ ፊት ስትደፋር ፣እናት ልጇ እንደ ኣይጥ መድሃኒት መሞከሪያ ሲሆን ኣይታ ከማዘን ውጪ ምንም ማድረግ አትችልም ነበር።ዛሬ ግን ከሽህ አመታት በፊት የተበተነች ኣገር እና። በሜላው ኣለም የተበተነ ህዝባቸውን  ከተበተነበት ሰብስበው እስራኤል ምትባል ሃገር ከሞተችበት በስብሳ ኣፋር ከሆነችበት ቀስቅስው መልሰው ኣገር ኣደረጓት!! አገርም ብቻ አይደላም በኢኮኖሚና በፖለቲካውም ሀያል ሃገር ኣደረጓት ለዚያው ኤንድ ምዕተ ኣመት ባልሞላ ኣጭር ግዜ።ኣሁን የኣንድ እስራኤላዊ ደም ከመቶ ፍልስጤማዊ ደም ይልቅ ዋጋ ኣለው።ይህንን ዎደኛ ነባራዊ ሁኔታ ስናመጣው

በኣንፃሩ ይህች ኢትዮጵያ ምትባል ገደኛ ሃገር የ3ሽህ ኣመት ታሪክ ያላት ብቻ ኣይደለችም ወሰኗም ኣሁን ተሸራርፎ የመጨረሻ ትንሹ የግዛቷ ክፍል ብቻነው ያለው ቀድሞማ ከቀይ ባህር በታች ያለው የኣፍሪካ ክፍል እንዳሁኑ በወሪው የሮም ጅነራል Scipio africanus ሰም ተውሰው ኣፍሪካ ሳይሉት በፉት ኢትዮጵያ ነበር የሚሉት፣ስሟ የገነነ የስልጣኔ እምብርት የነበረች፣ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ቀድማ የተቀበለች፣ትቀብላም ጠብቃ ያቆየች ና ያስተላለፋች፣ ሃገር ብቻ ኣይደለችም  ኢትዮጵያ ስሟ የኣሁኑ ኣትላንቲክ ውቅያኖስ መጠረያም ነበር።የኣሁኑ ኣትላንቲክ ውቅያኖስ ኣዲሱን ሰም ሳይሰጠው በፈት Ethiopian seaነበረና የሚባለው። እስራኤላውያን በኣለም ካርታ ለሺህ ኣመታት ያልነበረችን ሃገር ፣በኣለም ላይ ያተበተነ ዘራቸውን ስብስበው ያልነበረውን ፈጥረው ኣገር ላልነበረው ህዝባቸው ኣገር ፋጠሩለት ።ባንዲራ ሰቀሉለት ኣለም ላይ የመጨረሻውን የኑሮ ኣተላ ይኖር የነበረ ህዝባቸውን የኣለም ቁንጮ ኣደረጉት የተከበረ የታፈረ ኣገር ኣደረጉት!!።እኛ ለሺህ ኣመታት ፀንቶ የኖረ የኣባቶች  ኢትዮጵያን “ጠብቁ” የሚል የኣደራ ቃላቸውን በላን።በኢትዮጵያ ና ህዝቦቿ ነባር ባህል ኣደራ እርም፣ኣደራ ቁርባን ነበር ።ኣደራ ለክርስቲያኑ ማህተብ ለሙስሊሙ መሀላ ነበር።ዛሬ እትዮጵያ ላካድሬ ከፓርቲ፣ለዘውግ ፖለቲከኛው ክብሄር ብሎም ከጎሳም ኣንሳ ኣንሳ በአይን የማትታይ ነቁጥ ሆናለች። ነገር ግን ለነዚህ ኣገርን የሚያክል ግዙፍ ሃሳብ ይልቅ ብሄር ብዙዎችን እንደ ጅማሪ እብድ ያስለፋልፍ ይዟል !!ታላቅ የነበረችን ባለብዙ ታሪክ ሃገር በትነው ብዙ ትናንጥዬ ድንክ ሃገር ለመመስረት ትንሹም ትልቁም ዛሬ ደብሮኛል እገነጠላለሁ ይላል! ! ኢትዮጽያን ኣፈርስምታለሁ ኣያለ ይደነፋል ኣገር የሚያህል ግዙፍ ነገር በሙጫ የተጤበቀ በ ሰንበሌጥ የተሰራ ይመስል! ! ።በመጨረሻም የደራሲና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ፀጋዬን ገለፃ ተጠቅሜ ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ ለነዚህ ገንጣይ ኣለሌዎች ልግለፅላቸው!! ።

ኢትዮጵያዊነት አንዱ በተፈጥሮ የሚጎናፀፈው ሌላው ደግሞ በቸርነት የሚመፀወተው እርከን ወይም ደረጃ ያለው ማንነት ነው ብዬ በፍጹም አላምንም፣ ስያሻን የምንለብሰው ስያሻን ኣውልቀን የምንጥለውም ማንነት ኣይደለም።ሁሉም ዜጎች አሁን በታሪክ ክፉ እድል ከኛ የተነጠሉትም ጭምር እኩል ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ተጠራጥሬ አላውቅም። ነገር ግን ከአንድ ወይም ከሌላ ብሄር ወገን ነን የሚሉ ባእድና የማይገጥም ጽንሰ ሀሳብ ከየትም ለቃቅመው አገርን በመስራት ሂደት ውስጥ የተፈጠሩን ቁስሎች ቦርቡረውና ታሪክ አዛብተው፣ እንደ ብሄር የመጠቃትን ስሜት የፈበረኩና ያግለበለቡ፣ በዚህም ፍብርክ ስሜት መሰላልነት ወደ ስልጣን የወጡና አሁንም አዲስ ሌላ ድንክ አገር መመስረትን የሚያልሙ ለአገራች ህልውና የሚያሰጉ ብዙዎች መኖራቸውም እውነት ነው  በዚያውም ልክ ግን ራሳቸውን ከሌላው ይበልጥ ኢትዮጵያውያን አድርገው የሚሾሙ ዘረኝነታቸውን ኢትዮጵያ በሚል ውብ ስም የሸሸጉ በተግባር ግን ሁሉንም የዘረኝነት ብየና የሚያሟሉ፣ ከነርሱ የተለየ ሀሳብ የያዘን ሁሉ በራሳቸው የዘረኝነት ሚዛን ሰፍረው ስም የሚሰጡ፣ ኢትዮጵያውያ የሚለውን የተቀደሰ ስም በአፋቸው የመደጋገማቸውን ያህል በነውራቸው የሚያራክሱ ውድና ውብ ለሆነው ሁሉንም ለሚያስጠልለው ኢትዮጵያውያዊ ብሄርተኝነት እንደ ስድብ የሚቆጠሩ እልፎችንም ኣሁን ማየት ላያስገርም ይችላል ።ነገር ግን ዬቱንም ያህል ቢመራቸውና ቢጎምፕዝዛቸውም እውንታው ኣለም የሚያውቀን በኢትዮያዊነት እንጂ በኣማራነት ፣ኦሮሞነት ኣልያም ትግሬነት ኣይደለም ።ይልቁንም በናቅነው ኢትዮጵያዊነት ነው።ኢትዮጵያ ደግሞ ኣሁንም ከቴዲ ኣሁንም ይህችን ልዋስና ኢትዮጵያ መከራን ተሻግራ ፈተናን ተቋቁማ ብቅ የማለት ታሪክ ያላት እፁብ አገር ናት. እላችኋለሁ!!

ቸር ይግጠመን

ጽሁፉን በተመለከተ ማንኛውም ኣስተያየት hssen631@gmail.com  ኣድርሱኝ

ሀሰን ሙስጠፋ

Filed in: Amharic