>

ታማኝ ያቀረበልኝ ጥሪ ከቅንነት የመነጨ ነገር ግን በጣም የዘገየ ጥሪ ነው!!! (ጃዋር መሀመድ)

ታማኝ ያቀረበልኝ ጥሪ ከቅንነት የመነጨ ነገር ግን በጣም የዘገየ ጥሪ ነው!!!
ጃዋር መሀመድ

ታማኝ ‘ለኢትዮጵያ ህዝብ ታገል’ በማለት ያቀረበልኝ ጥሪ ከቅንነት የመነጨ ይመስለኛል። ነገር ግን በጣም የዘገየ ጥሪ ነው። በትግላቻን አምባገነናዊ ስርዓቱን ፈረካክሰን የኢትዮጲያን ህዝብ ሁሉ  ከአፈና ነጻ ካወጣነው በኋል ዘግይቶ የቀረበ ጥሪ ነው። በተጨማሪም  የ ‘ትግል’ ጥሪው የትግል ፖሊቲካን ( resistance politics) በድል አጠናቀን ወድ አስተዳደራዊ ፖሊቲካ ( governance politics) ከተሸጋጋርን በኋል አመሻሽቶ የደረሰ ጥሪ ነው። ልክ በተዋጣለት ስትራቴጂ አይበገሬ የተባለለትን አምባገነናዊ ስርዓት እንደደረመስነው አሁንም ህብረብሄራዊ ፈደራላል ዴሞክራቲክ ኢትዮጲያን ለመገንባት በከፍተኛ ፍጥንት እና ጥንቃቄ እየሰራን ነው። ይህን ስናደርግ ደግሞ ማንነታችንን ፍቀን  ብሄራችንን ክደን አይደለም። ትላንትም እንደ ኦሮሞ ታግለን ከሌሎች ብሄር ታጋዮች ጋር ተበበረን ይሄንን ለውጥ አመጣን። ትግሉ በቄሮ፣ በፋኖ፣ በበርበርታ እና ዘርማ ቢካሄድም የተገኝው ለውጥ እየጠቀመ ያለው ሁሉንም ያሀገራችን ህዝብ ነው። ትላንት በብሄር መደራጀት ሀገር ያፈርሳል ሲሉ ሀገርን ከመፈራረስ አድነን አሳይተናል። ሰላማዊ ትግል አማባገነናዊ ስርዓትን ለመቀየር አያስችልም ብለው ሲያላግጡብን የነበሩትን በተጨባጭ በሰራ አሳይተናቸው የድሉ ተጠቃሚ እንዳደረግን ሁሉ ወደፊትም ውጤት ተኮር አመራር መስጠቱን እንቀጥላበታለን።

Filed in: Amharic