>

«ኢልማን ቦፋ ቦፋደቴ!»  ኦቦ ጁኔይዲ ሳዶ  (አቻምየለህ ታምሩ)

«ኢልማን ቦፋ ቦፋደቴ!»  ኦቦ ጁኔይዲ ሳዶ 
አቻምየለህ ታምሩ
«ኢልማን ቦፋ ቦፋደቴ» የኦሮሞኛ አገላለጽ ነው። ይህ አገላለጽ ወደ አማርኛ ሲመለስ «የእባብ ልጅ እባብ» ማለት ነው። ይህ  ንግግር በጁኔይዲ ሳዶ አማራ እንደ እባብ እንዲቀጠቀጥ ለኦሮሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  የተላለፈ መልዕክት ነበር። አማራን «የእባብ ልጅ እባብ» ብሎ የሚያስበው ጂኔይዲ ኦሮምያ የሚባለው ክልል ፕሬዚደንት በነበረበት ጊዜ ስንት አማራ እንደ እባብ አስቀጥቅጦ እንደገደለ መገመት አይከብድም።
ኦቦ ጁኔይዲ  ከኢህሕአዴግ ጋር በትልቅ የስልጣን ኮርቻ የነበረና  ዛሬ ራሱን  ከፓርቲው አርቆ  ወደተቃውሞው ገብቶ ከቆየበት ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል።  ከአገዛዙ  ጋር ተጣልቶ የሸሸ የድሮ ባለስልጣን ሁሉ እንደ ሀቀኛ መቁጠርና ማጀገን ግን ጅልነት ነው።
አቶ ጁነይዲ  ሳዶ አማራን «ኢልማን ቦፋ ቦፋደቴ»  ያለው  የነገረን  ነውረኛው አባባል  ሲነገር እዚያው ሰብሰባ ላይ በአካል የነበረና የአቶ ጁነይዲ ሳዶ ስም ሲነሳ እጅጉን የሚያመው አንድ ጓደኛችን  ነው።
ጊዜው በ1997 ዓ.ም. የምርጫ ወቅት ነበር። አቶ ጁነዲን ሳዶ የኦሮሞ  ተወላጅ የሆኑትን «የአዳማ ዩኒቨርሲቲ» ተማሪዎችን ሰብስቦ ፖለቲካዊ ስብከት እያደረገ ነው። በሰብሰባው «የነፍጠኛው ስርዓት» የተባለው ስርዓት  በኦሮሞ ሕዝብ ላይ አደረሰ የተባለውን  በደል ማስረጽ ነበር።  የነፍጠኛ ስርዓቱ የኦሮሞ ሕዝብ ጠላትነት ብዙ ከተሰበከ በኋላ አሁን ያሉት የነፍጠኛ ልጆችም ከአባቶቻቸው እንደማይለዩ እንደውም ተደራጅተው የነፍጠኛውን ሰርዓት ለመመለስ እየጣሩ እንዳሉና ይህም  መፈቀድ አንደሌለበት ብዙ ተባለ። በዚሁ ብዙ ሰው በስሜት ተናጠ። በመሀል አንድ ተማሪ ተነስቶ «ታድያ የዛሬ መቶ ዓመት የነበረን ነገር ካሁኑ ጋር እንዴት በቀጥታ ማገናኘት ይቻላል? እንዴት ያሁኑ የአማራ ተወላጆች ከዚያኛው ጋር በቀጥታ መገናኘት ተጠያቂም ማድረግ ይቻላል?” ብሎ አቶ ጁኔይዲን  ጠየቀ።
ለዚህ ተማሪ ኦቦ  ጁነይዲ ሳዶ የሰጡው  መልስ እጅግ ዘግናኝ ነበር። ቃል በቃል «ኢልማን ቦፋ ቦፋደቴ» ወይንም  «የእባብ ልጅ እባብ» ሲል መለሰለት። ወዳጃችን እንዳለን ይህ መልስ ሕሊና ላናቸው ወጣቶች  እጅግ አደገኛና መሰሪ አገላለፅ ነበር። ወዳጃችን  መረጃውን የነገረን የያኔው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ  እንደ ነጁነይዲ ሳዶ አይነቶች ጥላቻን የሚዘሩና  እልቆ ቢስ  በደል በሕዝብ ላይ ያደረሱ ሰዎች ከአገዛዙ ጋር ተጣልተው መጽሐፍ ጽፈው ወይም በሌላ መልክ ተከስተው በአገዛዙ ጋር  አብረው ስለሰሩ  ይቅርታ ቢጠይቁ እንደኔ ተቀባይነት ሊኖረው እንደማይገባ ያምናል። ጁኔይዲ ግን «ተደምሮ» ዛሬ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ወንጀለኛን በአበባ ጉንጉን ለማሳመር ቢሞከርም  «ኢልማን ቦፋ ቦፋደቴ!» ያለንን  ጁኔይዲንን  ወንጀለኛነት ግን አይለውጠውም።
Filed in: Amharic