>

የፌዴራል ፖሊስን መግለጫ ሰማቹህልኝ??? (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው) 

የፌዴራል ፖሊስን መግለጫ ሰማቹህልኝ???
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 
እግዚአብሔር ያሳያቹህ! “ኢ/ር ስመኘው እራሱን እንዳጠፋ አረጋግጠናል!” ብለው ሲያውጁ ቅንጣት እንኳ አላፈሩም፡፡
በጣም የሚያስቀው ነገር ስመኘው ማስታወሻ ትቶ ነው እራሱን የገደለው አሉና ማስታወሻው “ልጆቸን አደራ!” የሚል ነው ብለው እርፍ፡፡
በእነሱ ቤት እኮ ስመኘው ማስታወሻ ትቶ እራሱን ሲያጠፋ ማስታወሻው ላይ “እራሱን ለማጥፋቱ መንስኤ የሆነውን ምክንያትና ተጠያቂውን አካል አልጠቀሰም!” ሲሉ ተጠያቂ አካል እንዳንጠብቅና የሌለ መሆኑን እንድናምን ሕዝቡን ማግባባታቸው ነው፡፡
እንግዲህ ይታያቹህ! ኢ/ር ስመኘው እራሱን ያጠፋ ከሆነና አስቀድሞ ግን ውጭ ወጥቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሊገልጸው የሚፈልገው ነገር መኖሩን ነገር ግን ከወጣ በኋላ ወደ ሕዝብ መድረስ የሚችልበትን ዕድል ሊያገኝ መቻሉን መጠራጠሩን የሚገልጽ መረጃ ከተገኘና ስመኘው መረጃውን ለሕዝብ ለማድረስ የዚህን ያህል ተነሣሽነቱ ከነበረው እንዴት ሆኖ ነው ኢ/ር ስመኘውን የሚያክል ሰው እራሱን ለማጥፋት የሚያስገድደው ከባድ ፈተና ገጥሞት እራሱን ሲያጠፋ ቢያንስ እንኳ በተወው ማስታዎሻ ላይና እንዲሁም ደግሞ ቀላል በሆነው መንገድ በኢሜይል ለሀገር ውስጥና ለውጭ የብዙኃን መገናኛዎችም እራሱን እንዲያጠፋ ያደረገውን ከፍተኛ ችግርና ተጠያቂ አካል ጨምሮ መረጃውን ሳያደርስ፣ ሳይልክና ሳያሳውቅ እንዴት ነው እራሱን ሊያጠፋ የሚችለው???
አሁን ይሄንን ቀሽም መግለጫ ማን ያምነናል ብለው ነው እንዲህ የሚወሸክቱት??? ፈጽሞ የማይመስልና የማይታመን መግለጫ ነው!!!
እጅግ በጣም ያሳዝናል!!! የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ወያኔን ከስሩ ነቅለህ ጥለህ የንጹሕ ልጅህን ደም በእልፍ ሳትበቀል የቀረህ እንደሆን ለወያኔ እንደፈለገ የመግደል መብትና ፈቃድ እንደሰጠኸው እወቅ!!!
እግዚአብሔር ሆይ! እባክህን በግፍ የፈሰሰውን የዚህን የንጹሑን ሰው ደም ፈጥነህ ተበቀል???
ወያኔ ወድቋል፣ ቤተመንግሥትን ለቆ ሔዶ መቀሌ ከትሟል፣ የመንግሥትን ሥልጣን አጥቷል ምንትስ እያልሽ የምትጃጃይ ሁሉ ይሄ የምትሉት ነገር ሁሉ የሌለ ነገር ወይም ትወናና ማስመሰል ለመሆኑ ከዚህ በላይ ማሳያ ያለ አይመስለኝም!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
                      ***
አንዲት ጋዜጠኛ በኢንጅነሩ ቀብር ቤቱ መበርበሩን ጠይቃ ነበር።
ጌታቸው ሽፈራው 
ፖሊስ ሌቦች እንደሆኑ አስመስሎ ነው የገለፀው። ግን መልሶ ምንም የተወሰደ ነገር የለም አለ።  ኢትዮጵያውያን ይህን ያህል የሞራል ውድቀት ውስጥ ነን እንበል፣ በሰው ቀብር ስርቆት ይፈፀማል ብለን እንገረም። ማንም ባልነበረበት ሌባ ገብቶ ዝም ብሎ ወጣ?  ያኔም እቃ ተሰረቀ አልተባለም። ሰነድ  ነው ተበረበረ የተባለውኮ!
~የደሕንነት ካሜራዎቹን ከመገደሉ በፊት ያስነሳው ኢንጅነር ስመኘው ነው በሉና?
~መስቀል አደባባይ ድረስ ተኪዶ ራስን የሚጠፋበትን ሌላ ተውኔትም ያስፈልጋል! ድረሱት!
እነ አብይ አንድ ሰሞን ኢንጅነር ስመኘው እንደተገደለ ተናግረዋል። አብይ አሜሪካ ላይ ቃል በቃል “በጠራራ ፀሀይ ሰው እየተገደለ” ብሎ ስለ ስመኘው ተናግሯል። አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን የመሰለ ጉዳይ ላይ ዝም ብሎ አይናገርም። አብይ ቅርቃር ውስጥ ከሚገባባቸው ጉዳዮች አንዱ ይህ የኢንጅነር ስመኘው ጉዳይ ነው። ሜቴክ አካባቢ ካሉት ግዙፍ ሰዎች ጋር ላለመጋጨትም ሆነ፣ ከትህነግ/ህወሓት ጋር ለማለሳለስ ከሆነ እዳው የአብይ አህመድ ይሆናል!
Filed in: Amharic