>
10:25 am - Sunday May 22, 2022

የትግራይ ክልል በራያ ቆቦ አካባቢ የታጠቀ ሀይል እያስጠጋ መሆኑ ታወቀ (አያሌው መንበር)

የትግራይ ክልል በራያ ቆቦ አካባቢ የታጠቀ ሀይል እያስጠጋ መሆኑ ታወቀ
አያሌው መንበር
“በአጎራባች ክልሎች ወሰን አካባቢ የታጠቀ ሀይል የማሰባሰብ እንቅስቃሴዎች ይታያሉ”
በመከላከያ ሚኒስትር የሰሜን እዝ አዛዥ ሜጀር ጀነራል ጌታቸው ጉዲና
 
የትግራይ ክልል በወልቃይት አካባቢ የማንነት ጥያቄ በተነሳበት ወቅት የወታደር ስልጣና ማድረጉና አረንጒዴ ዩኒፎርም የለበሱ መሳሪያ የያዙ ታጣቂዎችን ሲያስመርቅ እንደነበር እናስታውሳለን።በወቅቱ ይህንን ተከትሎ ህዝቡ ጭምር በአደባባይ ሴቶችን መሳሪያ እና መፈክር በማሸከም “አትነካኩን እናሳያችኋለን” የሚል ፕሮፖጋንዳ መስራቱም እንዲሁ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።ይህንን ተከትሎ የአማራ ህዝብ ወደ ቁጣ ገባ። ህወሃት ግን እንዲያውም ከትግራይ ክልል በእብሪተኝነት የፌደራል ልብስ የለበሱ የመንግስት ታጣቂዎችን ወደ አማራ በመላክ ሲቪሎቹን እነ ኮሎኔል ደመቀን አፍነው እንዲወስዱ ሙከራ ማድረጉና በኋላም የህዝባዊ አመፁ ገፊ ምክንያት ነበር።
ህወሃት የወልቃይትን ጥያቄ አልፈታም።እንዲያውም ይህ ባለበት እያለ በጠገዴ አካባቢ ይፋዊ የወታደርና ደህንነት ስልጠና እየሰጠ እንደሆነ መንግስት ሳይቀር አረጋግጧል።አሁን ደግሞ የራያ ህዝብ በአላማጣና ኮረም አካባቢ የማንነት ጥያቄ ማንሳቱን ተከትሎ ህወሃት ወደ ጅምላ አፈና፣ እስራትና ድብደባ ገብቶ ሰንብቷል።በተለይም ለዶ/ር አብይ መንግስት ድጋፍ ሰልፍ መውጣታቸውንና በማንነታችን ላይ አፈና እየተፈፀመብን ነው ማለታቸውን ተከትሎ የክልሉ መንግስት ልዩ ሀይሉን በመጠቀም የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪውን ጨምሮ ሌሎች ራያዎችን ገድሏል።
አፈናና ግድያው አሁንም ቀጥሏል።እስከ ትናንት ድረስ ከ350 በላይ የኮረምና አላማጣ ዋጃ ራያዎች ከቀያቸው ተሰደው ቆቦ ተጠልለው ይገኛሉ። በአንድ ምሽት ብቻ አንድ ቀበሌ ላይ 196 ንፁሃን የእስር ማዘዣ ወረቀት ወጥቶባቸው የተወሰኑት በጨካ ሲገቡ የተወሰኑት ወደ ቆቦ ሲሄዱ፣ ቀሪዎቹም ወደየት እንደሄዱ አይታወቅም ይላሉ ወጣቶቹ።ይህንን ተከትሎ በአዲስ አበባ የራያ ወጣቶች አደባባይ ወጥተው ጠይቀዋል። የራያ የአገር ሽማግሌዎችም “በርስታችን በሀገራችን መኖር አልቻልነም፤ ልጆቻችን እየታደኑብን ነው” በማለት ለቅሬታ ከራያ ኮረም፣ አላማጣ…ወዘተ ተነስተው አዲስ አበባ ገብተዋል።
ይህ ሁሉ በሆነበት ሁኔታ ከቀናት በፊት በርካታ ቁጥር ያላቸውና ዩኒፎርም የለበሱ የትግራይ ክልል ወታድሮች ወደ ራያ አላማጣና ዋጃ በገፍ ገብተዋል።እንዲያውም የአይን እማኞች እንደሚሉት ጊዜያዊ ካምፕ ሁሉ ተሰርቶላቸዋል።.ይህንን ሀሳብ የሚያጠናክር ንግግርም የመከላከያ ሚኒስቴር ስጋት እንዳለው በትናንቱ የEBC ዘገባ አብራርቷል።በመከላከያ ሚኒስትር የሰሜን እዝ አዛዥ ሜጀር ጀነራል ጌታቸው ጉዲና ትናንት በመቀሌ በተከበረው የአዲስ አመት ልዩ ዝግጅት ላይ ባስተላለፉት አሳሳቢ መልዕክት ክልሎች ለሌላ ተግባርና አላማ የመዘጋጀት ምልክቶች አሉ።
ሜጀር ጀነራሉ አክለውም “በአጎራባች ክልሎች ወሰን አካባቢ የታጠቀ ሀይል የማሰባሰብ እንቅስቃሴዎች ይታያሉ” በማለት ተናገረዋል።ይህም ማለት የትግራይ ክልል በአማራ ክልል ድንበር አካባቢ ሀይል እያሰፈረ እንደሆነ የተወራውን እያረጋገጡ ነው።የትግራይ ክልል ይህንን ተግባር ላለፉት ሶስት አመታት በስፋት ሲሰራበት የቆየ ሲሆን በቀደምም በትግሪኛና አማርኛ ባወጣው መግለጫው ላይም የተለያዩ ትርጉም ያላቸው በይዘት ተቀራራቢ ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ ለአማራዎች ሰጥቷል።ስለሆነም የትግራይ ክልል በፌደራል ስርዓቱ ካለመታዘዙም አልፎ ለአጎራባች ክልሎች ስጋት መሆኑ በግልፅ መታየቱን መከላከያ ሚኒስትርም ጠቁሟል።
ይህ እየታወቀ እና ዜጎች መብታቸው እየታፈነ በአደባባይ እየተገደሉ እንዲሁም ተፈናቅለው ጫካ ውስጥ በርሃብ እየሞቱ እያየ የፌደራል መንግስት መከላከያ እንዲገባ ያላደረገው ለምንድን ነው? ብለን ሁላችንም ልንጠይቅ ይገባል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ክልል መንግስት የመንግስት ግምጃቤትን መሳሪያ እያወጣ በነፍስ ወከፍ ማስታጠቁ ግምት ውስጥ ተገብቶ የአማራ አርሶ አደር ራሱን ይጠብቅ ዘንድ ስራ ቢሰራ እንዲሁም የፌደራል መንግስትም ቶሎ ጠልቃ ገብቶ ራያና ወልቃይትን ወደ እናት ግዛታቸውና ወደ ህዝባቸው አማራ ይመልሱ ዘንድ ሁላችንም ልንጮህላቸው ይገባል።
በመከላከያ ሚኒስትር የሰሜን እዝ አዛዥ ሜጀር ጀነራል ጌታቸው ጉዲና  https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1913652545386528&id=100002254023027
Filed in: Amharic