>

ሲጥል እንጅ ሲታገል የማይታየው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው!!! (ሚኪ አምሀራ)

ሲጥል እንጅ ሲታገል የማይታየው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው!!!
ሚኪ አምሀራ
ከህዝቡ በተጨማሪ በራሱ በኢህአዴግ ዉስጥ የተካሄደዉ ትግል ለዉጡን ፈጣን አድርጎታል፡፡ በተለየም በኦህዴድ እና በብአዴን ዉስጥ ያለዉ የለዉጥ ሃይል ወደ ህዝቡ መወገኑ ህወሃትን አንገዳግዶ መቀሌ ላይ ደሮ ጠባቂ አድርጓታል፡፡ አዎ ለህዝቤ ጄኔራል ነኝ በማለት ህወሃትን ፊት ለፊት በመጋፈጥ የጀመሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ በዚህ አመት ጥሩ የኢህአዴግ ፖለቲከኛ አድርጌ መርጫቸዋለዉ፡፡ አቶ ገዱ ህወሃትን እንዴት ማንበርክክ እንደሚቻል ቀድመዉ የተረዱ እና ለሌችንም ያስተማሩ ናቸዉ፡፡
 ሲጥል እንጅ ሲታገል አይታይም የሚበላዉ አቶ ገዱ በብዙ ፈተና ዉስጥ ሆነዉ የህዝቡን ፍላጎት ከሞላ ጎደል ለመረዳት ሞክረዋል፡፡ የእርሳቸዉን የለዉጥ ፍላጎት ከማንኛዉም በላይ አዳጋች የሚያደርገዉ ደግሞ በራሳቸዉ ፓርቲ ዉስጥ ከግማሽ በላዩ ለዉጥ የማይፈልግ መሆኑ ፤ ለዉጥ አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን ከግማሽ በላይ የሚሆነዉ የማእከላዊ ኮሚቴ እና ላይኛዉ አመራር ከብአዴን ይልቅ ጥሩ ህወሃት መሆናቸዉ፡፡
የህሀዋት የአፈና መዋቅር እና ወታደሩ ሌላዉ አስቸጋሪ ነገር ነበር፡፡ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ የአማራ ወጣት እና የአክቲቪስቶች ጫና ለአቶ ገዱ ብርታት ቢሆንም ፈተናም እንደሚሆንበት ሳይታለም የተፈታ ነዉ፡፡ ይሄን ሁሉ ተቋቁመዉ ብአዴንን በመጨረሻም ሪፎርም ለማድረግ መዘጋጀታቸዉ፡፡ የብአዴን ሊቀመንበር ሳይሆኑ እንኳን በድርጅቱ ላይ ለዉጥ እንደሚመጣ በእርግጠኝነት መናገራቸዉ፡፡
በባህርዳር ሰልፍ ያደረጉት በሳል ንግግር፡፡ ያመጹትን የራሳቸዉን አባላት ተለወጡ ወይም ትወገዳላችሁ ማለታቸዉ፡፡ እንዲሁም አይነኬ የተባሉ አባሎቹን ማገድ መጀመሩ፤ አጀንዳወችንም መዉሰዱ፡፡ በ 17ቱ ቀን ስብሰባ ላይ ዶ/ር አብይ እና አቶ ለማ ህወሃት የእስር ማዘዣ አዉጥታ አስራለዉ ስትል  እኔ እያለዉ ይህ አይሆንም አለበለዚያም ብአዴን ከኢህአዴግ ይወጣል በማለት ህወሃትን ተስፋ ያስቆረጡት አቶ ገዱ የሰከነ እና ጥሩ ፖለቲካ በኢህአዴግ ዉስጥ ሲጫወቱ ከርመዋል፡፡  በአዲሱ አመት አቶ ገዱ እና ጓዶቻቸዉ የተሻለ በመንቀሳቀስ የአማራን ህዝብ ብሎም የአትጵያን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብር ሪፎርም እና አጠቃላይ ፖለቲካዊ ለዉጥ ያመጣሉ ብለን እንጠብቃለን፡፡
Filed in: Amharic