>

የኦነግን አርማ ለመስቀል የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ ነቃቅሎ መጣሉ ለምን አስፈለገ??? (ይድነቃቸው ከበደ)

የኦነግን አርማ ለመስቀል የሀገሪቱን ሰንደቅ አላማ ነቃቅሎ መጣሉ ለምን አስፈለገ???
ይድነቃቸው ከበደ
በአዲስ አበባ መድሀኒያለም አካባቢ ችግር ተፈጥሯል:: የችግሩ መንስኤ የኦነግ ባንድራን የያዙ “ቄሮ”ዎች በመኪናዎች ተጭነው መጥተው ከአስኮ ጀምሮ የኦነግን ባንዲራ እየሰቀሉ አስፓልቱን ቀለም እየቀቡ በመምጣት ፓስተር አካባቢ ሲደርሱ ከአካባቢ ወጣቶች ጋር አለመግባባት ተፈጥሯል ።
 የኢትዬጲያ ባንዲራ ነቅለው በመጣል።   የኦነግን ባንዲራ ሲሰቅሉ የተመለከቱ ወጣቶች እንዴት ተደርጎ በሚል የተነሳው ውዝግብ ወደ ድንጋይ ውርወራ አድጎ ለፖሊስ ያስቸገረ ትርምስ ተፈጥሯል።
አዲስ አበባ አስኮ ፣መድኃኔዓለም፣ አውቶቡስ ተራ ያለው አካባቢም ግርግሩ እየበረታ ሄዷል ፤ “ቄሮ” ነን በሚሉ  ወጣቶች  እየተሰራ ያለው ስራ ተገቢ ያልሆነ እና ከተማዋንም ወደ አስከፊ ትርምስ የሚወስዳት እንደሆነ ነው የሚገባን ።
በመሰረቱ ባንዲራው የአገሪቱ ብሄራዊ ሰንደቅ አላማ እንጂ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት መለያ አርማ አይደለም።
“ቄሮ” ዎቹ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሳያወርዱና መሬት ላይ ሳይጥሉ እነሱ የሚፈልጉትን መስቀል እየቻሉ፤ ጉዳዩን ወደሌላ እንዲያመራ ማድረግ ተገቢ አይደለም ፤ በዚህ ምክንያት  የወንድማማቾቹ ፀብ በፍጹም መፈጠር  የለበትም ።
~ የባንዴራ ውድድር ወደ ከፋ ግርግር ሳያመራ በፊት መንግሥት ከወዲሁ መላ በመፈለግ መፍትሄ ቢሰጥበት መልካም ነው።
~ አዲስአበቤ ሰፈር እንጂ ብሔር የለውም ለሚሉ የሸገር ልጆች መጪው ጊዜ ከበድ እያለባቸው የሚሄድ ይመስላል።
Filed in: Amharic