>

በዛላ አምበሳ የተፈጠረ አስቂኝና አሳፋሪ ታሪክ!!! (የሰሜኑ ቋያ)

በዛላ አምበሳ የተፈጠረ አስቂኝና አሳፋሪ ታሪክ!!!
የሰሜኑ ቋያ

የሁለቱ አገራት መሪዎችና ከፍተኛ አመራሮች ሲገናኙ ደብረፂዯን ፕሬዝዳንት ኢሳያስን ስላም ሊል ሲል ይቁነጠነጣል ከዛ ወደ ኢሳያስ ሲቀርብ እየተርበተበተ እጁን ከኪሱ አስገብቶ ሲያወጣ ያየውና ይከታተለው የነበረ የኢሳያስ ሲቪል ለባሽ ጠባቂ ተከትሎት ከኪሱ ይገባል ኢሳያስም ደብረፂዯን እየሳመ እያለ ይሄ ሲከሰት መለስተኛ ግርግር ይነሳል ኢሱም ተበሳጭቶ ዛላአንበሳ ላይ ወደታደሩን ሰላም ብሎ ቀሪ ፕሮግራሙን ትቶ የአገራችንን ጠቅላይና ምክትል ሚንስትሮች መክሮ ወደ ቀጣዩ ፕሮግራም ሄዱ የእኛዎቹም መሪዎች ይቅርታ ጠይቀው ነገሩ እንዳይጎላና ወደ ህዝቡ ወሬው እንዳይዛመት ተመካክረው ተለያዩ ::ይህም ብቻ አይደለም ይህች አቅሙን አያውቅ ደንቆሮ ህወሃት የምትባል አሳፋሪ ድርጅት ለኤርትራ አስመራ ላይ ፅ/ቤት ልክፈት ብላ ጠይቃ የኤርትራ መሪዎች መሳቂያ ሆና ነው የሰነበተችው ::
ኢሱም ” እባካችሁ ህግ የሚባል ነገር አስተምሯቸው ወይም አያሳፍሯችሁ” ብሎ ለመሪዎች መናገሩን ስንስማ እነ አጅሬ ገና እንኳን ለጎረቤት ለአለም ህዝብ ያስቁብናል ማፈሪያዎችችች ብለን ሳቅን ::

ሌላው ዛላአንበሳ ታሳዝናለች በእውነት በጣም !!ከትናንቱ ጋር ሶሰት ጊዜ ደግሳ ሶሰቱም በመሪዎቿ ቀዥቃዣነት ህግ አላዋቂነት ድንቁርና ምክንያት ተበላሽባት ::
አንደኛው – ትንሽ ድግስ አድርጋ ጠርታ ኤርትራውያን አልተዘጋጀንም ብለው ዘጉ ::
ሁለተኛው – ያለ ኤርትራና የኢትዮጵያ መንግስት እውቅና እኛ በራሳችን የህዝብ ግንኙነቱን ጀመርን ለማለት ትልቅ ዝግጅት ተደርጎ ደብረፂዯን ሊንተባተብ ተዘጋጅቶ ከኤርትራ በኩል ሁለት የተለያየን ህዝቦች ነን የእኛና የኢትዮጵያ መንግስት እውቅና ባልስጡት ዝግጅት አንገኝም የሚል መልዕክት በወታደሮች አማካኝነት ልከው ቀሩ ምግቡንም እራሳቸው ብቻቸውን እየቆዘሙ በሉ የደብረፂዯን ወረቀትም ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ተጣለች
ሶስተኛው- ይሄው ጉደኛው ደብረፂዯን ምንም ነገር ሳይዝ ኢሳያስን ሲያይ በመርበትበቱና እጁን ከኪሱ አስገብቶ በማውጣቱ አጃቢዎቹ ባዩት ነገር ደስ ስላላቸው ህዝቡ እና የሁለቱ አገር መሪዎች በአግባቡ ሳያወጉ ተበላሽ ::
ለማንኛውም የኤርትራና የትግራይ ህዝብ በመካከላችሁ ህወሃት የምትባል ከይሲ ያስቀመጠችውን ግንብ አፍርሳችሁ በመገናኘታችሁ ደስ ብሎኛል ::
ነገር ግን ይህች ነቀርሳ ህወሃት በህይወት ካለች ይሄ ስላም አስተማማኝ አይደለምና ችግሩን ከመስረቱ ለመንቀል ከኢትዮጲያ ህዝብ ጎን ቁሙ እላለሁ ::

Filed in: Amharic