>

ትንንሽ አጀንዳ እየሰጡ የሚቀጣጠለውን እሳት ዳር ሆኖ ለመሞቅ ማሰብ አላዋቂነት ነው!!! (ሳሙኤል ጌታቸው)

ትንንሽ አጀንዳ እየሰጡ የሚቀጣጠለውን እሳት ዳር ሆኖ ለመሞቅ ማሰብ አላዋቂነት ነው!!!
ሳሙኤል ጌታቸው
ህወሃት ወደ መቀሌ ተገፍታለች። ወያኔ ይውደም ~ Down Down Woyane እያሉ ወጣቶችን ማሰባሰብ ጊዜ ያለፈበት ይመስላል። ዘውገኞቹ በሀሳብ ፓለቲካ እንደማያሸንፉ ያውቃሉ ፤ ስለዚህ አምላካቸውን የጠላት ያለህ እያሉ ነው።
ዛሬ ዛሬ ለብሄር ፓለቲከኞች ዋንኛ ጠላታቸው የአንድነቱ ሀይል ነው። ኢትዮጵያ ናት ጠላታቸው። ትናንት ወያኔ ከቀያችን ገፋን ሲሉ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ‘ሰፋሪ’ ያሉትን ኢትዮጵያዊ ከቀዬው ማፈናቀልን ነው እንደ ትልቅ የፓለቲካ ግብ የሚቆጥሩት።
አዲስ አበባ የአንድነቱ ሀይል መዲና መሆኗ ያሳየው የጳጉሜ 4ቱ ትዕይንት ጎሰኞቹን አስደንግጧቸዋል። ከመቱ እስከ ሂርና ከጎባ እስከ አሌልቱ ላለው ደጋፊያቸው ጠላትህ ይኸው ይሉት ዘንድ ትንኮሳ provocation ጥሩ ስልት መስሎ ታይቷቸዋል። በቄሮ ስም የሚንቀሳቀሱ አክራሪ ጎጠኞች ሁካታውን ደም መቃባቱን ይፈልጉታል ፤ ገጠር ለተቀመጠው ወጣት “ወገንህ አዲስ አበባ ላይ ተፈጀ” በሚል ለመቀስቀስ እሳቱን ለማግለብለቢያ እንደ ቤንዚን ይጠቀሙበታል።
 ታዬ ደንዳ ይህን ነው ያለው፦ 
ከዝህ በፊት ብያለሁ። አሁንም ደግሜ እላለሁ! ከትናንሽ አጀንዳዎች እንዉጣ። ስለ ምልክት ሳይሆን ስለሀገር ከልብ እናስብ! ሀገር ካለች ባንዲራ መስቀል እና ሀዉልት መገንባት አይከብድም! ሀገር ከሌለ ግን ባንዲራ ብቻዉን ትርጉም የለዉም! አሁን ሊቢያ ወይም የመን ላይ ባንዲራ መያዝ ወይም ሀዉልት መትከል ምን ያደርጋል? ችግራችን በባንዲራ ወይም በሀዉልት አይፈታም።የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ።  – ጆሮ ያለዉ ይስማ!
እንዳለው ከግጭቱ ጀርባ አትራፊዎች አድፍጠዋል ፤ እያንዳንዷ ድንጋይ ውርወራ የእነሱን 4ኪሎ የመግባት ህልም ዕውን የማድረግ ያህል ናት !
ለወጣቶቻችን ምክሬ አንድ ነው። ኦነግ ሲፈልግ ፓርላማውንም ቀለም ይቀባ። ወደነበረበት ቀለም የቅዳሜው ጫጉላው እንዳለቀ ወደነበረበት ቀለም   ይመለሳል። ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባው እስከመንደር ድረስ ህዝብን ማደራጀት ፤ የኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት መርሆዎች ማሳወቅ ላይ ነው።
 አዲስ አበባን ፊንፊኔ የማድረግ፣ ‘ሰፋሪ’ የተባልነውን ሰዎች የማፈናቀሉ ፕሮጀክት ዛሬ ሀሳብ ላይ ብቻ ያለ ወሬ ነው ፤  ዕውን የሚሆንበት ትልም ግን ብሄረተኞቹ ጋር እንዳለ መዘንጋት አያስፈልግም። ያንን መከላከል የሚቻለው በመደራጀት ብቻ ነው።
Filed in: Amharic