>

....አባታችሁ እምዬ ምኒልክ ከአፀደ ገነት! (ቴዎድሮስ ታደሰ በላይ)

አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ!!!
አባታችሁ እምዬ ምኒልክ ከአፀደ ገነት!
ቴዎድሮስ ታደሰ በላይ
“ይድረስ ለምትወደን እና ለምንወድህ ህዝባችን እኔ አባትህ ንጉስ ምኒልክ ያደረኩልህን እልፍ ስራና ውለታ ቀጣዩ ትውልድ ያስበውና ይዘክረው ዘንድ ማስታወሻ የሚሆን የመታሰቢያ ሐውልት ከዛሬ 87 ዓመታት በፊት ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም ልጀ ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ለማሰራት አሰቡ፡፡
ሐውልቱንም በጀርመናዊው መሃንዲስ ሙሴ ሄንትል አማካኝነት አስጠንተው፤ ከጀርመን ተቀርፆ እንዲመጣ አዘዙ፡፡ ሀውልቱ የተመደበለት ቦታ ተደልድሎ ከተዘጋጀ በኋላ ገና ሳይተከል/ሳይቆም ልጀ መጋቢት 22 ቀን 1922 ዓ.ም አረፉ፡፡
በመሆኑም የልጀን እረፍት ተከትሎ ንጉሰ ነገሥት ለመሆን እየተዘጋጁ የነበሩት ያኔ እኛን ሁላ ፈንግሎ አልጋ ወራሽ እንደሚሆን የተነበይኩት ተፈሪ መኮንን፣ ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም ሐውልቴን በታላቅ ክብረ በዓል እንዲተከል አደረጉ፡፡
በሐውልቴ ላይ እኔን ካባ አልብሶ አንባር አስጠልቆ እጄን ጣምራ ጦር አሲዞ በፈረሴ በ‹አባ ዳኘው› ላይ አስቀምጦ በግርማና በሞገስ እንድታይ አደረገኝ፡፡
የሐውልቴ ቁመት ምግባሬን አስቦ እንጅ ከተፈጥሮ አካላዊ መጠኔ በላይ ነው። እኔን በፈረሴ ‹አባ ዳኘው› ላይ አውጥቶ፤ ፊቴ ወደ ሰሜን መልሶ፤ ዳኘውን በኋላ እግሮቹ አቁሞ፣ የፊት እግሮቹን ወደላይ አንስቶ በቆረቆርኳት ከተማ እንብርት ላይ  ‹‹ከትልቅ ወይንም ከትንሽ መወለድ ሙያ አይደለም፤ ራስን ለትልቅ ታሪክ መውለድ ግን ሙያ ነው›› የሚል ጽሑፍ ከስሬ አትሞ ከፍ አድርጎ ከመልአኬ ቅዱስ ጊዎርጊስ ደብር ፊት አቆመኝ።
ለዚህም የሀገሬ ህዝብ ልዕል ምስጋናየ ይድረስህ።
ይህን የመታሰቢያ ሀውልቴን ያ ሞዥልቄ የገረፍኩት ፋሺስት ጥልያን ሀገሬን በወረረችበት ወቅት በ1929 ዓ.ም እንዳፈረሰው ሰማሁ አፈራረሱንም ብርሃኑ ድንቄ የተባለው የውጭ ማለፊያ ቆንስል ‹‹የአምስቱ የመከራ ዓመታት አጭር ታሪክ›› በሚል መጥሀፉ እንዲ ከትቦት አንበብሁ፦
 ‹‹ … በቅድሚያ ሐውልቱ ያለበትን አካባቢ ረጅም እንጨት እየማገሩ በቆርቆሮ ሲያጥሩ ሰነበቱ …. ይህንን ያየው የአዲስ አበባ ሕዝብ ‹‹ሊያፈርሱት ነው›› ብሎ እርስ በእርሱ በሐዘን መነጋገሩን ቢሰሙ ‹‹ልናድስ›› ነው ብለው አስወሩ፡፡ ሁሉንም ነገር ካመቻቹ በኋላ ግን በየበሩ በታንክ ጭምር ጥበቃ አጠናክረው … ወደ ማታ የአራዳን አካባቢ በታንክ አጥረው በባውዛ ሌሊቱን ከተማውን እየተቆጣጠሩ በሌላ ኃይል ደግሞ ሐውልቱን ሲያፈርሱ አድረው ሲነጋጋ ወደ አልታወቀ ቦታ ወስደው ቀበሩት፡፡ ሕዝቡ እድሜና ፆታ ሳያግደው ሐዘኑን ይገልጽ እንደነበር አዛውንቶች ይመሰክራሉ …”
በጊዜው የአዲስ አበባ ነዋሪ የነበረው የሃንጋሪው ዶክተር ላዲ ስላስ ላቫ እንደፃፈው፣ ሐውልቱ ከፈረሰበት ቦታ ቆመው ያለቅሱ የነበሩትን ሰዎች የጣሊያን ወታደሮች በኃይል ይበትኑ እንደነበር ገልጿል፡፡”
ደሞ አንድ ሕፃን ልጅ ሲያለቅስ ጥልያኖች ደርሰው ለምን እንደሚያለቅስ ቢጠይቁት ‹‹የንጉሱን ምልክት ስላወረዳችሁ ነው›› ብሎ እንደመለሰላቸውና ጣሊያኖችም ከሙሶሊኒ ሌላ ንጉሥ እንደሌለው በመንገር ልጁን ገርፈው እንዳባረሩት ጃንሆይ ራሳቸው በአንደበታቸው ነግረውኛል፡፡ ጥልያኖች ሐውልቱን ካፈረሱ በኋላ ሰው ሳያይ ሸፍነው በመውሰድ በታላቁ ቤተ-መንግሥት አዳራሽ ጀርባ ቀበሩት …››
የፋሺስት እብሪተኛ ወራሪ ኃይል ከኢትዮጵያ ከተባረረ በኋላም፣ ሐውልቱ ከተቀበረበት ቦታ ወጥቶ እንደገና ታድሶና ተጠግኖ ሚያዝያ 27 ቀን 1934 ዓ.ም ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንዲቆም ጃንሆይ እንዳደረጉ ነግረውኛል፡፡
እና የሀገሬ ህዝብ ሆይ በኔ ዙሪያ የሚነሱ ጉንጭ አልፋ ክርክሮችን እሰማለሁ አሁን የወረሞ ህዝብ ለምን በኔ ላይ እንደተነሳ ሊቀ ሰይጣናችሁን መጠየቅ እወድ ነበር?! ግን እዚህ ሰማይ ቤት ያለንበት ምድብ ስለሚለያይ መጠየቅ አልቻልኩም። ደሞስ ገሀነም ከምትቃጠል ነብስ ጋር ንግግር ምን ሊያደርግልኝ?!
ግን ማርያም ብየ እነግራችኋለሁ እነሱን እንዳባታቸው አሳደርኳቸው እንጅ ምንም አልበደልኳቸው! በድለህናል ካሉ? በዘመነ መንግስቴ መጠየቅ ነበር የወንድ ወጉ።
እና በደም እና በአጥንቴ ነፃ ያወጣሁህ የተወደድከው እና የተከበርከው የሀገሬ ህዝብ ሆይ፦ የኔን ሀውልት ሊንድ የሚመጣ #ፋሽሽት ጥልያን እንጅ የሀገሬ ህዝብ አይደለም። አይሆንም። ምን ማድረግ እንዳለብህ ብልሀቱን ላናንተ አልነግራችሁም።
የሀገሬ ሰው ብዙ ብዙ ነገር ብልህ በወደድኩ ነገር ግን የዘመንህ እና የዘመኔ የኑሮ ጥበብ በአያሌው ስለሚለያይ ለትርጉም ክፍት እንዳይሆን ብየ ተቸገርኩ። ብቻ ግን የዘመናችሁ ቦለቲካ መደራጀት ነውና ሳልደራጅ እንደታደግኳቹህ ተደራጅታችሁ እኔን ሳይሆን ራሳችሁን ታደጉ። ያ ቋረኛ አንበሳ እንደነገራችሁ ሀውልቴን እናንተ ቁማችሁ ብታስንዱ ለኔ አይደለም ለራሳችሁ አልቅሱ።
አባታችሁ እምየ ዳግማዊ ሚኒሊክ ከአፀደ ገነት!”
Filed in: Amharic