>

ቄሮ ማነው... አመራሮችስ አለው? (ዐቢይ ሠለሞን)

ቄሮ ማነው አመራሮችስ አለው?

ዐቢይ ሠለሞን

በአዲስ አበባ ዙሪያ ላይ ”ቄሮ ነን” ባዮች  ሰዎችን እያፈናቀሉ ይገኛሉ፡፡ በመጀመሪያ ”ቄሮ ” ማነው?… የፖለቲካ ፓርቲ ነው? አመራሩስ ማነው? ቄሮም ሆነ በሱ ስም ለሚከሰቱ ግድያዎች፣ማፈናቀሎች እና ዝርፊያዎች የሚጠየቀውስ ማነው? የመንግሥትስ ቸልተኝነት እና ትዕግስት እስከምን ድረስ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የሀዘን መግለጫ ሰተዋል፡፡ እናም የተፈናቀሉትን የሚደገፍ ኮሚቴ እንደተቋቋመ ገልጸዋል፡፡ፖሊስ ፊልም ላይ እንደምናየው አስከሬን ለማንሳት ሆኗል የሚደርሰው፡፡
70 የሚሆኑ ሰዎችንም ጠርጥሮ እንደያዘ ገልፀዋል፡፡

በዚው ከቀጠለ ወደ ለየለት ትርምስ እንዳንገባ ስጋት አለ!

 እናም ቄሮ ፋኖም ሆነ ዘርማ ወይ በድርጅት ታቅፎ ተጠያቂነት ያለው አመራርና ድርጅት ሊሆኑ ይገባል፡፡
ይህም በነሱ ስም የሚደረጉ ወንጀሎችን ይቀንሳል፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ ለውጡን ለማምጣት እስከ ሆነ  ድረስ እነዚህ ግሩፖች የተሰባሰቡት ይፈለግ የነበረው ለውጥ በተወሰነ መልኩ ስለመጣ እነዚህ ግሩፖች መበተን አለባቸው ብዬ አምናለው ፡፡ አለበለዚያ… ቄሮ፣ ዘርማ እና ፋኖ ጠርተው በመውጣት ሃላፊነት የሚወስዱ መሪዎችና ድርጅቶች ሊሆኑ ይገባል። ካልሆነም የምናየው ነገሮች በከፋ መልካቸው መቀጠላቸው አይቀሬ ነውና!

Filed in: Amharic