>

መንግስት እንደሀገር ሽማግሌ መምከር ሳይሆን፣ ህግ ማስከበር አለበት!!! (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

መንግስት እንደሀገር ሽማግሌ መምከር ሳይሆን፣ ህግ ማስከበር አለበት!!!
ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
.
እየሆነ ያለው በፍጹም ከሰብአዊነት ውጭ ነው፡፡ ሰው እንኳን በወገኑ ላይ እንዲህ ያለውን ዘግናኝ ግፍ አይሰራም፡፡ ጅጅጋ፣ አዋሳ፣ ሻሸመኔ፣ . . . . ቡራዩ/ አሸዋ ሜዳ!  . . . ግድያን፣ ዝርፊያን፣ የእናቴችንና እህቶችን መደፈር . . . . የእለት – ተእለት መዝገበ ቃላችን አካል እየሆነ እየለመድነው ነው፡፡ ያስፈራል፡፡ . .  . ህግ የሚያስፈልገው ደካሞችን ከጉልበተኞች፣ ሰላማዊ ዜጎችን ከግፈኞች ለመጠበቅ ነው፤ መንግስት የሚያስፈልገው ደግሞ ህግን ለማስፈጸም ነው፡፡ በየሰዉ ውስጥ ያለው የአውሬነት ባህርይ በመንግስት የህግ ሉጋም ከግልቢያው መገታት አለበት፡፡ መፈክርና ምክር ለሰለጠነ ሰው ነው፡፡ . . . በእያንዳንዱ የዜጎች ጥቃት ተጠያቂዎችንና የተሰጠውን ፍትሀዊ ፍርድ መንግስት ለህዝቡ እስካልገለጸ ድረስ፣ በየጥቃቱ ማግስት የሚሰጥን ትርጉም የለሽ መግለጫ የግፉ አካል እስኪመስል ድረስ እየተደጋገመ ነው፡፡ . . .
Filed in: Amharic