>

ኢትዮጵያን ለመበታተን ጋብቻ የፈፀሙት ሃይሎች የጫጉላ ጊዜ ላይ ናቸው!!! (መሳይ መኮንን)

ኢትዮጵያን ለመበታተን ጋብቻ የፈፀሙት ሃይሎች የጫጉላ ጊዜ ላይ ናቸው!!!
መሳይ መኮንን
ይህ በፎቶ ግራፉ ላይ የሚታየው የሁለቱ ሰዎች መገናኘት ያጋጣሚ ቢሆን እንኳን መመርመር አለበት:: ፅንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች መቀሌ ከመሸገው የህወህት ቡድን ጋር በጥምረት እየሰሩ ለመሆናቸው በቂ መረጃዎች አሉ::
የጀዋር መሀመድ ቡድን ከዶ/ር ደብረፅዮን ህውሃት ጋር በድብቅ መገናኘቱም ተረጋግጧል።
አቶ ጌታቸው ረዳ እና ፕሮፌሰር ስቅኤል ጋቢሳ በድብቅ ተገናኝተው መነጋገራቸው በራሱ አንዱ ማረጋገጫ ሊሆን ይችላል::
 የሁለቱ ሃይሎች ጥምረት ለአብይ አስተዳደር ለጊዜው ብርቱ ፈተና ይሆናል:: ኢትዮጵያን ለመበታተን ጋብቻ የፈፀሙት እነዚህ ሃይሎች የጫጉላ ጊዜ ላይ ናቸው::በሀገሪቱ ላይ የጥፋት ሰይፋቸውን በመሰንዘር እልቂትን እያዘጋጁ ለመሆናቸው ከጥርጣሬ ያለፈ መሬት ላይ ያለ ሀቅ ሆኗል::
በነገራችን ላይ የዚሁ ፅንፈኛ ቡድን መሪ በሳሪስና መርካቶ 43 ሰዎች ተገድለውብናል: ዝም ያልነው ሀገር እንዳይበጣበጥ ብለን ነው ሲል ሰማሁት ልበል? 43 ሰዎች ተገድለው ፖሊስ እንዴት ዝም አለ? በዚህ ጉዳይ ላይ ከፌደራል ፖሊስ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባዋል:: ምንም በሌለበት: አንድ አስክሬን ባልታየበት 43 ሰዎች ተገድለውብናል የሚለው መግለጫ በመርካቶና ሳሪስ አከባቢዎች ጥቃት ለመፈፀም ተዶልቷል ለማለት የሚያስገድደን ነው::
በሀሳብ ተሟግቶ በሰላማዊ መንገድ እና በምርጫ ካርድ የያዙትን ጭፍን ዓላማ እንደማያሳኩ ስለሚያውቁ ነው “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው” በሚል ስትራቴጂ ከአራጆቻቸው ጋር ጋብቻ የፈፀሙት። ዋናው በጊዜ መታወቁ ነው ከዛ ባለፈ ከዚህ በኋላ የትም አይደርሱም።
 በነገራችን ላይ ሲዳማ አከባቢም እየሄዱ የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና ከአብይ መንግስት ጋር ሆድና ጀርባ እንዲሆን ከዞኑ ካድሬዎች ጋር እየተገናኙ ማደራጀት ጀምሯል። “ኤጄቶ” በሚል ስም ወጣቱን ለማደራጀት ጥረት እያደረጉ ነው።
 (ፎቶግራፉን ከዘሀበሻ ላይ ያገኘሁት ነው:: የህወሀቱ ጌታቸው ረዳና የአክራሪው ቡድን አባል ህዝቄል ገቢሳ የሚታዩበት ነው)
Filed in: Amharic