>
5:13 pm - Thursday April 20, 5161

የካሮት ጊዜ አልቆ የዱላው ሲመጣ ለአሸናፊው ውሸቱ ሁሉ እውነት  ሆኖ ይነገርለታል!!! (የሽሀሳብ አበራ)

የካሮት ጊዜ አልቆ የዱላው ሲመጣ ለአሸናፊው ውሸቱ ሁሉ እውነት  ሆኖ ይነገርለታል!!!
የሽሀሳብ አበራ
ትህነግ የተነሳበትን ዓላማ ከማሳካት አንፃር  ስኬታማ ፓርቲ ነው፡፡  ከ 6 ሚሊየን ህዝብ ወጥቶ ቀሪውን  የ 94 ሚሊየን ህዝብ ወኪል በራሱ አምሳል መርጦ እንደ እንግሊዝ በእጅ አዙር መርቷል፡፡ የአማራ እና የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች እርስ በእርስ ባለፈ ትርክት ሲጠላለፉ ትህነግ ለሁለቱ ዳኛ ሆኖ የስልጣን ዘመኑን አርዝሟል፡፡ ሁለቱን ህዝቦች በማቃረን ወንበሩን አስፍቷል፡፡ትህነግ በሴራ የተካነ የፖለቲካ ፓርቲ ነው፡፡  አሻንጉሊት  ድርጅት ከመፍጠር ጀምሮ አክራሪ የኦነግ ብሄርተኛ ተፈጥሮ  ከሌላው ብሄር ጋር እንዲጣላ ሰርቶም ተሳክቶለታል፡፡የትህነግ  በቁጥር አናሳ ከሆነ ህዝብ ስለመጣ ዲሞክራሲ አሸናፊ አያደርገውም፡፡ስለማያደርገው በግጭቶች እየነገደ ያተርፋል፡፡
 …
ትህነግ በኮሚኒስታዊ እሳቤ አድጎ ታላቋን ትግራይ ሊመሰርት እሳቤ ነበረው፡፡ነገር ግን ትግራይን አልገነጠለም፡፡ ከዓላማው አንፃር ትህነግ ሲበዛ ሩህሩህ እና ደግ ነው፡፡
 …
ትህነግ ለተነሳበት ዓላማ ታምኖ ነገም ዛሬም ይሰራል፡፡ ትህነግ ፖለቲካው ላይ ገናና ባይሆን እንኳን ማጣላቱን እና ማተራመሱን አንዱ የህልውና ጉዳይ አድርጎ ይወስዳል፡፡ትህነግ ለዓላማው ታማኝ ፓርቲ ነውና፡፡
 …
የበዛ ህዝብ እና ሃብት የነበረው ብአዴን ለትንሹ ትህነግ አድሮ ኖረ፡፡ ትህነግ ዓላማዋን አስፈፀመችበትም፡፡ በብአዴን እንጂ በትህነግ አይፈረድም፡፡ ትህነግ የሃይማኖት ድርጅት ስላልሆነ ከራሱ በላይ ሌላው እንዲጠቀም ግድ አይለውም፡፡በዚህም  አይፈረድበትም፡፡ አነሳሱን አሳይቶ ነው የጀመረው፡፡
 …
እነ ጃዋር ለኦሮሚያ  ያልሆነች ለኢትዮጵያ  ብትወድቅ ብትነሳ አይመለከታቸውም፡፡ይህ የአደባባይ  መርሆቸው ነው፡፡ ከፌዴራል ያለ ኦህዴድም ቢሆንም ከሃገሪቱ ይልቅ ኦሮሚያን ማስቀደሙ አይቀርም፡፡ብሄርተኝነት ለራስ ማድላት ነውና፡፡የኦሮሞ ብሄርተኝነት ከ 400 ዓመት በፊትም በገዳ ስራዓት ነበረ፡፡በመደራጀት ኦሮሞዎች አርዓያ ናቸው፡፡መደራጀት ባህላቸው እና ታሪካቸው ነው፡፡ይሄን አስቀጥለው የፖለቲካ ማህበረሰብ ገንብተዋል፡፡
 …
በዚሁ ሁሉ ሂደት ውስጥ  የአማራ ችግሩ ያለው  የፖለቲካ ሃይሎችን ፍላጎት እና ዓላማ ተንትኖ ራስን ሆኖ  መቆም ላይ ነው፡፡
 …
ደግ ሁንልኝ ስላልከው ደግ የሚሆን ፖለቲካ የለም፡፡ ህግ፣ ስራዓት እና እኩልነት የሚረጋገጠው በማሸነፍ ነው፡፡
 …
ስለዚህ ማዶ ሂደን  ትክክል ነው ያሉትን ዓላማቸውን ከምንኮንነን የራሳችን ዓላማ መሬት ላይ መስራት የተሻለ አማራጭ ነው፡፡
 ወዲያ እና  ወዲህ ሆኖ እነሱ በሰሩት እኛ አጀንዳ ተቀብለን መራኮት ብዙ አያስጉዝም፡፡
  …
የአማራ ብሄርተኝነት ፖለቲካው ሞቀም ቀዘቀዘም ለአማራ ብሎም ለኢትዮጵያ  አስፈላጊ ነው፡፡ስለሆነም ብሄርተኝነቱን ወደ ተቋም መቀየር ያስፈልጋል፡፡ብሄርተኝነቱ ተቋም ከሆነ  ለማዶው ሁኔታ ሁሉ ምላሽ ይሰጣል፡፡ታክቲካል እና ስትራቴጂክ አጋር  ይፈለጋል፡፡
 ….
የአማራ ወጣቶች ማህበር፣ሌሎች አማራዊ የሲቪክ አደረጃጅቶች በፍጥነት  አድገው መመስረት ይኖርባቸዋል፡፡ ከኢህአዴግ  ጉባዔ በኃላ መንገዱ ይጠባል፡፡ግንባሩ አድርግ ያለውን ብቻ ማድረግ ህጋዊ እውቅና ይሰጠዋል፡፡
 …
የካሮቱ ጊዜ አልቆ የዱላው ጊዜ መምጣቱ አይቀርም፡፡ carrot and stick approach  is a main manfisteation of  political procedure.
 ካሮቱ ሳያልቅ የፖለቲካ እና የማህበራዊ የውሃ ልክ ካልተገነባ ትናንት ዛሬን ቀድሞት ነገ ይመጣል፡፡ ውስጣዊ አንድነት ከታከመ እና መሰረቱን  ከተሰራ ውጫዊው  በመደራደር ይፈታል፡፡ ፖለቲካ ሃይል ያለው እውነት አለው እንዲል ማካቬሊ፡፡የፖለቲካ ሃይልን እና ሱታፌን(participation) ማሳደግ ትርፍ ስራ አይደለም፡፡
 …
ህግ እና እውነት የአሸናፊዎች  ብቻ ናቸው፡፡ በተመድ ስብሰባ 150 ሃገር ተሰብስቦ  ፣149 ደግፎ አሜሪካ ብቻ ከተቃዎመች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ግን ደግሞ እኮ አሜሪካ የዲሞክራሲ አናት ነኝ ትላለች፡፡ብትልም ያምርባታል፡፡ጠንካራ እና አሸናፊ ሁሉ ውሸቱ እውነት፣ክፋቱ ሁሉ ደግ ሆኖ ይወራለታል፡፡
 …
በጥቅሉ ዓለም ያሸናፊዎች ብቻ ናት!! አሸናፊ እንድንሆን የአማራ ብሄርተኝነትን ወደ ተቋም ቀይሮ፣መጠቀም  ተገቢ ብቻ ሳይሆን የሃገሪቱ ሁኔታ ያስገድዳል፡፡
Filed in: Amharic