>
10:11 am - Saturday December 4, 2021

ዱቢ ሚላ - ጃ-ዋር (ዳንኤል ገዛህኝ)

ዱቢ ሚላ – ጃ-ዋር
ዳንኤል ገዛህኝ
አይነ-ስውሩ ሼክ በመባል ይታውቃሉ ሼክ ኦማር አብዱራህማን በ1997 የሉክሶር እልቂት እንደዚሁም ኒውዮርክን በአንድ ጀምበር በከፍተኛ የቦንብ ጥቃት ለማሽመድመድ በማሰብ ከፍተኛ የሽብር ጥቃት አቀነባባሪነት Master Mind ተከሰው በእድሜ ልክ ፍረደኛነት በኖርዝ ካሮላይና እስር ቤት ቆይተው ባለፈው 2017 ፌብሪዋሪ 18 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
የኒው ዮርክ ነዋሪ የነበሩት አይነስውሩ ሼክ …ሼክ ኦማር አብዱራህማን በ1993 የአለም የንግድ ተቁዋም የቦንብ ፍንዳታ አቀነባብረዋል። የአለም የንግድ ተቁዋም እና እምብርት የሆነችዋን ኒውዮርክን ከዳር እስከዳር በከፍተኛ የቦንብ ፍንዳታ በማውደም ለማሽመድመድ አቅደው ውጥናቸው ከሽፎባቸዋል። ይሁን እና ሼኩ በቁጥጥር እንደዋሉ ነበር የታይም ሜጋዝን አዘጋጅ የሽብር ጥቃቱን ምክንያት አንድ ጥያቄ የጠየቃቸው…
ለምን ይህንን የሽብር ጥቃት እብዳሰቡ ጥያቄ ሲሰነዝርላቸው…
እሳቸውም ሲመልሱ ምላሻቸውን በአንድ ቃል ነው ያጠናቀቁት… “ፍቅር ያሳውራል” ነበር ያሉት ማለትም ላመንክበት አላማ አይንህ ብቻ አይደለም ልብህን ይታወራል አይኖችህ እስኪጠፉ በፍቅር ትታወራለህ ነበር ያሉት። እርግጥም ሼኩ የአል ጀማአ አል ኢስላሚያ መሪ ነበሩ በኒው ዮርክ ደግሞ ከተወለዱባት እና ካደጉባት ግብጽ ተሰደው በጥገኝነት በአሜሪካ ኒውዮርክ  ይኖሩ ነበር ሆኖም ለሚወዱት እስልምና እምነት ሲሉ ማለትም በእርሳቸው አመለካከት የእስላም ጠላት ናት የሚሉዋትን አሜሪካንን ለማውደም የሽብር ጥቃት አቀነባበሩ እናም ለምን ሲባሉ “ፍቅር ያስልውራል” አሉ።
አላማ ለባለቤቱ ለማንም ቅዱስ ነው። ነገር ግን ለራስ ብቻ መልካም የሆነን ነገር …ነገር ግን ሌሎችን የሚጎዳ ተግባር በምንም መልኩ ቅዱስ ተግባር ሊሆን አይገባም።
በኢትዮጵያ የፓለቲካ የነጻነት ትግል ጉዞ ውስጥ ትልቁን መስዋእትነት የከፈሉ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ያለፉበት ጉዞ በእውነት እና በሀቅ…በትክክለኛ የነጻነት ጥያቄ ላይ የተመሰረተ እንደነበር ታሪካቸው እምልኝ ምስክር ነው።
በምንም መልኩ እነዚያ ታጋዮች ዛሬ ዛሬ እየሰማን እንዳለው “ኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ትውጥል…” Ethiopia Out of Oromiya ቅስቀሳ ጋር በምንም መልኩ የሚግናኝ አይደለም። የኦሮሞዎች የፓለቲካ ችግር እንደሌላው ብሄር ሁሉ የነጻነት ችግር…የሀብት ክፍፍል እኩልነት ችግር…በመረጠው መሪ ያለመመራት ችግር ወዘተርፈ ዘርፈ ችግር እንጅ አሁን እንድመጡት አዳዲስ ለብቻ ሀገር ሆኖ የመውጣት ጥያቄ ችግር አይደለም።
የኢጆሌ ባሌ አመጽ ጥይልቄው የእኩልነት እንጂ Great Oromiya የሚል ነገር አልነበረውም።አገሪ ቱሉ…ጀነራል ታደስ ብሩ… ማሞ መዘምር…ሀይሌ ፊዳ…ባሮ ቱምሳ…በርካትልዎቹ በተይ ከአማራ ብሄር ተወላጆች ጋር ለኢትዮጵያ አንድነት በአንድ ኢትዮጵያ ፍቅር ልክፍት ነው መስዋእትነት የከፈሉት።
ዛሬ የኦሮሞ ትግል ማጠንጠኛው የኦሮሞ ህዝብ ለረጅም አመታት ከከፍተኛ የሀገር አስተዳደር ስልጣን ተገፍተው እንደቆዩ ተደርጎዋል እየተባለ ማቀንቀን ነው። ሆኖም እውነታውን ታሪክን የሁዋሊት መመልከት ከተቻለ ኦሮሞዎች ከንጉሱ አገዛዝ እስከ ደርጉ ስርአት ድረስ አሉ የተባሉ የስልጣን እርከኖችን ይዘው መቆየታችውን ነው።
ይሁን እንጅ በገንዘብ አቅም በሚድያ ሞኖፓል ራሳቸው ያደራጁ አክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ባለሀብቶች ዘመናት የተሻገረውን የሰፊው ኦሮሞ ህዝብን ትግል በዝንኝነት ጦስ ማርከው ጠምዝዘው በእጃቸው አስግፕብተውታል። የኦሮሞ ህዝብ ትግል እንዴት ከምርኮ ሊወጣ ይችላል ? ይህ በእጅጉ ፈታኝ ጥያቄ ነው።
ጃዋር መሀመድ ምንም አይነት የፓለቲካ ፓርቲ የለውም ነገር  እንደ አሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ያሉት ሚድያዎች ያለ ሌላ ድምጽ እና አማራጭ በብቸኝነት “ወጣቱ የፓለቲካ ተንታኝ”  ጎልቶ እና ገዝፎ እንዲወጣ እድል ፈጥሮለታል። በዚሁ እውቅና ላይ ምንም የኤዲቶርያል ፓሊሱ እና  የኤዲቶርያል አባላት የሌለው ጥያቄ አቅራቢ እና የአየር ላይ ተዋናይ ዜና አንባብያን በመቅጠር  omn እዚህ ደርሶዋል። የጃዋር እና የሚድያው ብሎም ኦሮምያን የመገንጠል አጀንዳው እሱን ከመሰለ አቁዋም ጋር ያሉ ተንታኞችን በመጋበዝ በተጠና እና በተደራጀ ሁኔታ ባለፉት ሁለት አመታት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቶዋል ። የ ኦሮምያን ልዩ ሰራዊት በቲዮሪ ከማዋቀር እስከ ኦሮምያ መንግስት ምስረታ እስከ መንግስታዊ አወቅልቀር። እርግጥ ነው በሚድያ በገሀድ ከሚደረገው ቅስቀሳ ባሻገር የኦሮሚያ መንግስት ቻርተር መረቀቁም የሚታውቅ ነበር ሆኖም ጉዳዩን ማንኛውም የኢትዮጵያዊነት ትግል አቀንቃኝ ሀይል አደገኛንቱን ገፍቶ አልሄደበትም እንጅ።
በጃዋር የፓለቲካ ማጠንጠኛ በርካታዎቹ የኦሮሞ ትግል በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ተባባሪ ሀይሎች ተጠምዝዘው ከአክራሪ መርሁ ውስጥ ሳይወዱ በግድ ምርኮኛ ሆነዋል። ልጅ ያቦካው እንዱሉ የጃዋር ንግግሮች እና ትንታኔዎች ሙሉ በሆነ መልኩ አወዛጋቢ የሚጋጬም ናቸው።
ጃዋር በአብዛኛው የተጠና ፓሊሲ የለውም ግን ድብቅ አጅንዳ አለው እሱ በተወለደበት አካባቢ ከእሱ እምነት እና ፍላጎት ውጭ ማንም እንደማይሆን እሆናለሁ ካለ በሜንጫ አንገት እንደሚቀላ ተናግሮዋል ፍቅር እውር ሲያደርግ እንዲህ አይደል ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ እንደሚለቀልቅ።እናም የጃዋር ያልተጠና ጉዞ መዘዙ ብዙ…ብዙ ገና ብዙ ያስከፍላል እሱም ይከፍላል …ዛሬ ደግሞ የአዛኝ ቅቤ አንጉዋች የመፈንቅለ መንግስት Cudetat የጉድ ሀገር ገንፎ።
Filed in: Amharic