>

 ጉልበት ያላቸው መስለው ለመታየት ቢሞክሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ሌላ ነው!!! (ፋሲል የኔአለም)

 ጉልበት ያላቸው መስለው ለመታየት ቢሞክሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ሌላ ነው!!!
ፋሲል የኔአለም
 
* እውነት እላችሁዋለሁ፣ ፖለቲካቸው ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። ይህም መግለጫ ኪሳራን (bankruptcy) ከማወጃቸው በፊት ትርፍ የሚያስገኝልን አንድ ነገር እንሞክር ብለው የለቀቁት ነው።

እነ አቶ በቀለ ገርባ ባወጡት መግለጫ ዙሪያ ብዙ ማለት ይቻላል። ኢሳት ውስጥ የሚሰሩ የኦሮሞ ልጆች የኢሳትን አላማ ስለሚያውቁት ምስክርነቱን ለእነሱና ለታሪክ እተወዋለሁ። አንድ ነገር ግን ማለት እፈልጋለሁ። እነ በቀለ ገርባም ሆኑ የብሄር ድርጅቶች አይተውት በማያውቁት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል።

 

 እውነት እላችሁዋለሁ፣ ፖለቲካቸው ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። ይህም መግለጫ ኪሳራን (bankruptcy) ከማወጃቸው በፊት ትርፍ የሚያስገኝልን አንድ ነገር እንሞክር ብለው የለቀቁት ነው። አሁን ጉልበት ያላቸው መስለው ለመታየት ቢሞክሩም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ሌላ ነው። በኢሳት ላይ የጀመሩት ዘመቻ እየተመናመነ የመጣውን ድጋፊያቸውን መልሰው ለማሰባሰብ ከሚጠቀሙበት ስልት አንዱ መሆኑን በመረዳት፣ ለዜጎች መብት የሚታገሉ ሃይሎች ሁሉ በእነሱ ወጥመድ ውስጥ ላለመግባት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው።
 እነሱ የሚፈልጉት በእነሱ የውጊያ መስመር ገብተን እንድንፋለማቸው ነው።  እነሱ በመረጡልን ሳይሆን እኛ በመረጥነው መንገድ እንዲገቡ የራሳችንን የእውነት መንገድ ብቻ መከተል አለብን። የእኛ መንገድ የአንድነት፣ የፍቅር፣ የመደመርና የዲሞክራሲ መንገድ መሆኑን ለህዝቡ ማስረዳት መቀጠል አለብን፤ እንዲህ ስናደርግ መክሰራቸውን አምነው ተቀብለው  ከገበያው እንዲወጡ ማድረግ እንችላለን።
 እነሱ በቁልቁለቱ ላይ ለመጓዝ መርጠዋል። ይቅናቸው። እኛ ግን ከያዝነው የከፍታ መንገድ ላለመውረድ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን።
Filed in: Amharic