>

የብአዴን ሪፎርሚስቶች  አሸንፈው መውጣት ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ወሳኝ ነው (ቾምቤ ተሾመ)

የብአዴን ሪፎርሚስቶች  አሸንፈው መውጣት ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ወሳኝ ነው

ቾምቤ ተሾመ

የብአዴን ሪፎርሚስቶች  አሸንፈው መውጣት ለኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሂደት ወሳኝ ነው  በቅርቡ በሚካሄደው የብእዴን ስብሰባ ድርጅቱ ከወያኔ ተላላኪዎች አንጽቶ መውጣት እጅግ በጣም ወሳኝ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ወያኔ የትግራይን ጥቅም ለማስጠበቅ ከአካባቢው አልፎ ሌሎች  አስተዳደራዊ ክልሎች ውስጥ ገንዘቡንና የነበረ መዋቅሩን በመጠቀም የመሃከላዊ መንግስትን ለማዳከም ከአክራሪ የኦሮሞ አክቲቬስቶችን በመመልመልና በገንዘብ በመርዳት ወደ ስልጣን ለመመለስ ካለዚያም ሀገሪቷ እረፍት አግኘታ ወያኔ የሰራውን
ወንጀልና ዘረፋ እንዳታግልጥ ያለ የሌለ ጉልበቱን  እየተጠቀመ ነው፡፡

የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ጠላቱን ና ወዳጁም በመለየት ስለኢትዮጵያ ጉዞ ያለውን ርአይ በግልጽ አስቀምጣል፤ የሱማሌ ክልልም የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ተገቢውን እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፤ በአሁኑ ሰአት ሁለተኛ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአማራው ህዝብ እየመራ ያለው የተደራጀና እራሱን መከላከል ችሎታና አቅም ያለው ብአዴን ግን በውስጡ በተሰገሰጉ የወያኔ ተላላኪዎች ተተብትቦ ታሪክ የጣለበትን ሃላፊነት መወጣት አልቻለም፡፡

ቆራጥ እርምጃ ወስዶ የሚወገዱትን ልክ እንደ የኦሮሞ ዲሞክራቲ ፓርቲ እንደመሰናበትና  ጊዜው  ሚጠይቀውን አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ አቅቶት ፍራ ተባ ሲል ፤በሂስና ግለ ሂስ በሚባል የወያኔ ትብተባ ውስጥ ገብቶ ጊዜውን ሲያቃጥል ፤የኢትዮጵያ ፓለቲካ ሚናውን መጫወት አልቻለም ፡፡ ስብሳባው መጥርያ ምልከቱ ሳይቀር ድሮ ወያኔ የሰጠውን ኩታ ለብሶ ለመሰብሰብ ሰጣ ገባ ይላል፡፡ እነ በረከት የአማራ ስነ ልቦናን እንደ ወያኔ ተወካይ ሆነው  ሲያጠቁት እንዳልከረሙ በቅጡ የሰሩትን ጸረ አማራ ጸረ ኢትዮጵያ ስራ እንካን በቅጡ መኮነን ያልቻለ ድርጅት ነው ፤ ይህንን የተዝለፈለፈ አቋሙን  ቆሮጦ መጣል የነበረበት ጊዜ ዛሬ ሳይሆን አልፎ ከርሟል፤  ዞሬ ወያኔ የልብ ልብ እንደገና አዉጥቶ ትምከህተኝችን ( አማራን) እዋጋለሁ እያለ
እንደገና እያቅራራ በሚገኝበ ውቅት ብአዴን ከነበረከትና ከመሳስሉት የወያኔ ተላላኪዎች ጋር በተልባ ላይ የሚደንስበት ወቅት አይደለም፡፡

በአሁኑ ሰአት ወያኔና ጸረ ዶ/ር አብይ የኦሮሞ አክራሪዎች በጋሃድ  አንድ መስመር ይዘው ጸረ – ኢትዮጵያ ስራቸውን በተቀነባበረ መንገድ እያካሄዱ እንደሆነ ለሁሉም  ግልጽ ነው፤ ነገር ግን ብአዴን የሚገባውን ያህል ድጋፋዊ ተጸእኖ መፍጠር እስካሁን አልቻለም ፤ ምክያቱም ቤቱን አጽድቶ በቶሎ መገኝት የሚገባው ቦታ ላይ
መገኝት ባለመቻሉ  ነው;፤ ብአዴን ባቡሩ ከሄደ በኋላ ደረስኩ ቢል ምንም ትርጉም የለውም ነገር ግን የሚወክለው ህዝብን ያህል ሀላፊነትን መውሰድና ለኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ማቅናት የህዝቦች አንድነት አሁን የገጠመውን ችግሮች አልፎ እንዲጎለብት ታሪካዊ ህላፊነቱን መወጣት ግዴታው ነው፡፡

Filed in: Amharic