>

የህወሀትና ኦነግ "ስትራጄያዊ"አጋርነት!?! (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

የህወሀትና ኦነግ “ስትራጄያዊ”አጋርነት!?!
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፈጣንና ተለዋዋጭ ሂደት ውስጥ የኦነግና የህወሃት አሮጌ ያልተቀደሰ ጋብቻ የጥፋት መርዙን አዝሎ እንደ አዲስ ብቅ ብሉዋል።
ግንኙነታቸውን ስትራቴጂያዊ ይበሉት እንጅ ጠጋ ብለን ስናየው የጠላቴ ጠላት የሚባለው ስልታዊ አጋርነት ነው።ይህም እነሱ ትህምክት የሚሉት በግልፅ አጠራር አማራውና በኢትዮጵያዊ ዜግነት ራሱን የሚገልፀውን የህብረተሰብ ክፍል ነው።የግንኙነታቸው የጋራ አላማ ኦነግ ትልቅ ሀገር ፍለጋ ህወሃት ደግሞ ከፋፎሎና አዳክሞ መግዛት ነው።ህወሃት አጠገቡ ያለውን በባህል በእምነት በህዝብ ትስስር በስነ ምህዳር የሚቀርበውን አማራ ጠላት አድርጎ እንዴት ኦነግን ስትራቴጂያዊ አጋር ሊያደርግ ይችላል? በሌላ በኩል ኦነግ በበህል በእምነት  በህዝብ ትስስር በስነምህዳር በንግድ  አጠገቡ ያለውን አመራ ጠላት አድርጎ እንዴት ሀወሃትን ስትራቴጅያዊ አጋሬ ነው ሊል ይችላል? አሁን ትግሉ በደረሰበት የእድገት ደረጃ ህወሃት ለኦነግ ህልም ማርኪያ የሚሆን ጉልበት መስጠት የሚችል አይመስለኝም።ኦነግም የምኞት ባሪያ ሆኖ ለህወሃት ከፋፍሎ የመግዛት ህልም መጠቀሚያ የሚሆን አይመስለኝም።ሁለቱም ጠላቴ የሚሉትን አማራና ትህምክት እንደዳዊት እየደገሙ ሀገር ከመረበሽ ባለፈ ወደስልጣን የሚያደረስ ግልፅ የጋራ ሃሳብ የላቸውም። የኢትዮጵያ ህዝብ በግልፅ ካልታገላቸው ለስልጣን ባይበቁም ህውከት ለመፍጠር የሚያስችል ቁመና አላቸው።
Filed in: Amharic