>

ጃዋርና ህወሓቶች ደህና ሰንብቱ!!! (ሀብታሙ አያሌው) 

ጃዋርና ህወሓቶች ደህና ሰንብቱ!!!
ሀብታሙ አያሌው 
ከውድድር ውጭ የሆኑት የቀድሞው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም ከአሁን በኋላ በመንግስት የስራ ኃላፊነት እንደማይቀመጡ ተወስኗል፡፡
ፋና በዜና እወጃው የአቶ ደመቀን ከኀላፊነት የመልቀቅ ጥያቄ የአዴፓ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ተቀብሎ ለጉባኤው ማቅረቡን የዘገበበትን ገፅ  በመለጠፍ ጀዋርና የህወሓት ጀሌዎች በፊስ ቡክ እልልታ ጀምረው ነበር።  እኛም በበኩላችን በዚህ አደገኛ ወቅት የአቶ ደመቀ ከኃላፊነት መነሳት የሚያስከትለውን አደጋ እና የለውጥ ሂደቱ ዋነኛው ሞተር መሆኑ እየታወቀ አቶ ደመቀ ለመልቀቅ ቢጠይቁም ማዕከላዊ ኮሚቴውም ሆነ ህዝቡ ሊፈቅድ እንደማይገባ ገልፀን ሙግታችንን ቀጠልን።
የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴና ጠቅላላ ጉባኤውም የሰፊውን ህዝብ ድምፅ ችላ አላለውም። አቶ ደመቀም ህዝቡ እና ፓርቲያቸውን አድምጠው ታዛዥ ነኝ ሲሉ በኃላፊነታቸው ለመቀጠል ተስማምተዋል።
አቶ ደመቀ መኮንን በክብር ቢሰናበቱ ተብሎ የቀረበውን ሀሳብ ጉባኤው በመቃወሙ ነው ባሉበት እንዲቀጥሉ የተደረገው፡፡
ብአዴን ለማዕካዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ባይወዳደሩ ያላቸውን 12 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የቀረበውን መነሻ ተቀብሎ አጽድቋል።
  ጀዋርና የህወሓት ጀሌዎች ደህና ሰንብቱ። ለጊዜው ምኞታችሁ  መክኗል። አቶ ደመቀ መኮንን እና ፓርቲያቸው የህዝብ ድምፅ ስላከበራችሁ እናመሰግናለን።
ተያያዥነት ያላቸው ተጨማሪ መረጃዎች ከአማራ ማስ ሚድያ
ለትምህርት የሚላኩ እና አሁን በትምህርት ላይ የሚገኙና የተሰናበቱ:- 
• አቶ ዓለምነው መኮንን
• አቶ ለገሰ ቱሉ
• አቶ ጌታቸው ጀምበር
• አቶ ኢብራሂም ሙሀመድ
• አቶ ደሳለኝ አምባው እና
• ወይዘሮ ባንቺ ይርጋ መለሰን ባይወዳደሩ ብሎ መነሻ አቅርቧል፡፡
በክብር የተሰናበቱ፡-
• አቶ ከበደ ጫኔ
• አቶ መኮንን ያለውምወሰን
• ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው እና
• አቶ ጌታቸው አምባየን በክብር ቢሰናበቱ ብሎ አቅርቧል፡፡
በአምባሳደርነት እያገለገሉ ያሉ እና የተሰናበቱ፡-
• አቶ ካሳ ተክለብርሀንና
• ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰን ከውድድሩ ውጭ ቢሆኑ ብሎ  መነሻ አጸድቋል፡፡
ከውድድር ውጭ የሆኑት የቀድሞው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም ከአሁን በኋላ በመንግስት የስራ ኃላፊነት እንደማይቀመጡ ተወስኗል፡፡ ጉባኤው ዛሬ ጠዋት 1፡30 የተሰየመ ሲሆን 65 አባላት ያሉትን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
በተመሳሳይ:-
 
ደኢህዴን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን፣  አቶ ሽፈራው ሽጉጤን፣ አቶ ሲራጅ ፈጌሳን ጨምሮ 23 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላቱን በክብር አሰናብቷል። ሌሎች ሶስት አባላቱን በእግድ እንዲቆዩ ወስኗል
Filed in: Amharic