>
5:13 pm - Saturday April 20, 0137

"ከአሁን በኋላ ማንም የማንም ሎሌ አይሆንም!"  (የደህዴን ሊቀመንበር ወይዘሮ ሙፈሪሀት ካሚል!)

“ከአሁን በኋላ ማንም የማንም ሎሌ አይሆንም!”
 የደህዴን ሊቀመንበር ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪሀት ካሚል!
 
 <<ህዝብ ቃላችንን ጠግቧል!  የሚፈልገው ተግባራችንን ነው!!!>>

 

ክቡራን የአረንጓዴዋ መልካ-ምድር ተወካዮች፤ ዛሬ በጆሮዎቹ ሳይሆን በልባቹህ እንድትሰሙኝ አጥብቄ እማፀናለሁ !
ክቡራን ወንድምና እህቶቼ አንዱ ብሄር ካንዱ ብሔር ካልተቃቀፈ እንወድቃለን አሊያም የተደራጁ ስለኛ ሰዉነት ዜግነት ግድ የሌላቸዉ ግለሰቦች አሻንጉሊት እንሆናለን !!!
ክቡራን ህይወት ትስስሮሽ ናት! ማንም ሰዉ ነፃ አይደለም፤ ለላንቲካ ቅፅበት ቢሆን እንኳን ብቻችሁን መሆን አትችሉም የመላዉ ኢትዮጵያ ሁለንተና ያስፈልጋቹሀል እኛም ለነሱ በጣም እናስፈልጋቸዋለን ሌላዉ ቢቀር ሰሜኑም ምስራቁም ምዕራቡም የሚተነፍሰዉ አየር በኛ አረንጓዴ መልካዓም ምድር ስጦታ ነዉ !!
እርስ በእርሳችን እንተቃቀፍ ስል እንደከዚህ ቀደሙ ሎሌና ጌታ እንሁን እያልኩኝ አይደለም ከአሁን በኋላ ማንም የማንም አሽከር አይሆንም!
ሁለት አይነት ትስስር አለ ከስርና ከላይ አንዱ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ እኩል ቆሞ መደጋገፍ ነዉ!
የመጀመሪያዉ ሎሌና ጌታነት ነዉ ባገራችን ለዘመናት ይህ አይነቱ የጥገኝነት ገፅታ ሲሰራበት ነበር መልኩን ቀይሮ ዛሬም ድረስ ቀጥሎ ነበር አንዳችን ለአንዳችን ጥገኛ ሆነን ነበር፤ አንዱ አንዱን ይበዘብዛል፤ አንዱ አንዱን አጥንት እየቆጠረ ለመቆጣጠር ይጣጣራል፤ አንዱ የአንዱ ጌታ ለመሆን ይሞክራል፤ አንዱ አንዱን ከሰብዓዊነት ደረጃ አዉርዶ ወደ እቃና ሸቀጥነት ደረጃ አኮስሶ ለመግዛት ይፈልጋል !!
ዘጠና ዘጠኝ ከመቶዉ የፖለቲካ ሊሂቃኑ ፍላጎት ይኸዉ ነዉ። ለዛም ነዉ የገነት ኦር የጀነትን ኬላ መክፈት ያልቻልነዉ፤ ለዛም ነዉ በሀገራችን የሲኦል (የጀሀነም) ቁልፍ ሞልቶ የተትረፈረፈዉ!
ክቡራን ሁለተኛዉን የእኩልነት የፍቅር ትስስር ለመፍጠር አመለካከታችን ላይ ስር ነቀል ለዉጥ ለማምጣት አዎንታዊ ሞራል እንገንባ፤ ይህን ማድረግ ከቻለን የመንግስተ ሰማያት መባረክ በረከት ወደ ምድራችን ይወርዳል።
አንዱ ብሔር ለአንዱ ብሔር ጌታም ሎሌም ሳይሆን በእኩልነትና በነፃነት እንዲሁም በፍፁማዊ ስምምነት አንዳችን የአንዳችንን ትንፋሽ እየተመገብን በሁለት መካከል ያሉ አንድ ነፍስ ሆነን ፍቅርና ሀሴትን ለመጪዉ ትዉልድ እናዉርስ ይህ ብቻ ነዉ እኩልነት፣ ዴሞክራሲ፣ ነፃነት ተብሎ የሚጠራዉ።
የመጀመሪያዉ ቅጥፈትና የቃላት ጫወታ ነዉ!!!
ሰዉ ትልቅ ፍጥረት ነዉ ሸቀጥ አይደለም፤ ስለሆነም የመጀመሪያዉን ትስስር እንቢ ብሏል እምቢታዉ ከአስተዋይነት ስሜት የመጣ ነዉ።
በሎሌና በጌታ የፖለቲካ ሲስተም መስማማትና እሺ ማለት ግን አስተዋይነት አይጠይቅም። እሺ
ካላቹህ ማንም ለምን? ብሎ አይጠይቃቹሁም።
ስለዚህ ምንም አይነት ምክንያት ወይንም ማስመሰያ ሀሳብ አያስፈልግም። እንቢኝ!!! ስትሉ ግን ለምን? የሚለዉ ጥያቄ መከተሉ አይቀርም።
ክቡራን እህትና ወንድሞቼ እዚህ ላይ ግን ማስተዋል ያለብን ነገር አለ የሁለተኛዉ የእኩልነትና የለዉጥ ጥሪ ህብርና ዉህደቱ እንዳይቀናጅ ያደረገዉም ነገር የንቁነት ጉዳይ ነዉ። ንቁነት ነፃነትን አጎናፅፏችዃል፤ ነፃነት ደግሞ እንቢ የማለትን ሀይል ይሰጣል ነገር ግን እሺታ ከሌለ ደግሞ ህብር ሊኖር አይችልም። ህብርና ዉህደት የሚገኘዉ በእሺታ ዉስጥ ብቻ ነዉ!!!
ክቡራን ፍፁማዊ ፍትህና ነፃነት የሚከሰተዉ የጌታና ሎሌ ሲስተሙን እምቢ! ባልን ቅፅበት የተሰማንን የነፃነት ደስታ ሁለተኛዉን የእኩልነት የለዉጥ ጥያቄ ያለምንም ማመንታትና ቅድመ ሁኔታ እሺ ማለት የቻልን ግዜ ብቻና ብቻ ነዉ !!!
እምቢታ ንቃት እንጂ ፋሽን አይደለም እንዳንድ ጨቅላዎች እዚና እዛ በእንቢታ እየተዝናኑ ነዉ! መላዉ ህይወታቹሁን በዚህ የእምቢታ ስካር ዉስጥ ከገፋቹሁማ ማደግ አቁማችኋል ማለት
ነዉ ሰከን ብለን የእምቢታ ግባችንን እናጢን !!!
ከቃል ባለፈ ለህዝባችን በተግባር የምንፈተንበት ስራ ሰርተን ማሳየት አለብን። ወቅቱ የአላማ አንድነት የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉንም የስሜት ህዋሳት መጠቀም የሚችል በንቁ አመራር የተገነባ ድርጅት ሊኖረን ግድ የሚልበት ወቅት ላይ ደርሰናል።
Filed in: Amharic