>
5:13 pm - Friday April 20, 4446

''ኦነግ ስምምነቱን አክብሮ ጦሩን በፍጥነት ወደ ካምፕ እንዲያስገባ በድጋሚ እንጠይቃለን!!! (አቶ አዲሱ አረጋ)

”ኦነግ ስምምነቱን አክብሮ ጦሩን በፍጥነት ወደ ካምፕ እንዲያስገባ በድጋሚ እንጠይቃለን!!!
አቶ አዲሱ አረጋ
ከኦነግ ሃይል ውጭ ታጥቀው እየተንቀሳቀሱ ያሉትም ትጥቃቸውን ፈተው ወደ መደበኛ ስራቸው መመለስ አለባቸው!!!”
 
ትላንት በወደቅንበት ቦታ ዛሬም መውደቅ አንፍልግም። ከዚህ በፊት የሃገራችን የዲሞክራሲ ሜዳ በመጥበቡ የሰላም ትግል ለማድረግ ምቹ ሁኔታ ስላልነበረ የተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎች የፓለቲካ አጀንዳቸውን ለማስፍጸም የትጥቅ ትግል ለማድረግ ተገደው ሲንቀሳቀሱ እንደቆዩ ይታወቃል።
ትውልድ በከፍለው መስዋትነት በባለፍው 5 ወራት እየታየ ባለው ለውጥ መንግስት በከፍተኛ ቁርጠኝነት ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው። በአሸባሪነት ስም ተሰይመው የነበሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ሚዲያዎች እና ግለሰቦች ስያሜያቸው ተነስቶ በነጻነት በሃገራቸው እንዲንቀሳቀሱ ተደርጎዋል።
የዲሞክራሲ ህግ እና ሰብአዊ መብት የሚያፍኑ ህጎች እንዲሰረዙ ወይም ተጣርተው እንዲሻሻሉ እቅጠጫ ተቀምጦ እየተሰራ ነው። ኦነግን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ወደ ሃገር ገብተው እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የዲሞክራሲ ሜዳ ለማስፋት የተወሰዱ እርምጃዎችን በትክክል ከተጠቀምንበት ከማንም በላይ ኦሮሞን የሚጠቅም ነው።
እየተወሰደ ያለው እርምጃ እንደ ሃገርም ሆነ እንደ ኦሮሞ የሚካሄደውን ፖለቲካ በሃሳብ በፉክክር እና ሰላም ላይ ብቻ የተመሰረተ ዘመናዊ ፖለቲካ እንዲኖር ያደርጋል። ስንናፍቅ የነበረውን ነጻነትም ይሰጠናል። ከዚህ ተቃራኒ ከቆምን ግን እንደ ትላንቱ ተመልሰን መውደቅ እና መዋረድ እንደምንችል መረሳት የለበትም።
ኦሮሞ በትግሉ የተፍጠረውን ምቹ ሁኔታ ተንከባክቦ በመጠቀም ፖለቲካውን ወደ ትክክለኛ ዲሞክራሲ ለማሸጋገር በአንድነት ሊቆም ይገባል። የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ወደ ሰላም ትግል ለመመለስ የወሰኑትም የትግል ዘዴያቸውን በፍጥነት ወደ ሰላም ትግል ማዞር አለባቸው። ከመንግስት ጋር የገቡትን ስምምነት በማክበር የጦር ሃይላቸውን በፍጥነት ወደ ተዘጋጀው ካምፕ ማስገባት አለባቸው።
የሰላም ትግል ለማድረግ ከወሰኑ ቦሃላ በሌላ በኩል በታጠቀ ሃይል በጫካ ውስጥ መንቀሳቀስ የለበትም። በዘመናዊ መንግስት ውስጥ የህግ የበላይነት ማስከበር እና የጦር መሳሪያዎችን መቆጣጠር የመንግስት ድርሻ ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይሄ ካልሆነ ሰላምን ለሚያደፍርሱ እና ህዝብን ለሚያሸብሩ መንገድ ይከፍታል። አሁን እያየን ያለነውም ይሄንኑ ነው።
እንደሚታወቀው መስከረም 16,2011 በኦነግ ስም በታጠቁ ሃይሎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ወረዳ በተፈጸመው ግድያ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አከባቢ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ከአከባቢያቸው ንብረታቸውን ጥለው ወደ ምእራብ ወለጋ ባሃ አናሌ፣ሳሲጋ፣ ሊሙ፣ ሊሙ ሃሮ እና ዲጋ ዞን እየሸሹ ነው።
የፖለቲካ ፓርቲዎች በጊዜ መጨረስ ያለባቸውን ጉዳይ ባለመጨረሳቸው ባለመደማመጣቸው ክፍተት እና ስህተት በመፍጠር ህዝቦች እንዲሞቱ እንዲፍናቀሉ እና መብታቸው እንዲነካ ማድረግ የለባቸውም።
ኦሮሞ የፖለቲካ ልዩነቶችን በዘመናዊ መንገድ ማራመድ አቅቶት እንደ ትላንቱ እንዲተኩዋኮስ እንዲገዳደል እና ተመልሶ ባርነት ውስጥ እንዲወድቅ አንፍልግም።
ለዚህም በኦነግ ስም ታጥቀው በኦሮሚያ አንድ አንድ አከባቢ የአሚንቀሳቅሱትን በትእግስት እና በብስለት እያየን ነው።
ኦነግ የተደረሰውን ስምምነት አክብሮ ታጥቆ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ጦሩን በፍጥነት ወደተዘጋጀው ካምፕ እንዲያስገባ በድጋሚ እንጠይቃለን።
ከኦነግ ሃይል ውጭ ታጥቀው እየተንቀሳቀሱ ያሉትም ትጥቃቸውን ፈተው ወደ መደበኛ ስራቸው መመለስ አለባቸው።
አቶ አዲሱ አረጋ በኤፍ ቢ ገፃቸዉ ካሰፈሩት ተተረጎሞ የተወሰደ  ምንጭ:-  ዳዊት እንደሻው
Filed in: Amharic