>

ዶክተር አብይ መንግስትዎ ፈጥኖ እርምጃ ካልወሰደ ዳግም እልቂት ሊመጣ ነው!!! (ሀብታሙ አያሌው)

ዶክተር አብይ መንግስትዎ ፈጥኖ እርምጃ ካልወሰደ ዳግም እልቂት ሊመጣ ነው!!!
ሀብታሙ አያሌው
ጠርዝ የረገጠው ብሔርተኛው የህወሓት ቡድን ባለፉት 27 ዓመታት ዋነኛ የዘረፋ ማከሉ ከነበሩት ክልሎች አንዱ የጋምቤላ ክልል እንደ ነበረ ይታወቃል። ሌላውን ሁሉ ትተነው
  1 . 65 በመቶ የክልሉ መሬት በሜካናይዝድ
       የእርሻ ልማት ስም በህወሓት ሰዎች ቁጥጥር
       ስር መሆኑ ይታወቃል።
  2  . በተቆጣጠሩት መሬት ስም ከልማት ባንክ በብድር ስም
        የዘረፉት ገንዘብ 20 ቢሊዮን መድረሱ በይፋ
        በመንግስት ሚዲያ ከተገለፀ ገና ሁለተኛ ቀን ነው
 3 .  በሼህ አላሙዲ በኩል የሳውዲ ኢንቨስተር ተብለው
       የገቡት ከህወሓት ባለስልጣናት ጋር በጥቅም የተሳሰሩ
       አረቦች በክልሉ ያደረሱት በደል እና ዘረፋ ከማንም
       የተሰወረ አይደለም።
4 .  ህወሓት ለዘረፋው ማስፋፊያ ባቀናጀው ሴራ በአንድ ቀን ብቻ 400 ጋምቤላ ኢትዬጵያውያን  ኝዌሮች በነ ሳሞራ ዮኑስ መጨፍጨፋቸው በዓለም የሚታወቅ ነው …
      አሁን በልማት ባንክ የተፈፀመው ዘረፋ ሲጋለጥ እና ዘረፋውን ያስፈፀመው የባንኩ ኃላፊ የህወሓት ሹመኛ ከአገር ወጥቶ መሰወሩ በይፋ ሲነገር። በጌታቸው አሰፋ የሚመራው ቡድን ወንጀሉን ለመሸፈን እና የመጋለጡን አጀንዳ ለመቀልበስ በጋምቤላ እልቂት ለማድረስ ቅስቀሳ ጀምሯል። ለዚህም ዘረኝነትን በማምከን ሲራቸውን እያከሸፈ ያለውን ኦባንግ ሜቶን በመክሰስ ሴራቸውን እያጋጋሉ ነው።
ዶክተር አብይ መንግስትዎ ፈጥኖ እርምጃ ካልወሰደ ዳግም እልቂት ሊመጣ ነውና መቀሌ የመሸገውን ወንጀለኛ እና ዘራፊ ቡድን አንድ ቢሉት ጥሩ ነው። እነዚህን ሰዎች በማባበል ብዙ እርቀት መጓዝ አይቻልም ። መንግስት እነዚህ ቡድኖች ከአክራሪ ብሔርተኞች ጋር በስውር እየተቀናጁ  ወንጀላቸውን ለመሸፈን እና ያጡትን ስልጣን ለማስመለስ እልቂት ሲፈፅሙ መግለጫ እያወጣ በማውገዝ ማዘኑን አቁሞ የህግ የበላይነት ያስፍን።
Filed in: Amharic