>
1:58 am - Saturday December 10, 2022

በሐዋሳው ጉባኤ - ከበሮው በዝቷል! ጡሩምባው ጆሮ ያደነቁራል! ስብከቱ ያታክታል!!! (መሳይ መኮንን)

በሐዋሳው ጉባኤ – ከበሮው በዝቷል! ጡሩምባው ጆሮ ያደነቁራል! ስብከቱ ያታክታል!!!
መሳይ መኮንን
እየተካሄደ ባለው የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ በሰፊው የምለው ይኖረኛል። ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ተጨማሪና ሙሉዕ የሆነ ጉልበት ይሰጣል ብዬ የምጠብቀው ጉባዔ ነው።  እስከዚያው ግን ለውጥን የሚገፈትሩ፡ እንደተለመዱት ዓይነቶች የኢህአዴግ አታካችና ለዛ ያጡ ጉባዔዎች ያስተዋልኳቸው አንዳንድ ነገሮችን ላንሳ።
ከበሮው በዝቷል። ጡሩምባው ጆሮ ያደነቁራል። ስብከቱ ያታክታል። ከተሰራው በላይ ፕሮፖጋንዳው ሰማይ ደርሷል። እንደኮሚኒስት ቻይና ፓርቲ መድረክ ቲያትሩ አሰልቺ ነው። እንደቀደምቶቹ ጉባዔዎች ኢህአዴግን የኢትዮጵያ ብቸኛ፡ መልኮታዊ ሃይል ያለው፡ የኢትዮጵያ መዳኛ አድርጎ የማሳየት የተለመደ ቀፋፊ የሆነ ስብከት የበዛበት ጉባዔ መስሏል። ለውጥ ዋዜማ ላይ የሚደረግ ጉባዔ እውነተኛ የሀገሪቱን ችግሮች መክሮ መፍትሄ ያስቀምጣል ብለን እየጠበቅን እያለ የድርጅትን ቁምና አልቅጥ ለጥጦ ብርሃንም መንገድም እኔ ነኝ ዓይነት “ስታሊኒያዊ- መለሲዝም” ስብከት ይደብራል። ለውጡ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ይቸልሳል።
ይህን ጉባዔ ወሳኝ ነው የሚል ግምት የወሰድኩት ከድርጅታዊ ግርግር ያለፈ ሀገራዊ አንገብጋቢ ጉዳዮችን መክሮ መፍትሄ ይሰጣል ከሚል ነው። ጉባዔው ኢትዮጵያ በጭንቅ ላይ ባለችበት ወቅት የሚከናወን በመሆኑ ከፕሮፖጋንዳው ቀንሶ ፖለቲካዊ ነጥብ ከማስቆጠር ተቆጥቦ እውነተኛና የምር የሆኑ እርምጃዎችን በመውሰድ ሀገሪቱ ላይ ያንዣበበውን አደጋ ለመግፈፍ ቁርጠኛ አቋም ይይዛል በሚል ነው በትኩረት የምከታተለው። ሆኖም እንደቀደምቶቹ የእነበረከት ስምዖን አይነቶቹ ጉባዔ ተራ ድራማዎችን ዘንድሮም ስመለከት ስሜቴ ቅጭም እያለብኝ ነው።
ለዚህም አንዱ ማሳያ በእነጌታቸው አሰፋ በደህንነት መስሪያ ቤት ፔሮል እየፈረሙ ደመውዝ የሚከፈላቸው፡ የተቃዋሚውን ጎራ ለማዳከም በህወሀት ተልእኮ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የነበሩ አደርባይ ግለሰቦችን በዚህ ጉባዔ ላይ በዚያው “ተቃዋሚ” በሚል መጠሪያ በክብር እንግድነት መጋበዛቸው ነው። ኢህአዴግ የምር ለሆነ ለውጥ ተዘጋጅቶ ከሆኑ እንደዚህ አይነት ኮተቶችን መተው አለበት። የውሸትና የማስመሰል ድራማዎችን ከነተዋንያኖቹ እያሳየን እውነተኛ ለውጥ አመጣለሁ ብሎ መስበክ የሚያዋጣው አይሆንም። እነዚህ “ማህተም በኪሳቸው ይዘው የሚዞሩ የተቃዋሚዎች ተቃዋሚ የሆኑ የህወሀት ምልምል ተከፋይ አሯሯጭ ግለሰቦችን” በሀዋሳው ጉባዔ ላይ ስናያቸው አሁንም ኢህአዴግ የቆሸሸውን፡ ህዝብ አንቅሮ የተፋውን፡ የቀደመ መስመሩን መቀጠል የፈለገ ነው የመሰለን። ስለእውነተኛ ምርጫ እያወራህ ዘንድሮም በእነዚህ ሰዎች መታጀብ መፈለግ ከወዲሁ ብጫ መብራት ማሳየት ማለት ነው።
በእውቀቱ ስዩም ”ኢህአዴግ ከዙፋን ወርዶ ኢህአዴግ ዙፋን ወረሰ” በሎ እንደተቀኘው እኛም እንደዚያ እንዳንል ያደርጉናል ብለን ተስፋ ሰንቀናል። ለማንኛውም የጉባዔውን መጨረሻ እንየውና እንመለሳለን።

Filed in: Amharic