>
5:13 pm - Tuesday April 20, 4184

የፓለቲካ ባህላችን የታመመ ነው!!! (አቶ ለማ መገርሳ)

የፓለቲካ ባህላችን የታመመ ነው!!!
አቶ ለማ መገርሳ
 
ለዚች አገር ለአንድ ዓመት አይደለም፤ ለአንድ ቀን አይደለም ለአንድ ሰዓትም ቢሆን ዋጋ የከፈለ ሰው ክብር ሊኖረው ይገባል። እኛ አገር ዕድሜውን በሙሉ መስዋት ያደረገ ሰው ክብር ይሰጠዋል? ስንዞርበት፣ ለውለታው ክብር ሳንሰጥ ኑሮውን፣ ህይወቱን ሁለመናውን እናመሳቃቅላለን
አሁን ላይ አስር፣ ሃያና መቶ ትምህርት ቤቶችን ስለመገንባት አይደለም ማውራት ያለብን። እንተወው! እሱን ገንዘብ ባለን ጊዜ እንገነበዋለን። መንገድም ቢሆን ገንዘብ በእጃችን ላይ ሲኖር ይሰራል። ጥያቄው እሱ አይደለም። ይህን ህዝብ ውጣና ስራ ብትለው ለሃያ አራት ሰዓት ካለ ዕረፍት የሚሰራ ህዝብ ነው።
ዋናው ነገር የፓለቲካ ባህላችን መለወጥ አለበት። ስለ እሱ ነው መወያየት ያለብን። የፓለቲካ ባህላችን የታመመ ነው። እያፈረሰን ያለው ይህ የፖለቲካ ባህላችን ነው። በመካከላችን ያለው ጥላቻ፣ መጠፋፋት አንዳችን በሌላችን ላይ የምናደርገው ዘመቻ መቆም አለበት።
 እንሰበሰባለን፣ እናጨበጭባለን፣ አብረን እንዘፍናለን ፤ ቆይተን ደግሞ አንዳችን በአንዳችን ላይ እንዞራለን። በዚህም አንለያይም፣ እንጠፋፋለን። በዚህ ውስጥ ሁላችንም አለንበት።
ለዚች አገር ለአንድ ዓመት አይደለም፤ ለአንድ ቀን አይደለም ለአንድ ሰዓትም ቢሆን ዋጋ የከፈለ ሰው ክብር ሊኖረው ይገባል። እኛ አገር ዕድሜውን በሙሉ መስዋት ያደረገ ሰው ክብር ይሰጠዋል? ስንዞርበት፣ ለውለታው ክብር ሳንሰጥ ኑሮውን፣ ህይወቱን ሁለመናውን እናመሳቃቅላለን።
ይህ ነው የእኛ አገር የፖለቲካ ባህል። ይህ ነው ከውስጣችን መውጣት ያልቻለው መርዝ። እንዲህ እየተጎዳዳን እንዲህ እየተጠፋፋን የት ልንደርስ እንችላለን? የትስ ያደርሰናል?
Filed in: Amharic