አቻምየለህ ታምሩ
* ዛሬ ከወደ አዋሳ እንደሰማነው የወልቃይት ጥያቄ ተነስቶ ክርክር በተካሄደበት ወቅት * ወልቃይት ከጎንደር ተወስዶ ምዕራብ ትግራይ የሆነው፤
* ራያ[አንጎት] ከወሎ ተወስዶ ደቡብ ትግራይ የተደረገው
* መተከል ከጎጃም ተቆርሶ መለስ ዜናዊ ወደፈጠረው ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የተካለለው … ሕገ መንግሥት ተብዬው ከመጽደቁ ከሶስት ዓመታት በፊት በመሆኑ የወልቃይት ጥያቄ በሕገ መንግሥት እልባት አግኝቷል በሚል በሕወሓት የቀረበው ነውረኛነት ተቀባይነት የለውም ብለው በቅርቡ የአዴፓን ማዕከላዊ ኮምቴ የተቀላቀሉ አባላት መከራከራቸውን ውስጠ አዋቂዎች ተናግረዋል!
—
ከሁለት ዓመታት በፊት ብአዴኖቹ እነ አዲሱ ለገሠ፣ አለምነው መኮነን፣ ገዱ አንዳርጋቸውና ካሳ ተክለ ብርሃን ስለ ወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ በልማታዊ ጋዜጠኞች ተጠይቀው ጉዳዩ «በሕገ መንግሥቱ መሰረት የተፈታ መሆኑን» ሳያፍሩ ተናግረው ነበር።
ይህንን አሳፋሪ የሕወሓት እንደራሴዎች መልስ ተከትሎ «ብአዴን የሕወሓት ነውረኛ ድርጅት እንጂ የአማራ ሕዝብ አካል አይደለም» በሚል በሶስት ተከታታይ ክፍሎች ባቀረብሁት የሕወሓቱ ብአዴን ታሪክ «ምንም እንኳ ሕገ መንግሥታቸውን ባልቀበለውም፤ በሕገ መንግሥታቸው መሠረት እንኳ ብንሄድ ወልቃይት ከጎንደር ተወስዶ ምዕራብ ትግራይ የሆነው፤ ራያ[አንጎት] ከወሎ ተወስዶ ደቡብ ትግራይ የተደረገውና መተከል ከጎጃም ተቆርሶ መለስ ዜናዊ ወደፈጠረው ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የተካለለው በ1987 ዓ.ም. የጸደቀው ሕገ መንግሥት ተብዮው የወያኔ ፕሮግራም በሥራ ላይ ከመዋሉ ከሶስት ዓመታት በፊት ማለትም በ1984 ዓ.ም. በመሆኑ የወልቃይትን ጉዳይ ዛሬ የብአዴን ነውረኞች ጉዳዩ «በሕገ መንግሥቱ መሰረት እልባት አግኝቷል» በሚል ለቀጠራቸውና ቀለብ እየሰፈረ በሆዳቸው ለሚገዛቸው ፋሽስት ወያኔ በመወገን ከአማራ አንጻር በመቆም የሰጡት ነውረኛ ምላሽ ውሃ የሚቋጥር ነገር እንደሌለበት አንስቼ ነበር።
ዛሬ ከወደ አዋሳ እንደሰማነው የወልቃይት ጥያቄ ተነስቶ ክርክር በተካሄደበት ወቅት ወልቃይት ከጎንደር ተወስዶ ምዕራብ ትግራይ የሆነው፤ ራያ[አንጎት] ከወሎ ተወስዶ ደቡብ ትግራይ የተደረገውና መተከል ከጎጃም ተቆርሶ መለስ ዜናዊ ወደፈጠረው ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የተካለለው ሕገ መንግሥት ተብዮው ከመጽደቁ ከሶስት ዓመታት በፊት በመሆኑ የወልቃይት ጥያቄ በሕገ መንግሥት እልባት አግኝቷል በሚል በሕወሓት የቀረበው ነውረኛነት ተቀባይነት የለውም ብለው በቅርቡ የአዴፓን ማዕከላዊ ኮምቴ የተቀላቀሉ አባላት መከራከራቸውን ውስጠ አዋቂዎች ተናግረዋል። እነዚህ የአዴፓ አዳዲስ አባላት የወልቃይትን ጉዳይ በድፍረት አንስተው በዚህ ደረጃ መከራከራቸው በጎ ቢሆንም ቅሉ የወልቃይት፣ ራያ[አንጎት] እና የመተከል ጉዳይ ግን ባግባቡ መመለስ ያለበት ከታሪካዊ ይዞታ አኳያ ብቻ መሆኑ ለሰኮንድ መዘንጋት የለበትም።
ወልቃይት በግፍ ወደ ትግራይ የተካተተው ፤ እስከ አሸንጌ ያለው የራያ ክፍልም ለም መሬት ፍለጋ ባላገሩን እንዲፈናቀል እየተደረገ በወረራ የተያዘው ከጎንደር/ ስሜንና ከወሎ እንጂ በታሪክ አንድም ዘመን የትግራይ አካል ሆነው አያውቁምና መቅረብ ያለበት ተገቢ ጥያቄ ወደ ነበሩበት ታሪካዊ ይዞታቸው እንዲመለሱ መጠየቅ ብቻ ነው። የወልቃይትን ታሪካዊ ይዞታ በሚመለከት ከሁለት ዓመት በፊት «Forceful Annexation, Violation of Human Rights and Silent genocide: A Quest for Identity and Geographic Restoration of Wolkait-Tegede, Gondar,Amhara,Ethiopia» በሚል የጻፍነውን ኢንተርኔት ላይ ፈግሎ ማንበብ ይጠቅማል። ወልቃይትንና ራያን የትግራይ አካላ ነበሩ የሚል ካለ ደግሞ ታሪካዊ ማስረጃውን ያቅርብና ቢፈልግ በመረጠው ሜዲያ፤ ቢያሻው ደግሞ በማናቸውም ገለልተኛ ፍርድ ቤት ቀርበን እንሟገትና እንዳኝ! አበቃ!