>

የአድርባይነት ጣጣ!! (ሀብታሙ አያሌው)

የአድርባይነት ጣጣ!!
ሀብታሙ አያሌው
1.  “በአገሪቷ ውስጥ ሁለት መንግስት አለ፤  ከፈለግን በ24  ሰዓታት ውስጥ መንግስትን የመገልበጥ አቅም አለን፤አዲስ አበባ የኦሮሞ ነች፤ ቡራዩ ሲቸገሩ የተሰደዱ የደቡብ ተወላጆች በኛ ፈቃድ የሚኖሩባት ወረዳ ናት”  እያለ የሚቀሰቅሰውን ከታሪክ ከህግ እና ከሞራል ልዕልና እርቆ ጥላቻ የሚቀሰቅሰውን ጀዋርን አቅፎ ጋዜጠኛ ቤቲን ማስጠንቀቅ ምን ማለት ነው ?
 2.   የመንግስት ስልጣን ስለያዘ ብቻ የአቃቤ ህግ   መስሪያቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደና
       “የአዲስ አበባ  ወጣቶች አሁን ጥያቄያችሁ ግልፅ  ሆኗል ልካችሁን እናሳያችኋለን”  ብሎ  በዛተ ማግስት
       የአዲስ አበባን ወጣት ወደ ጦላይ በረሃ ወስዶ ፍዳውን  ማሳየት መብቱ በሆነባት አገር ቤቲ ላይ ጉልበት
       ማሳየት ምን ማለት ይሆን ?
3.    አፄ ምኒልክ  5 ሚሊዬን ኦሮሞ ጨርሷል እያለ  ለሚቀሰቅስ ዘረኛ ለመሀመድ አዴሞ ሹመት ሰጥቶ
        ቤቲን ማባረር ምን ማለት ነው ?
4.  ነጋ ጠባ “አማራን ባለበት ጨርሱት”  ብላ በማህበራዊ  ሚዲያው በግልፅ የምትቀሰቅስ ዘረኝነት
የተጠናወታትን ጂጂ የምትባል ሴት እንደ ጀግና  በፖሊስ አጅቦ የሚዞረው  የኦሮሚያ ፖሊስ ለምን ሳይባል ለዘረኝነት ቅስቀሳዋ ወሮታ  እየተከፈላት እያየ ዝም ያለው የዶክተር አብይ መንግስት ቤቲ ላይ ለምን በረታ ?
5.   የኦሮሞ ድርጅት ነን የሚሉ የአምስት ፓርቲ ተወካዬች ነን  በሚል በግልፅ እራሱ መንግስት በሚምልና
       በሚገዘትበት ህገ መንግስት የተደነገገውን በመካድ ከህግ ከታሪክና ከሞራል በራቀ መንገድ አዲስ አበባ
       የአንድ ብሔር ነው እያሉ ሲያውጁ ሲቀሰቅሱ ዝም ብሎ  ደርሶ ጀግና ልሁን ማለት ምን ማለት ይሆን ?
 ጋዜጠኛዋ እውነትን ከማፈላለግ ድንበር  ተሻግራ  ተጠየቂውን ነጥብ የማስጣል ትኩረት እንደነበራት
 ግልፅ ነበር።  ከዚህ በቀር ቃለምልልሱን ከድረገፅ  የሚያስነሳና ማስጠንቀቂያ የሚያሰጥ አንድም  ምክንያት አልነበረም።  የዶክተር አብይ መንግስት ለምን ይሄን እርምጃ መውሰድ ፈለገ ለሚለው ጥያቄ ምላሽ…ብዙ ማለት ቢቻልም ለጊዜው ይቆየን…   የአብን ሊቀመንበር እራሱ ይሄን አሳፋሪ ተግባር   እንደሚያወግዝ ተስፋ አደርጋለሁ።
Filed in: Amharic