>

በቤተመንግስት ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል!!!

በቤተመንግስት ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል!!!
ሀብታሙ አያሌው
ምን ተፈጠረ የሚለውን ለማጣራት የውስጥ ሰው አገኘሁ   እናም በጣም አስደንጋጭ ነገር  ሰማሁ።  በቅርችቡ አዲስ የተመደቡት የቤተመንግስቱ ልዩ ኃይሎች በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአቶ ደመቀ መኮንን ላይ አፈና ለማድረግ ሞከሩ፤ አስከፊ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት ከውጭ የጥበቃ ልዩ ኃይል ከበባ ፈፅሞ ሁኔታውን በማክሸፍ አቶ ደመቀ ዶክተር አብይ ቢሮ መግባት መቻላቸውን አረጋገጠልኝ። ከመስቀል አደባባይ እስከ አራት ኪሎ ያለው መንገድ እና ቤተመንግስት ዙሪያ ገባውን  በዚህ ሰዓት እንደተዘጋ ነው።
መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ወይም እገታ ተደርጓል!!
ስዩም ተሾመ
 
ዘመኑን ሁሉ ሲዋሽ የኖረን ሚድያ እንዴት ድንገት እመኑ ይባላል?!?
 
ማወቅ መጠየቅ ነው! #ቤተ_መንግስት
ይሄ ህዝብ እኮ ገራሚ ነው። በቤተ መንግስት አከባቢ የነበሩ መንገደኞችን ወታደሮች ከመኪናዎቻቸው አስወርደው፣ እንዲሁም በቤተ መንግስቱ አቅራቢያ በሚገኙ መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችን አስወጥተው እያዋከቡ እስከ ትምህርት ሚኒስቴር ድረስ ከወሰዱ በኋላ፣ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር ቤተ መንግስቱን ሲከብብ እየተመለከተ “ወደ ቤተ መንግስት የሚገቡ ወታደሮች እየተፈተሹ ነው” ይለኛል። ነገር ገባው የተባለ ደግሞ ከዚህ ትንሽ ፈቀቅ ብሎ “የቤተ መንግስት ወታደሮች የደሞወዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው አድማ ወጥተው ነው” ይላል። በእውነቱ “እንደ አፋችሁ ያድርገው!” ከማለት ሌላ ምን ይባላል?
ነገር ግን ነገሮችን ማያያዝና በጥሞና ማስተዋል የሚችል አዕምሮ ያለው ሰው “ወደ ቤተ መንግስት የሚገቡ ወታደሮች እየተፈተሹ ነው” ሲባል “ታዲያ በቤተ-መንግስቱ አቅራቢያ የሚገኙ መንገደኞችና የመስሪያ ቤት ሰራተኞችን ከያሉበት እያዋከቡ በማስወጣት መፈተሸ ለምን አስፈለገ” ብሎ መጠየቅ እንዴት ይሳነዋል? እሺ “የቤተ መንግስት ወታደሮች የደሞወዝ እንዲጨመርላቸው አድማ አድርገው ነው” የሚለውን ሃሳብ ተቀብሎ ሳያመነዥግ ከመዋጡ በፊት “ታዲያ በመላ አዲስ አበባ የኢንተርኔት አገልግሎትን ማቋረጥ ለምን አስፈለገ” ብሎ መጠየቅ የለበትም? “ጉዳዩ የደሞወዝ ጥያቄ ከሆነ ይሄ ሁሉ ወታደር ቤተ-መንግስቱን የሚከብበት ምክንያት ምንድነው?” ብሎ መጠየቅስ እንዴት ይከብዳል። ወታደሮች የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትን መቆጣጠር ያስፈለገበት ምክንያትስ?
ከላይ የተነሱትን ጥያቄዎች መጠየቅና አንድ ላይ አያይዞ መመልከት የቻለ ሰው ዛሬ በቤተ-መንግስት ውስጥ መፈንቅለ-ሙከራ ወይም እገታ እንደተደረገ መገመት ይችላል። ሌላው ቢቀር ለስንት አመት ውሸት ሲቀልበው የነበረውን ሚዲያ ተዓማኒ አድርጎ “EBC እኮ እንዲህ ብሏል!” እያለ ጅልነቱ ሳያንስ ሌላውን ሊያጃጅል አይሞክርም።
(ፂዮን ግርማ  በገጿ ይህን ለጥፋለች)
ባገኘኋት አጭር የግራ ቀኝ መረጃ በቤተመንግሥት ውስጥ የሚገኙ አንድ ሻለቃ ጠባቂዎች (ሁሉም አይደሉም) የደሞዝና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ዛሬ ጠዋት አንስተው ነበር። ምንጮች እንደነገሩኝ ጥያቄውን ያቀረቡት ግቢ ውስጥ ቢሆንም አቀራረቡ ግን በተቃውሞ ሰልፍ መልክ ነበር። ቆየት ብሎ ትጥቃቸውን ፈተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር በሰላም በጥያቄዎቻቸው ዙሪያ ሲወያዩ እንደነበር ነው።
የውጭ ጥበቃውን በተመለከተ ያገኘሁት መረጃ፡- የውስጡ  ጥያቄ ሌላ መልክ ይኑረው አይኑረው ለጊዜው ባለመታወቁ ለጥንቃቄ በሕጋዊ መንገድ የተጠራ አድማ አፍራሽ ኃይል ነው የሚል ነው። (ተጨማሪ መረጃ ካገኘሁ ላካፍላችሁ እሞክራለሁ። 
ናትናኤል መኮንን በገጹ ይህን አስፍሯል!
Ethiopia : በአራት ኪሎ ከቤተ መንግስት ጀምሮ እስከ ፖርላማው በወታደር ተከቧል መንገዶች ዝግ
ናቸው:: ፒካፕ የሆኑ መኪኖችን ወታደሮች በግዳጅ እያስቆሙ ለትራንስፖርት በሚመስል መልኩ
እየተጠቀሙባቸው ነው:: በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግስት አካል እስካሁን ያሳወቀው ነገር የለም:: በአካባቢው ያሉ ቢሮዎች ተዘግተው ሰራተኛውና ነዋሪው እንዲወጣ ተደርጓል::
በአዲስ አበባ አራት ኪሎ ቤተመንግስትና አካባቢው ግርግር እንደተስተዋለ ከአዲስ አበባ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያመለክታሉ። እስካሁን የግርግሩን መነሻ በተመለከተ ሁነኛ መረጃ ባይኖርም የተለያዩ ወሬዎች እየተናፈሱ ነው። ብዛት ያላቸው ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ወታደሮችን ጭነው ወደ ቤተመንግስቱ ሲያመሩ ታይተዋል፣ ቀደም ሲልም ቤተመንግስት አካባቢ አሽከርካሪዎች ከመኪናቸው እንዲወርዱ ሲደረጉ እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል። ቤተመንግስት አካባቢ ያሉ መስሪያቤቶች ሰራተኞች ህንፃዎቹን እየለቀቁ እንዲወጡ ተደርጓል። ቤተመንግስት ዙሪያ ያሉ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ሆነዋል።
አሁን ዘግይቶ በደረሰ ዜና መሰርት ደግሞ በአዲስ አበባ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ተነግሯል።
Filed in: Amharic