>
6:09 pm - Wednesday January 26, 2022

ለውጡና የጊዜው ፈተና (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

ለውጡና የጊዜው ፈተና
መንገሻ ዘውዱ ተፈራ
ለውጥ ስንል የአንድ ነገር በይዘትም ሆነ በቅርጽ ከነበረበት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መቀየር ወይም መሻሻል ሲሆን አሁን በዚህ ጹሁፍ ሰለ ለውጥ ለማስረዳት ሳይሆን አሁን በሐገራችን ኢትዮጵያ ትላንት ከነበረው አፈና በመጠኑም ቢሆን እንዲህ የጉንጭ የጉንጫችን መተንፈስ ሰልበቃንበት የሰርዓት ለውጥ ብልጭታና ይህን መልሶ ሊያሳጣን ሰለተደቀነብን የለወጡ ባለቤትነት ሽሚያ የጊዜው ፈተና ነው።
ሰለእያንዳንዱ ግለሰብ ወይም ቡድን ትግል አበረካቾች ዝርዝር እንፃፍ ከተባለ የእያንዳንዱ አስተዋፅኦ ብቻ ሙሉ መፃህፍ ሊወጣው የሚችልም ይሆናል። ይህ ግን ቢያንስ አልፎ አልፎ ጥቂቶቹን ብቻ በማሳየት እኔ በደማሁበት በሚል በየአካባቢው የሚሰማውን ዋጋ ይከፈለኝ ጥያቄ የሚመስል ጉርምርምታ ምናልባትም በአለፈ እርስ በእርሳችን በመጠፋፋት ያገኘነውን የለውጥ እድል እንዳናጣው ለማመላከት ነው።
ሰፋ አድርጎ ማየትና መገንዘብ ከተቻለ ለውጡ በተወሰኑ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች ብቻ የተገኘ ሳይሆን ህወሃቶች ተመሰረትን ካሉበት ከ1967ዓ/ም ጀምሮ አስከ ትላንትናው መስከረም 25/2010 ዓ/ም የሃዋሳዋ ዳግማዊት ጣይቱ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ መላው ኢትዮጵያዊያን የተሳተፍንበት የትግል ወጤት ነው።
ሙት ወቃሽ አያድረገንና ህወሃትና የተንኮልና ጥፋት ደቀ መዝሙሩ ሟቹ 17 ሆነው በአንድ ጓንዴ ጠመንጃ እንድ መንደር ተጠግተው ትግል ሰለ መጀመራቸው ነግረውናል። አዚህ ላይ ስለ ቁጠራቸውና መሳሪያቸው ሳይሆን ትግሉ የተጀምረው አንደ መጠጊያ ከተጠቀሙበት የትግራይ መንደር መሆኑን ለማሳየት ነው።
የህወሃት ታጋይ ነን ባዮቹ መጀመሪያ መጠጊያ ካደረጉበት መንደር ጀምሮ ለመላው የትግራይ ህዝብ፦ ከወሎ ክፍለ ሐገር ዋና ከተማው አሳይታ ከነበረው የአውሳ አውራጃ (አሁን አፋር ክልል)፤ ዋና ከተማው ማይጫው ከሆነው ራያ አዘቦን፤ ዋና ከተማው አላማጣ ከሆነው ራያ ቆቦ አሰከ ወልድያ ከተማ አል ውሃ ወንዝ ድረስ፤ ከበጌ ምድርና ሰሜን ክፍለ ሐገር ደግሞ ሰሜን አውራጃ ጠለምትን አሰከ ሊማሊሞ አፋፍ ድረስ፤ ከወገራ አውራጃ ወልቃይት ጠገዴ ያለውን መሬት የእኛ በማድረግ ነፃ ልናወጣችሁ መጣን ነበር ያሏቸው።
የትግራይ ህዝብ ግን የዛሬውን በትላንት ህልም በመገመት ያለምንም ስህተት ከኢትዮጵያ ተንጥለው መኖር እንደማይፈልጉ በመንገር የልቅስ እነሱንም ስህተታቸውን በመንገር አርፈው እንዲቀመጡ ከፈለጉም ምህረት አንደሚጠይቁላቸው ከመንገር ውጭ ተከትለው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አልዘመቱም።
እነዚህ የጥፋት እሳቶች ግን ከአረፉበት መንደር ጀምሮ የዚህ አይነት ኢትዮጵያዊነት ስሜት ያላቸውን ታላላቅ የትግራይ ሐገር ሽማግሌዎች እየገደሉ ነው የቀጠሉ። ይህን ከሌላው የእኔ አይነት የምንሰማውን ለማመን ቢከብደን ከእራሳቸው ከነበሩ ነባር ታገዮች አቶ አበረሃ ያየህ አቶ ገ/መድህን አርአያና ሌሎችም ከአንደበታቸው ሰምተናል። ታዲያ እነዚህ ኢትዮጵያዊያን የትግራይ ልጆች ትግል አስተዋፅ አላደረገም?
ዛሬ ከኢትዮጵያ ህዝብ ሊነጠሉት ሌት ከቀን ሲታትሩ የዚያን ጊዜው ጭካኔአቸውና አረመኔነታቸው የፍርሃት ቆፈን አልለቃቸው በሎ ውስጥ ሆዳቸው እያረረ ዝም ቢሉ የትላንቱን ትግላቸውና መስዋዕትነታቸው ሊረሳ አይገባም።
ህወሃት አሰከ አሁን ባለው 27  ዓመታት በየደረሱበትና በተቆጣጠሩት አማራ፣ኦሮሚያ፣ደቡብህዝቦች፣ ቤኒሻንጉል፣አፋር፣ሐረሪ፣ጋምቤላ፣ሶማሌ በአጠቃላይ መላው ኢትዮጵያ ስለ እናት ሐገር ኢትዮጵያ የሚናገሩ የሐገሪቱ መዛግብት ትልልቅ ሰዎችን አጥፍተዋቸዋል።ነፍሳቸውን ይማርና አነዚህ ትልልቅ ሰዎች አኮ የዚህ ለውጥ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ባለቤቶች ናቸው።
በ1983 ዓ/ም ወያኔ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር አማራ ክልል ከሱዳን ጋር ድንበር እንዳይኖረው አድርጎ የመሬት ማሳያ ንድፍ ሰርቶ በዚያ መሰርት አማራ ክልል ከሱዳን ድንበር አልነበረውም።
ከፊሎቹ አሁንም በህይወት ያሉ የጎንደር ተወላጆች ይህን አይን ያወጣ ሌብነት እግባብ አይደለም ብለው በጠንካራ ኃይለ ቃል ደብዳቤ በመፃፍ በሰላማዊ መንገድ ከመጠየቅ ጀምሮ በግልፅ የተናገሩና አሰከ ጦርነት የገቡ እሉ። ሌሎቹ ደግሞ ጥበብ በተሞላበት ህይወታቸውን ለመሰዋዕትነት በማቅረብ ገንዘባቸውን በማፍስስ መሬታቸውን በመያዝ ሲታገሉ፤ በስልጣን ላይ የነበሩ ደግሞ ስልጣን ብለን ድንበራችን ይዘቱን ከሚለቅ እኛ እንጠፋ ብለው በመተባበር ሰልጣናቸውን ያጡ አሉ፤ አሁን ለታሪከ ያሉ ጋዜጠኞችም በዘገባ በመተባባር የዛሬው የአማራ ክልል ከሱዳን ድንበርተኝነት ያቆዩ ታጋዮች የትግሉ አካል አኮ ናቸው።
በሰው አገር በአስጨናቂ የኑሮ ጫና ውስጥ ሆነው በርገር እየበሉ እየተባሉ ሲወነጀሉ የበረዶ ቁር ብርድ የፀሐይ ሐሩር ሳይፈሩ በመታገል HR128 የሳወጁት ወገኖቻችን ለትግሉ ውጤቱ ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል። አዚህ ጋር ተያይዞ ሊጠቀስ የሚችል የኢሳትስ ሌት ተቀን ግብግብ ለዚህ ለውጥ  ግምባር ቀድም ተጠቃሽ አይደልም?
ምናልባት ትግሉ ትላንት 2008 ዓ/ም የተጀመረው ነው ብለን የምናስብ ካለን እናስተውል አንዲህማ ቢሆን ኖሮ ወያኔ 27 ዓመት እያሰቃዩን ባልቆዩ ነበር። ሌላው ቢቀር በ1997ዓ/ም አመፅ ባሰወገድናቸው ነበር።
ሁላችንም ማስታወስ አንደምንችለው ትግላችን እየገፋ መጥቶ 2010 ዓ/ም ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በየወረዳችን አንዳንድ የትግሬ መከላከያ አዛዥ ከበስተጀርባ በትግራይ”አፋኝ ኃይል በመታገዝ አፋችን መልሰን ዘግተን ነበር እኮ።
በመሰረቱ ትግል የአንድ ጊዜ ሆያ ሆየ ሳይሆን ከላይ የተዘረዘሩት ጥቂቶቹና ብዙ ያልተዘረዘሩት እንዲሁም የፋኖ ቄሮ ዘርማና ሌሌችም የመላው ኢትዮጵያ ልጆች የጋራ ትግል የወለዳቸው የዶ/ር አብይ ኦሮማራ ደህዴን መላው ኢትዮጵያዊያን የትግል አስተዋፅኦ ደርብርብ የትግል ውጤት ነው እንዲህ አሁን ልጓማችን ተፈቶ እንድናወራ መቻላችን።
ይህም ሆኖ አሁንም ህዋሃቶች በዘረፉት ገንዘብና በየቦታው ባቋቋሟቸው ግብረ :በላዎቻቸው ዶ/ር አብይንና አስተዳደራቸውን ደካማ በማስመሰል መፈንቀለ መንግስት ለማካሄድ እያፋጁን መገኘታው አልበቃ ብሎ ኦሮማራን ከደህዴን ለመነጣጠል ሌላ ሴራ ሲያሴሩ ይኸው አድሜ ይስጣቸውና ዳግማዊት ጣይቱ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከእኔ ሀገሬ ብለው በወሰዱት እርምጃ ሴራውን አከሸፉትና ይኸው ሁለተኛው ወሳኝ የአሻናፊነት ጉዞአችን ተጀመረ። ይህ አኮ ትልቅ ዋጋ ያለው የትግል አበርክቶ ነው።
በመሆኑም ይህን አሁን የምንገኝበት የትግል ውጤት ወደፊት ለማስቀጠል የሚጠብቀን የትግል ጉዞ የደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን የተቃራኒዎችም የትግል ስልት ስህትት አስተዋፅኦ የሚኖረው የብዙ ግብዓት የረዥም ጊዜ ጥረት ውጤት መሆኑን በመረዳት እያንዳንዳችን ትግላችን በብልሃትና በጥንቃቄ የማሰቀጠል ኃላፊነት ያለብን መሆኑን መረዳትና በዚህ አግባብ መታገል ይገባል።
ለዚህ ነው እኔ የተለየ አድረጌአለሁ የማያስብል ።ነገር ግን አሁንም እኔ የተለየ አድርጌአለሁ የምንል ካለን የድሮ አባቶች አውቀትን በሚያስተላልፉበት ተረትና ምሰሌ “አህያ የተጫነችውን አትበላም አባባል” አንዱ ለአንዱ ቤዛነት ተፈጠሮዊና ማህበራዊ የሞራል ግዴታ ያለብን መሆኑን ለማሰየት ነው።
ስለዚህ ቢቻል የትግሉ ውጤት በመላው 100 ሚሊዮን ህዝብ የመጣ መሆኑን ማመንና እርስ በእርሳችን ከመናቆር ሳንገፋፋ የመጣውን የጋራ ሀብት የለውጥ አጋጣሚ ተጠቅመን እንደየአቅማችን የድርሻችን በማበርከት ሐገራችን ከጠበቅናት ከተንከባከብናትና በትክክለኛ መንገድ በዕወቀት ተመስረተን ካለማናት ለእኛ ለኢትዮጵየዊያን ብቻ ሳይሆን ለአፈሪካ ብሎም ለዓለም የሚተርፍ ሀብት ያለን መሆናችን በመረዳት አሁን ወደ ሚጠበቅብን ልማትና አድገት ጉዞ ማምራት ነው።
ለዚህ ደግሞ ቢያንስ እኛ በሕይወት በመኖር እንዲህ ለመነጋገርና የትግላችን ፍሬ ለማየት አድል አግኝተናል፤ አስኪ የሞቱትን፤ እንደይፈጥሩ ሆነው በሕይወት ያሉትን ለደቂቃ ከእኛ ጋር እያወዳደርን እናስባቸውና ዋጋ መከፈል ካለበት ለእነዚህ ሰዎች ምንና ስንት ዋጋ ይከፈላቸው? ብለን እራሳችን ብንጠይቅ ትክክለኛ ውሳኔ ላይ አንደርሳለን ብየ አምናለሁ።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
Filed in: Amharic