>

የሆነው ይሄው ነው፤ እገታ ተፈፀመ ከሸፈ

የሆነው ይሄው ነው፤ እገታ ተፈፀመ ከሸፈ

ሃብታሙ አያሌው

1. ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነበሩት ሚሊኒየም አዳራሽ ስብሰባ ላይ ነበር።
2. ከስብሰባ ሲመለስ የቤተመንግስቱ ጠባቂ ኃይል እና
ከውጭ የመጣው ቀይ መለዬ የአጋዚ ጦር መካከውል ከፍተኛ መፋጠጥ ገጥመዋል።
3. አቶ ደመቀ ወደ ቤተመንግስቱ ሊገባ ሲል ልዩ ኃይሉ ከበባ ፈፀመ
4. ከቤተመንግስቱ ጀርባ የጥበቃ ኃይል ድንኳን ውስጥ አቶ ደመቀ እንዲያናግራቸው ተስማምቶ እገታው ከውጭ በመጣ ሌላ ልዩ ኃይል ከሸፈ።
5. አቶ ደመቀ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እንዲገባ ከተደረገ በኋላ ሁለቱ መሪዎች ተወያይተው ውይይት
ተካሄደ
6. ኮሚሽነር ዘይኑ ዶክተር አብይ አናገራቸው ሲል ተናገረ ፎቶዎች አቶ ደመቀ እንዳናገራቸው የሚያመለክት ሆነው ይፋ ሆኑ።
7. አቶ ደመቀ ከወታደሮች ጋር ፎቶ ተነስቶ እንዲለጠፍ በማድረግ መንግስት ህዝቡን ወደማረጋጋት ሄደ።

ዘመኑ የመረጃ ነው ምክንያቱ በእርግጥ የደሞዝ ነው ወይም ሌላ የፖለቲካ ሻጥር ለጊዜው ይቆየን…እገታው ማን ላይ እንደነበረ ፎቶውን ያየ ብቻ በቀላሉ መረዳት ይችላል።

ዋናው ነገር እገታው ከሽፏል መንግስት በጉዳዩ ላይ ከዚህ በላይ እንዲል አይጠበቅም።

 

ሃገር መከላከያ የተለያየ ክፍለ~ጦር የተውጣጡ የጦር ሰራዊት አባላት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል።

ጽዮን ግርማ

አባላቱ ከተጣለባቸው ሃገራዊ ሃላፊነት እና ግዳጅ ጋር ተያያዥ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
በውይይቱ የመከላከያ አባላት እንደዜጋ ጥያቄያቸው ሊደመጥ እና በተግባር መመለስ እንዳለበት አቶ ደመቀ ጠቁመዋል።
መንግስት እንደሃገር የጀመረው የሪፎርም ስራ በመከላከያ ዘርፉም በተመሳሳይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ተጨማሪ ውይይት በሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ መድረኮች የሚመቻቹ መሆኑን አቶ ደመቀ አስረድተው፤ በቀጣይም መንግስት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ደረጃ በደረጃ እንደሚፈታ አረጋግጠዋል።

የመከላከያ አባለቱም በውይይቱ ለተነሱ የዘርፉ ችግሮች በሰከነ አግባብ እንዲፈታ እና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
~~~~~
በመቀጠል አባላቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ጋር ውይይት አድርገዋል።
~~~~~
30/01/11 (ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተረጋገጠ ተፌስ ቡክ ገፅ የተገኘ ነው)

Filed in: Amharic