>
4:33 pm - Wednesday November 30, 2022

የመረጃው ምንጭ እውነታው ይህ ነው ይላል (ሃብታሙ አያሌው)

የመረጃው ምንጭ እውነታው ይህ ነው ይላል 
ሃብታሙ አያሌው
መንግስት ስለሁኔታው ከዚህ በላይ እንዲል አልጠብቅም። መቼም ታገትን እንዲሉ አይጠበቅም። ያለቀጠሮ መሳሪያ ይዞ መጥቶ አስገድዶ ያናገረን ሰራዊት አብርዶ መመለሱ ጥሩ ቢሆንም በጎ ሁኔታ እና ልምድ ግን አይደለም። የሆነው ሁኖ ወደ መረጃ ምንጬ ተመልሼ የሆነውን በዝርዝር እንዲያስረዳኝ በመጠየቅ በርግጥ በርግጥ እገታ አልነበረምን ? ስል ለጠየኩት ጥያቄ እውነታው ይህ ነበር ብሎኛል !!
ጠዋት 4:45
~~~~~~
ከወትሮው ባልተለመደ መልኩ የመከላከያ ሰራዊት የተውጣጡ ቀይ ቦኔት የለበሱ አባላት አራት ኪሎ በአራቱም አቅጣጫ ላይ መታየት ጀመሩ። ወዲያው ባፋጣኝ ወደ ጊቢ ገብርኤል የሚወስደው መንገድ ለተሽከርካሪ ዝግ ተደረገ።
ቀትር 6:30
~~~~~~
በተለያየ አቅጣጫ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የሚመጡት ልዩ ሃይሎች ቁጥራቸው እየበዛ መጣ።
ከቀኑ 7:45
~~~~~~
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሚሊኒየም አዳራሽ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን በይፋ ከፍተው ከቦሌ ወደ አራት ኪሎ ፅ/ቤታቸው አቀኑ።
ከቀኑ 7:55
~~~~~~
ከተለያየ አቅጣጫ የሚጎርፉት የሰራዊቱ አባላት ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፤ አራት ኪሎ አካፋይ መንገድ ላይ ወደ ቤተመንግስት የሚወስዱ መኪናዎች አቅጣጫ እየቀየሩ አከባቢው ተጨናንቆ ነበር።
ከቀኑ 8:00
~~~~~~
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀን የያዘው መኪና {ጥይት የማይበሳው} ወደ አራት ኪሎ አካፋይ መስቀለኛ መንገዱ ጋር ደረሰ። የአቶ ደመቀ ልዩ ጠባቂዎች በፍጥነት ከመኪናው ወርደው አጅበው ለማሳለፍ ፤ አልተሳካም ወታደራዊ ሃይሉ አቶ ደመቀን አግቶ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዋና ጠባቂ {Cheif Secirty} ጋር ቃላት ተመላለሱ።
ይህ ሁኔታ ድንጋጤ ፈጠረ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን መንገድ ላይ ያገኙት በእቅድና በዝግጅት ወይስ ባጋጣሚ የታወቀ ነገር አልነበረም።
ባጭሩ አቶ ደመቀ “ከናንተ በላይ ጥያቄው ሊደመጥ የሚገባ ማንም አይኖርም። ዶ/ር አብይ እስኪመጣ ከኔ ጋር መወያየት እንችላለን።” የሚል ቃል ገብተው ከእገታው ተለቀቁ። በዚህ ግን አላበቃም፤ በሁኔታው የተደናገጠው የቤተመንግስቱ ልዩ ኃይል ሁኔታውን እስኪያጣራ ከቢሯቸው ውጪ አግቶ አቆያቸው።
ከቀኑ 8:45
~~~~~~
የጎንዬሽ ውይይቱ ሲሰምር አቶ ደመቀ ወደ ዶክተር አብይ ቢሮ ሄደ የወታደሮቹ የሃይል መሪዎቹም የሰራዊት አባላቱን ሰላማዊ ውይይት ለማድረግ የታጠቁትን መሳሪያ እንዲፈቱ አግባቡ ስምምነት ተፈጠረ።
ከቀኑ 9:00
~~~~~~
በውይይቱ መነሻ ላይ የሰራዊቱ አባላት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ያለማንገራገር ሌላ ስራቸውን ሰርዘው ሰራዊቱን ለማነጋገር መወሰናቸው አድናቆታቸውን እና አክብሮታቸውን ገለፁ።
ከቀኑ 9:00 ~ 10:30
~~~~~~~~~~
የሰራዊቱ አባላት ከደሞዝ፥ ከኑሮ ውድነት፥ ከመልካም አስተዳደር፥ ከግዳጅ ተልዕኮ ጋር የተያያዙ የግብዓት ጥያቄዎችን… አነሱ
ከቀኑ 10:30 ~ 10:45
~~~~~~~~~~~~
~> ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለሰራዊቱ አባላት ምላሽ መስጠት ጀመሩ።
~>መንግስት እንደሃገር የጀመረው የሪፎርም ስራ በመከላከያ ዘርፉም በተመሳሳይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ~ ብለዋል።
~>ተጨማሪ ውይይት በሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ መድረኮች እንደሚመቻች ~ ተናግረዋል።
ከቀኑ 10:45
~~~~~~
የም.ጠ.ሚ/ሩ ዋና ጠባቂ አስቸኳይ የስልክ ጥሪ እንደተደወለላቸው ለአቶ ደመቀ ቀረብ ብሎ ነገራቸው።
ከቀኑ 10:46
~~~~~~~~
አቶ ደመቀም የሰራዊት አባላቱን ይቅርታ ጠይቀው {የጀመሩበትን የንግግር ምት ሳይቀይሩ} . . . . ስልኩን ማናገር ጀመሩ።
ከቀኑ 10:47
~~~~~~~
አቶ ደመቀም ወደ ሰራዊት አባላቱ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው . . . .
“የደወለው ሰው ዶ/ር ዓብይ ነው። ስብሰባ አጠናቋል አሁን ጉባኤ አዳራሽ ለማናገር እየጠበቃችሁ ነው። . . ” እንዳሉ ሰራዊት አባላቱ ንግግራቸውን በጭብጨባ አናጠቧቸው።”
ከቀኑ 10:50
~~~~~
በማጠናቀቂያው ሁለት አባለት ሰራዊቱን በመወከል በውይይቱ ለተነሱ የዘርፉ ችግሮች በሰከነ አግባብ እንደሚፈታ ያላቸውን ዕምነት በመግለፅ፤ እና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
~~~~~
ከቀኑ 10:55
~~~~~~
የሰራዊት አባላቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በቶሎ ፎቶ ተነስተው ህዝብ እንዲረጋጋ እንዲሰራ ለሚዲያዎች ትዕዛዝ ተላለፈ. . . ወታደሮቹም የህብረት ፎቶ ለመነሳት መረባረብ ጀመሩ።
~~~~
30/01/11
Filed in: Amharic