>

በአየር መንገድ  ውስጥ የተንሰራፋው ዘረኝነት ፓይለቱን ገበሬ አደረገው (ሚኪ አምሀራ)

በአየር መንገድ  ውስጥ የተንሰራፋው ዘረኝነት ፓይለቱን ገበሬ አደረገው
ሚኪ አምሀራ
አዴፓ አማራ በመሆኑ ምክንያት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ተባሮ ጎጃም ዉስጥ ገበሬ የሆነዉን ፓይለት እንዲሁ አይቶ ሊያልፈዉ አይገባም፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ ዘረኝነት የተጠናወተዉ ተወለደ በሚባል ጭንቅላቱ በዘረኝነት የሰከረ ሰዉ የሚመራ እና ብዙ ጉዳት ያደረሰ ሰዉ ነዉ፡፡ ለነገሩ በዚህ ዘረኝነቱ ፈጣሪም አልማረዉም አሸክሞታል (ግላዊ ስለሆነ እተወዋለዉ ነገሩን)፡፡
ነገር ግን አዴፓ በቀጥታ ማብራሪያ ከዚህ ድርጅት ሊጠይቅ ይገባል፡፡ ጉዳዩ የዚህ ልጅ ብቻ አይደለም ባለፈዉም ሌላ ፓይለት ተባሮ አሜሪካ እንደሚኖር በሰጠዉ ኢንተርቪዉ አይተናል፡፡ ልጁ ኦሮሞ ነኝ ቢላቸዉም እስከ አያቱ ስም በመጠየቅ የነፍጠኛ ስም ነዉ ያለህ አማራ ነህ አሉኝ ብሎ ቃለ መጠይቅ ሰቷል፡፡ ከዚህ በፊትም የባህርዳር ልጅ  ዘረኝነት ሲመረዉ አዉሮፕላን ይዞ ኢሮፕ ዉስጥ ጥገኝነት መጠየቁን እናስታዉሳለን፡፡
 እኔ የማዉቃቸዉ የዚህ አየር መንገድ ሰራተኞ እና በደማቸዉ አማራ የሆኑ ደሞዝ ብቻ እየተሰጣቸዉ ስራ ለ አንድ አመት እና ከዚያ በላይ እንዳይሰሩ ተደርገዋል፡፡ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ይልቅ እነዚህ arms length የሚባሉ መስሪያ ቤቶች በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸዉ፡፡
በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ በደል ሲያደርሱ የከረሙ ድርጅቶች ናቸዉ፡፡ አየር መንገድ፤ መብራት ሃይል፤ ቴሌ፤ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት፤ መንገዶች ባለስልጣን፤ ልማት ባንክ፤ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፤ የቅርስ እና ጥበቃ ባለስልጣን፤ የካርታወች ኤጀንሲ; ጉሙሩክ እና የመሳሰሉት ድርጅቶች አዴፓ ገብቶ የሚሰሩትን ስራ ሊፈትሽ ይገባል፡፡
አማራ የእኛ አሽትረይ ነዉ እያለ ሀገሪቱ ስንት ወጭ አዉጥታ ያሰለጠነችዉን ባለሙያ በዘሩ ምክንያት የሚያባር ሃላፊ ያለበት ድርጅት ነዉ፡፡ አዴፓ በፍጥነት ይሄን ጉዳይ አጣርቶ አስፈላጊዉን እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ አለበት፡፡የአየር መንገዱ ሲኢኦ መባረር አለበት፡፡
ጥቂቶች ግን የብዙዎች ምሳሌዎች!
1, ካፒቴን ሀይለመድህን አበራ (ባህርዳር)
2, ካፒቴን ዮሃንስ ተስፋዬ (ደጀን)
3, ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ (መርጦለማርያም)
4, ካፒቴን አለሙ ጌትነት (መርጦለማርያም)
5, ካፒቴን ታደሰ ሙሉነህ (መርዓዊ)
~አምስቱም በአማራነታቸዉ የተጠቁ ናቸዉ፣አምስቱም አዉሮፕላን አብርረዋል
~ካፒቴን ሀይለመድህን አበራ እና ዮሃንስ ተስፋየ አለምአቀፍ አብራሪዎች ነበሩ፣ ሁለቱም ጅኒየስ ተማሪዎች ሁለቱን በ4 ነጥብ ወደ ዩኒቨርስቲ የገቡ። ሀይለመድህን ተሰደደ፣ዮሃንስ አርሶአደር ሆነ
~ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ፣ አለሙ ጌትነት እና ታደሰ ሙሉነህ የአየርሀይል አብራሪዎች ነበሩ ሶስቱም በእስር ተሰቃይተዋል። ካፒቴን ታደሰ ሙሉነህ በደረሰበት በደል በህመም ስቃይ ላይ ይገኛል። ካፒቴን ምስረሻ እና አለሙ ያሉበትን ሁኔታ በደምብ አላቅም።
አማራ ስትሆን እንዲህ ነዉ። ከማንም በላይ ጭንቅላት ይዘህ ጭንቅላትህን ያቆሽሹታል፣ ይጠሉታል። በጣም ብዙ ዮሃንሶች፣ ሀይለመድህኖች፣ ማስረሻዎች፣ አለሙዎች፣ ታደሰዎች በየጥሻዉ አሉ። ቤት ይቁጠራዉ። ሚዲያ ቢኖረን ሁሉን ከያሉበት ይወጡ ነበር።
Filed in: Amharic