>

የአማራ ቴቪ እና የእነ አቶ ተወልደ ፍጥጫ መጨረሻው ምን ??? (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

የአማራ ቴቪ እና የእነ አቶ ተወልደ ፍጥጫ መጨረሻው ምን ???
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
የአማራ ቴቪ (ምሁ) የግፍ ሰለባው አብራሪ ዮሐንስ ተስፋዬ ላቀረበው ክስ የአየርመንገዱን ምላሽ ከቦታው ተገኝቶ እንደተቀበለና የአብራሪ ዮሐንስ ተስፋዬን የመልስ መልስ በማካተት ለሕዝብ እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡
አስቀድሜ ላስጠነቅቃቹህ የምፈልገው ነገር ቢኖር ትክክለኛ መልስ ከወያኔው ቡድን እንዳትጠብቁ ነው፡፡ ከእነ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ትክክለኛ መልስ የሚጠብቅ ሰው ካለ እጅግ ሲበዛ የዋሕ ነው፡፡ ለሚዛናዊነት ሲባል የሚሉት መሰማት ስላለበት “መጠየቅ ነበረባቸው!” አልን እንጅ የፈጸሙትን ግፍ አምነው ቃል ይሰጣሉ ብለን ጠብቀን አልነበልም፡፡ የአማራ ቴቪ (ምኩ) መረጃውን ይፋ ካደረገው በኋላ ሔዶ መጠየቁ ሰዎቹ ሐሰተኛ ሰነድ ሁሉ አዘጋጅተው የፈጸሙትን ግፍ ለማስተባበል በሚገባ እንዲዘጋጁ አድርጓቸዋል፡፡
እነ አቶ ተወልደ የአየር መንገዱ ሠራተኞችን እያባረሩ አየር መንገዱን ብቃት፣ አቅምና ችሎታ በሌላቸው ምድረ ትግሬ እንደሞሉት ማንም የሚያውቀው የአደባባይ ምሥጢርና በዓይን የሚታይ በእጅ የሚዳሰስ እውነት ነው፡፡ በአማራ የአየር መንገዱ ሠራተኞች ላይ ግፍ መፈጸሙ አዲስ አይደለም፡፡ ለዘመናት ሲፈጸም የቆየ ግፍ ነው፡፡ ከዓመታት በፊት ኃይለመድኅን አበራ የሚያበረውን አውሮፕላን (በረርት) እንዲጠልፍ ያደረገው የሚናገሩትን የማያውቁት እነ አቶ ተወልደ አብራሪ ኃይለመድኅን አእምሮውን ስለሚያመው ሳይሆን በዚህ ዘር ተኮር ጥቃት በመማረሩ ነው፡፡
በዚያ ሰዓት “ጀግናውና ከሀዲው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ!” በሚለው ጽሑፌ ላይ
እንደገለጽኩት እነ አቶ ተወልደ እራሳቸውን ከተጠያቂነት ነጻ ያወጡ መስሏቸው “አእምሮውን ስለሚያመው ነው!” ብለው ሐሰተኛ ምክንያት በመስጠት ለማስተባበል ሲጥሩ “አውሮፕላኑን አእምሮውን በሚያመው አብራሪ እንዲበር በማድረግ የመንገደኞችን ደኅንነት ለአደጋ አጋልጠዋል!” የሚል ክስ በአየርመንገዱ ሊያስነሣ መቻሉንና የአየርመንገዱን ገበያም በእጅጉ ሊጎዳው እንደሚችል እንኳ ማሰብ መረዳት መገንዘብ የማይችሉ ደናቁርት ናቸው እነ አቶ ተወልደ ማለት፡፡
እራሳቸውን ከተጠያቂነት ነጻ ለማውጣት በማሰብ ብቻ የዚህን ያህል ፍጹም ኃላፊነትና ተጠያቂነት የጎደለው ርቀት በመሔድ ለማስተባበል የሚጥሩ ሰዎች አሁን በአብራሪ ዮሐንስ ተስፋዬ ጉዳይም እውነትን ይናገራሉ ብሎ መጠበቅ ሲበዛ የዋህነት ነው፡፡
እነሱም ተጠይቀው ዘገባው እንዲቀርብ ፈልጌ የነበረው አንደኛ ሚዛናዊነት መጠበቅ ስላለበት፡፡ ሁለተኛ አንደበታቸው ቢዋሽ እንኳ ከገጽታቸው (from their facial expression) ብዙ የምንረዳው እውነት ስለሚኖርና ሳይዘጋጁ ሲመልሱ ብዙ የሚያመልጣቸው ነገር ይኖር ስለነበረ ነው፡፡
ዘገባው ከመቅረቡ በፊት አስቀድሞ መልስ እንዲሰጡ ተጠይቀው ቢሆን ኖሮ ድረገጻቸው ላይ “አየር መንገዱ ዘርን፣ ሃይማኖትንና የፖለቲካ አመለካከትን መሠረት ካደረገ አድልኦ ነጻ ነው!” ብለው ሐሰትነቱን ሳርቅጠሉ ሁሉ የሚረዳውን የማይመስል መልስ በአጭሩ ለመስጠት እንደሞከሩት ሁሉ ይሄንኑ መልስ በስልክ (በመናግር) በመስጠት ይሸኙ ነበር እንጅ እንዲህ እንደአሁኑ ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው ሁሉ ጓዳቸውን ክፍት አድርገው የተብራራ መልስ ለመስጠት አይሞክሩም ነበር፡፡ እኛም ግልጽ ለመሆን ካለመፈለጋቸው የምንረዳው እውነት ይኖረን ነበር፡፡
አሁን ግን ከተፈጠረው ሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሣ አገዛዙ ስለተደናገጠና እውነቱ አየር የመንገዱን ጉድ አጋልጦ አየርመንገድ ውስጥ ያሉ የእነ አቶ ተወልደን የወያኔ ቡድን እዚያ ቦታ ላይ ያለ ችሎታቸው፣ ያለ አቅማቸው፣ ያለ ብቃታቸው ሥራ እየጎዱና እያበላሹ መቀመጥ ፍጹም ተገቢ አለመሆንን አጋልጦ ከቦታቸው እንዲነሡ ስለሚያስገድድ ይህ እርምጃ ካልተወሰደ ደግሞ አየርመንገዱን ለከባድ ኪሳራ ስለሚዳርግ የአማራ ቴቪም እውነቱን እንዲያድበሰብስ ይደረግና ጉዳዩ ተዳፍኖ እንዲቀር ይደረጋል እንጅ የፈለገ ነገር ቢሆን ከዚህ በኋላ የአማራ ቴቪ (ምሁ) እውነቱን አፍረጥርጦ ለሕዝብ ይፋ በማድረግ እነ አቶ ተወልደ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይንቀሳቀሳል ብላቹህ እንዳትጠብቁ!!!
የአማራ ቴቪ እውነቱን ላፍረጥርጥ ካለ አብራሪ ዮሐንስ ተስፋዬ ብቻ ሳይሆን ከታች ፎቶውን (ምሥለ አካሉን) የምትመለከቱት የበረራ ሥልጠናውን በማዕረግ ተመርቆ ሥራ በጀመረ በወሩ የተባረረውን የአዲስዓለም መኮንንን እና የዐቢይ አበበን በማያውቁት ጉዳይ መባረራቸው አግባብ አለመሆኑን በማረጋገጥ ወደሥራ ገበታቸው ለመመለስ እስከ ፍርድ ቤት ድረስ ሔደው “ለደኅንነት አስጊ በመሆናቸው ነው ያባረርኳቸው!” በሚል ድፍን ያለ ምላሽ “አማራነት የደኅንነት ሥጋት ነው!” የሚል አሳፋሪ ምላሽ ተሰጥቷቸው አርፈው እንዲቀመጡ የተደረጉትን እጅግ አሳዛኝ የግፍ ሰለባዎችን ጉዳይ በመዳሰስ እነ አቶ ተወልደ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጽሙትን ግፍ ማጋለጥ ይችላል፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ ግፍ የተፈጸመባቸው ወገኖችም አሉ፡፡ የአማራ ቴቪ ለእውነት የቆረጠ መሆኑን ካዩ ይመጣሉ፡፡ የአማራ ቴቪ ይሄንን ጉዳይ እስከመጨረሻው የማይወስደው መሆኑን ካየን የአብራሪ ዮሐንስ ተስፋዬን ጉዳይ የዘገበው አስቀድሜ እንዳልኳቹህ እረሩ ተቃጠሉ ለማለት እንጅ ለፍትሕ እንዳልሆነ እንረዳለን!!!
ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
Filed in: Amharic