>
5:18 pm - Sunday June 14, 4511

ኢመማና  ዶ/ር ታየን በትዝታ (ጌች ባያፈርስ)

ኢመማና  ዶ/ር ታየን በትዝታ
ጌች ባያፈርስ
አንጋፋው የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር/ኢመማ/ በተነሳ ቁጥር ቀድም የሚታወሰው ዶ/ር ታየ ወልደሰማያት ነው ።በ1941ዓ ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት እድሜ ጠገቡ ኢመማ ከጃነሆይ ጀምሮ ደርግና የወያኔ መንግስትም ከባድ ብትራቸውን በማሳረፍ ጠንካራየማህበሩ አመራሮችን በማሰር  በመግደልና በማሰድድ ማህበሩን እያሸመደመዱ ለሆዳቸው ያደሩ መምህራኖችን እየሾመ  የመንግስት አገልጋይ ሲያደርጉት  ቆይተዋል።
የጃንሆይና የደርግ ጊዜን የማህበሩን እንቅስቃሴና አፈና ተወት አድርገን በዘመነ ወያኔ ሰለተፈጠረው ኢመማ በወፍ በረር ለትውስታ  እንቃኘው ።
ደርግ በወደቀ ማግስት በሽግግር መንግስቱ ወቅት በደርግ የነበረው የማህበሩ ወኪሎች ከደርግ ጋር አብሮ የወደቀ በመሆኑ  ወያኔ ማህበሩ በነፃነት እንድቋቋም በመፍቀዱ  ማህበራቸው በደርግ ጊዜ የሰርአቱ አገልጋይ ሆኖ መቆየቱ የቆጫቸው መምህራን ከየክልሉ/ከየክፍለሀገሩ/ከትም/ቤት ጀምሮ መምህራን ወኪሎቻቸውን በመምረጥ አገር አቀፍን ኢመማ በአስተባባረ ደረጃ ተመሰረተ።
ታድያ የየዞኑን መምህራነ ወክለው የመጡ ተመራጮች ለምያቸውና ለመምህሩ የሚቆረቆሩ ጠንካራና ትንታግ ነበሩ ።የአድስ አበባ ዮኒቨርስቲ ም እንደአንድ ዞን ድርሻ ሰላለው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር የሆነውን ትንታጉን ዶ/ር ታየን ወክሎ ላከ በኢመማ ምርጫም ዶር ታየ የኢመማ ፕሬዚዳንት ተደርጎ ሲመረጥ ከየዞኑ በባትሪ ተፈልገው የመጡ የሚመስሉት እነገሞራው ካሳ እነአሰፋማሩ እነአወቀ ሙሉጌታ እነአባተአንጎሬ እነጌታቸው ፈይሳ እነሽመልሰ ታየ የመሳሰሉትን በሰራ አሰፈፃሚነት መርጦ በማሰለፍ በወቅቱ እየተረቀቀባለው አድሱ የትም/ፖሊሲ ውይይት ላይ ማህበሩ በመጋበዙ  ትም ፖሊሲው ትልቅ ችግር ያለበት የወያኔ ፖለቲካ ማረመጃ እና ትውልድ ገዳይ መሆኑንና እሰራ ላይ እንዳይውል ኢመማ መምህሩን በመያዝ ተቃውምውን አሰማ በመላሀገሪቱም ከፍተኛ ተቀባይነት በማገኘት መምህራንንም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ በአጭር ጊዜ ውሰጥ ከጎኑ ማሰለፍ በመቻሉ ኢመማ ወያኔ ጥርስ ውስጥ ገባ የአለም መ/ም ማህበርም ከኢመማ ጎን በመቆም ሞያዊ ድጋፍን አደረገ።
ወያኔም ሳታሰበው ብቅ ያለባትን የመምህራንን እንቅስቃሴ ለማፈን ማህበሩን በካድሬ መምህራን ጠልፎ በመውሰድ አሻንጉሊት ማህበር ለመፍጠር በጀት መድባ ተንቀሳቀሰች።
የወቅቱ ጠ/ሚር መለሰዘናዊ ኢመማን ማፍረሰ እንዳለበት ለካቢኔዋቹ ሲናገር”ኢሰፓን ከማፍረስ ኢማን ማፍረስ “ይቀድም ነበር በማለት በቁጭት ተናገሩ።
በንግግር ብቻ አልቆሙም በሚችሉበት የፈጠራ ክስ በማቀናበር ዶ/ር ታየ ለሰራ ጉብኝት አውሮፖ ኦንደሄደ የኢመማን ቢሮ በፌደራል ፓሊሰ በመውረር የኢመማን  ሰነድ ተሸክመው በመውሰድ ታየ የህቡዕ ድርጅት ሊመሰርት ነው በማለት ውጭ እንደወጣ እንድቀር ፕሮፕጋንዳ ለቀቁ ታየ ግን የኢመማን ትግል ለማኮለሸት ታሰቦ እንደሆን ሰለገባው ሁለት የአውሮፓ መም/ማህበር ተወካዮችን አሰከትሎ ሀገሩ ሲገባ ከቦሌ አውሮኘላን ማረፊያ ፌደራል ፖሊስ ተቀብሎ መረማሚያ ቤት በማስገባት የሸብር ድርጅት ለመመሰረት በማለት ክስ መስርቶ የ15አመት እሰራት ፈረደበት።
ወያኔ ዶ/ር ታየን ብታሰርም ማህበሩን በፈለገችው መልኩ በአጭር ጊዜ መማረክ ልቻለችም ትንታጉ ስራአሰፈፃሚ ከአለም መም/ማህበር በሚደረግለት ድጋፌና በየዞኑ ባለው መዋቅሩ በየአመቱ ጉባኤውን እያደረገ ቢሮውን አላሰረክብም ብሎ ፍ/ቤት ድረስ ሙግቱን ቀጠለ ይሄም ሁኔታ ወያኔ ሰላላሰደሰታት የኢመማ ዋና ፀሀፊና የኢሰመጉ ሰራ አሰፈፃሚ የነበረውን አቶ አሰፋ ማሩን በጠራራ ፀሀይ ከቤቱ ወደ ቢሮው ሲጓዝ በበርካታ ጥይት እረሸኑት አቶ ገምራው ካሳም ለሰራ እንደወጣ እንግሊዝ አገር በስደት ቀረ ።
ጉዳዪ የአሰቆጣው EI/educational International/የአለም መም/ማ  እንድሁም የተለያዩ የአለም አቀፍ የምያማህበሮች ባሳደሩት ተፅኖ ዶ/ር ታየ ከ6አመት እስራት በኋላ ሲፈታ መጀመሪያ የመጣው ወደኢመማ ቢሮ ነበር እንድህ እያለ ኢመማ በጠንካራ አመራሮቹ እስከ1998ድረስ ቢሮውን ይዞ  ከአለም አቀፍ መም/ማህበርና ከየዞኑ ካሉ አባላቶቹ ጋር እየታገለ በፍ/ቤት ክርክር ቢቆይም በየዞኖ ያሉ ጠንካራ ምህራኖች እየታደኑ ለስራትእና ከስራ መባረር የትምህርት እድል መከልከል ወዘተ የተቀበሉት የመከራ ፅዋ ሲሆን በመንግሰት በኩል እውቅና የተሰጠው ተለጣፋው ኢመማ በወ/ሮ ገነት ዘውዳ ፋታውራሪነት ትአዛዝ እየተቀበለና በጀት ተመድቦለት የመንግስት ቢሮ ተሰጥቶት ስራውንቀጥሊል ።
የቅንጅት አመራሮች ሲታሰሩና ሲከሰሱ ለሰራ እውጭ የነበረው ዶ/ር ታየም አብሮ በለለበት ተከሰስ የኢመማን አመራሮችንም ከቢሮ በማሰወጣት ተለጣፌው ማህበር ወደ ኢመማ ቢሮ ከ14አመት ትግል በኋላ ኢመማ በጉልበት ተወሰደ ዶ/ር ታየም  የሚወደው አገሩንም ሆነ ማህበሩን ተነጥቆ በአሜሪካን አገር በችካጎ ዮኒቨርስቲ  በምህርነቱ እያገለገለ ይገኛል ኢመማና ታየ በከፈሉት መራራ መሰዋዕትነት ሳይነጣጠሉ በመምህራን አምሮ ዛሬም ይኖራሉ።
ለዛሬው በዚሁ ልቋጨው።
Filed in: Amharic