>
5:13 pm - Sunday April 19, 1671

ጀነራል ሰዓረ መኮንን ከጠ/ሚኒስትሩ የተሻለ ግልፅነት አለው! (ግዛው ለገሰ)

ጀነራል ሰዓረ መኮንን ከጠ/ሚኒስትሩ የተሻለ ግልፅነት አለው!
ግዛው ለገሰ
– አብይም ዘይኑም የነገሩን 240 ጦር እግረ መንገዳቸውን ድንገት ቤተመንግስት እንደመጡ ነው፤
– እኛም ከሁኔታው ተነስተን፣ በተነገረን ተመርኩዘን ወታደሮቹ ድንገት እንደተከሰቱ አምነን ነበር፤
– እነአብይ ነገሩ አስደንግጥዋቸው 3G ሆነ የቢሮዎች WiFi ሳይቀር ሲዘጉ፣ እኛ ደግሞ ኢንተርኔት መቆሙ ከሚወራው ሁኔታ ጋር ተደምሮ ነገሩ መፈንቅለ መንግስት እንደሆነ ገመትንና ተረበሽን፤
– አብይ ደግሞ በማይረባ ወሬ ከመረበሽ ተቆጠቡ አለን፤ እኛም ለአብይም ቢሆን ዱብዳ ስለነበር ለሕዝብ የሚረባ ወሬ ለማድረስ ሁኔታው አልተመቸ ቢሆን ነው ብለም የጠ/ሚኒስትሩን ግሳፄ ተቀበልን (የሸገሩ አብዱ አሊ ዛሬ አንጀቴን አርሶኛል በዚህ ጉዳይ)፤
– የጀነራል ሰዓረን መግለጫ ስንሰማ ግን ነገሩ ውሎ-አደር ነው፤
– ከአንድ ቀን በፊት ወታደሮቹ ከአለቆቻቸው ጋር እሰጥ-አገባ አድርገዋል፤ ማታ ተሰብስበው ካልሰማችሁን ወደ መከላከያ ሄደን ለበላይ ኃላፊዎች አቤት እንላለን ብለዋል፤
– ጠዋት ላይ ወታደሮቹ እየተደዋወሉ አብይ ጋር እንገናኝ መባባላቸውን ጀነራል ሰዓረም ያቃል፤ አውቆም ለቤተመንግስት ጥበቃ በጠዋት ነግሬያለሁ ብልዋል፤
– ነገሩ ዱብዳ አልነበረም፤ ግን እንደጀነራሉ አባባል ጦሩ በአንዴ አልመጣም፤ በታክሲ እንዲሆም የቤት መኪና ሁሉ አስገድደው እየተንጠባጠቡ ነው አብይ ጋር የደረሱት (አብይ ሀገር ውስጥ ወይም አዲሳባ እንደነበርም መረጃ ሳይኖራቸው አይቀርም)፤
– ነገሩን ከመነሻው መቅዋጨት እንደተሳነው ግልፅ ቢሆንም፣ መንግስት ተሸብሮ ሕዝብ ማሸበሩን ያመነልን አካል አልነበረም፤
– አብይ «ወጣቶች ናቸው» ቢልም ጎልማሳ መሣሪያ የታጠቁ በመሆናቸው ቤተመንግስት ከደረሱ ወዲያ ኃይል መጠቀም አሽቸጋሪ እንደነበርና በዘዴ ትጥቅ እንዳስፈትዋቸው ጀነራል ሰዓረ ይናገራል፤
– ወታደሮቹ ይህን በመፈፀማቸው መከላከያንም አብይንም አዋርደዋል፤ አብይ ደግሞ የፑሽ-አፕ ቅጣት ብቻ ወስኖባቸው አብሮ ቅጣቱን ሲፈፅምና እራት ሲጋብዝ መከላከያን ይባስ ማዋረድ ሆነ፤
– ይህ ደግሞ ኢታማዦሩን ጨምሮ የሁሉንም ዕዝ አባላት ያስቆጣ ይመስላል፤ ፑሽ-አፑን ወዲያ ብሎ ጀነራል ሰዓረ ስለወታደራዊ እርምጃ አነሳ፤ ከፍተኛ ሕገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙን ገለፀ፤
– የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አቅልሎ ያየው ጉዳይ ተገቢ እንዳልነበር የኢታማዦሩ መግለጫ ያመላክታል፤ ሰዎች መታሰር ጀምረዋል፤
ለማጠቃለል ያህል . . .
– አብይ ነገር አብርዶ ሊሆን ይችላል፤ ግን ለቀናት የሚራብ ለዚያውም ልዩ ኮማንዶ የሆነ ጦር ኢትዮጵያ እንዳላት በይፋ ማመኑ ቁጥሩን ሊያሳንስለት ይችል ይሆናል እንጂ የፑሽ-አፕ ቅጣቱ ለእርሱም ለጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዡ ተገቢ ነበር፤
– ጀነራል ሰዓረ እንደሚለው 240 ጦር ቤተመንግስት እንደሚመጣ ቀድሞ ይታወቅ ከነበረ፣ ችግሩን በብስለት ፈታነው ብሎ ማውራት ሕዝብ ላይ መሳለቅ ነውና አብይም፣ ጀነራሉም፣ ኮሚሽነሩም በተዋረዳቸው ፑሽ-አፕ መስራት ይገባቸዋል፤
– ይህ ነገር ለውጡን በሚያደናቅፉ ኃይሎች የተቀናበረ ከሆነ ግን እኛም አንድ በአንድ ፑሽ-አፕ መስራታችን አይቀሬ ይመስላል፤ ሀገር አደጋ ላይ መሆንዋ እርግጥ ሆነ ማለት ነውና፤
– በሌላ በኩል ይህ ክስተት የሆኑ ሰዎችን ለመምታት የተደረገ የራሱ የአብይ ሳቦታዥ ከሆነ ደግሞ፣ የኢሕአዴግ ጥልቅ ተሀድሶ በትክክል ይገለጥልናል፡፡
Filed in: Amharic