>

ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ!!!
ቬሮኒካ መላኩ
” የባለፉትን 3ሺ አመታት አማራና ትግሬ ኢትዮጵያን  ገዝቷል ፣ የሚቀጥሉትን 3ሺህ አመታት ደሞ አገር የመግዛት ተራው የኦሮሞ ነውii”   
ሌንጮ ባቲ  የ ODF  ስራ አስፈፃሚ
የግሪክ ፈላስፎች ” ፖለቲከኛ ከመሆኑ በፊት ሰው እናድርገው ” የሚል ድንቅ አባባል  አለቻቸው። የሰው ልጅ  ከአውሬነት ባህሪው ተሞርዶ ተስተካክሎ ወደ ሰውነት ሳይሸጋገር  ፖለቲካ ውስጥ  ዘሎ ከገባ እንደ ኢዲ አሚን ዳዳ ወይም እንደ ሌንጮ ባቲ  የመሆን እድሉ ሰፊ ስለሆነ ” ፖለቲከኛ ከመሆኑ በፊት ሰው እናድርገው ።” ይላሉ።
አፍሪካ ጉደኛ አህጉር ነች ። አሁንም እውነተኛ ህልምን ከቅዤት ፣ ባዶ ተስፋን ከተጨባጭ ተስፋ መለየት የማይችሉ ዘገምተኛ ፖለቲከኞችን መፍጠር አላቆመችም።
ሲግመን ፍሮይድ The future of an illusion  ” የሚለው መፅሀፉ ላይ አንድ የሌንጮ ባቲ  አይነት የተምታታበትና “ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ ” ገፀ ባህሪ አለው።
በሌላ በኩል ሌንጮ ባቲ የፃፈውን ሳነብ ከክርስቶስ ልደት በፊት 210 አመት በፊት ቂን ሺ ሃውኛ የተባለ የቻይና ንጉስ  …<< ሜርኩሪ ዘላለማዊ  ህይወትን ይሰጣል ፣ ሜርኩሪ ከሞትም ያስቀራል ።>> ተብሎ  ስለተነገረው ዘለአለም ለመኖርና ንጉስ ለመሆን አስቦ አንድ ኩባያ ሙሉ ዝልግልግ ሜርኩሪ ጠጥቶ ዘላለም ኖሬ እገዛለሁ ብሎ አስቦ  በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ሞት ትኬቱን የቆረጠውን ንጉስ አስታወስኩኝ ።
በዚህ በ21ኛው ክዘ የሰው ልጅ በአእምሮ ጭማቂ በሆነው እውቀት በሚመራበት ዘመን እንደ ሌንጮ ባቲ ያለ ቆሞ ቀር መመልከት ኢትዮጵያ አሁንም የሰው ልጆች ማቆያ Zoo እንደሚያስፈልጋት አምኛለሁኝ።
የጀርመኑ ናዚ  መሪ አዶልፍ ሂትለርም  የአሪያን ዘር የሆነው ናዚ ፓርቲ ለ 1ሺህ አመታት ይገዛል ብሎ ፎክሮ በ12 አመታት ብቻ  ነበር ዶግ አመድ የሆነው።
ሌንጮ ሆይ  እስኪ ቀጣዩ 3ሺህ አመታት ይቆይልህና አንድ አመት እስኪ ደፍናችሁ የሰከነ አገር በሰከነ አመራር ስታስተዳድሩ አሳዩን?
ገና 5 ወራት ሳትደፍኑ 5ጊዜ መፈንቅለ መንግስት 2 ጊዜ የግዲያ ሙከራ እርስ በራሳችሁ ያስተናገዳችሁ ጉዶች አገሪቱንም ምድጃ ላይ የተጣደች ብረድስት ያደረጋችሁ ጉዶች  “ፅድቁ ቀርቶብኝ በውል በኮነነኝ ” እንደተባለው 3 ሺህ አመታት ትቃዣላችሁ።
Filed in: Amharic